“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጋምቤላ ክልል ሙሉ በሙሉ ለውጡን ተቀላቀለ፤ ድግሱ አደገኛ ነበር – የአፋር ክልልም አዲሱን የለውጥ ጎዳና በይፋ ሊቀላቀል ነው

ኢህአዴግ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ስር ነቀል ለውጥ አይቀበሉም የተባሉት አጋር ፓርቲዎች ቀስ በቀስ የለውጡ ባቡር ላይ እየተሳፈሩ ነው። የሶማሊ፣ የአፋር፣ የቤኒሻንጉልና የጋምቤላ ክልሎች ለውጡን እንዲቀበሉና ከለውጡ ጋር ተመሳስለው እንዲሄዱ መንግስት በጥንቃቄ መንቀሳቀሱንና እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ በተደጋጋሚ እያስታወቀ ነው።

ለመንግስት አደገኛ ፈተና ይሆናል የተባለው የሶማሊ ክልል ሃይል፣ በደም ተጨማልቆ፣ ይህንኑ የደም አበላ ጉዞውን እንደሚገፋበት በችግሩ ላይ ቤንዚን በሚያርከፈክፉ አማካይነት ብዙ ቢባልም፣ መሪውና አበሮቻቸው ወህኒ ገብተው ክልሉ ሰላም ሰፍኖበታል። እጅግ የሚቀፍ፣ ለሰሚና ለተመልካቹ ግራ የሚያጋባ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቆ በንጹሃን ደም ሲታጠብ የነበረው የአብዲሌ መንግስት ተሰባብሮ በምትኩ አዲስ ካቢኔና አስተዳደር ተመስርቶ ሂደቱ ቀና እየሆነ ነው።

ጋምቤላ በኦሞት ምትክ በተተኩ በጋት አማካይነት በዝርፊያ ተጠብሳ የከረመች በመሆኑ ለውጡን ላለመቀበል ኑዌርንና አኘዋክን በብሄር ለማባላት እቅድ ተነድፎ ነበር። ፕሬዚዳንቱ ከኑዌር ጎሳ በመሆናቸውና የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ሪቻርድ ማቻር የሳቸው ወገን በመሆናቸው ወጥመዱ አካባቢውን እንዲያነድ ተደርጎ መወጠኑን መንግስት አስቀድሞ ይረዳል።

ጋት ሉዋክ ይህንን ያደርጉት ከስልታን ከወረዱ በዝርፊያ ስለሚጠየቁ ከፍርሃቻ በተነሳና በሌሎች ለውጡ ስጋት በፈጠረባቸው ወገኖች ግፊትና አይዞህ ባይነት ነበር። የክልሉን ጉዳይ የሚከታተሉ እንዳሉት በዚሁ መነሻ ከፍርሃቻና በትዕዛዝ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት አካባቢውን የግጭት ቀጠና ለማድረግ ጋት ሉዋክ መንደራቸው ገብተው እያስታጠቁና እየቀሰቀሱ ነበር። መሳሪያውን በገፍ የሚገባው ከደቡብ ሱዳን ነበር።

አካሄዱን የተረዳው መንግስት የኑዌር ህዝብ እንዳይሳሳት ጉዳዩን በቅርብ ይከታተል ጀመር። በበቂ ዝግጅት ከዳር ሆኖ ከመከታተሉ በላይ ግን የኑዌር ተወላጅ የሆኑ አክቲቪስቶች ጋት ሉዋክን እግር ለግር እየተከታተሉ ቅስቀሳውን አመከኑበት። የአኝዋክ የኑዌር ህዝብ ጭቁን ሕዝብ ለሌቦች ሲባል የሚጋጩበት ምክንያት አለመኖሩን በማሳመን የጋት ሉዋክና ከጀርባ ያሉትን ሴረኞች ተንኮል አመከኑ። ከዛም ጋት ግምገማ ለመቀመጥ ተገደዱ። በግምገማው ለሚቀርብላቸው ጥያቄ መልስ መስጠት አቅቷቸው ፌንት እስኪያደርጉ ድረስ ተናዘዙ። ከነ ምክትላቸው ድርጅቱንም ከመምራት ተገለሉ። አድሱ የድርጅቱ መሪ አቶ ኡመድ ኡጁሉ አዲስ አበባ ላይ ምክትል ሊቀመንበር እንዲሆኑና ለጋት ወዳጅ የሊቀመንበርነቱን ቦታ እንዲያስረክቡ በተገዙ አስገምጋሚዎች ቢታዘዙም አሻፈረኝ ብለው የክልሉ መሪ ሆኑ።

ዛሬ ለምንግስት ሚዲያዎች እንዳሉት ግምገማው እስከ ወረዳ እና ቀበሌ ይዘልቃል። ለውጡን ተግባራዊ እናደርጋለን። ለህዝብ ጥያቄ መልስ እንሰጣለን። ሌቦችን ለህግ እናቀርባለን በማለት በፊትለፊት ተናገሩ። እናም የጋምቤላ ጉዳይ በዚሁ ተቋጨ። ጋምቤላ ተደመረች። ለወትሮው ትዕግስት ያጡ ብዙ ቢሉም ልክ በሶማሊ ክልል እንደሆነው በርጋት ጋምቤላ ከተደገሰላት ግጭት ተረፈች።

በሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ እየተናጠ ያለውና ለውጡ ወደ ክልላቸው እንዲገባ በስፋት እየጠየቁ ባሉ ወገኖች ትግል ግራ የተጋባው የአፋር ክልል አመራር ከዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በስተመጨረሻ ለመወያየት ተገዷል። የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አመራሮች የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር በተደረገው ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማይቀረውንና የማይቀለበሰውን የህዝብ ጥያቄ መመለስ አማራጭ እንደሌለው በማስረዳት ተሰብሳቢዎቹ ከስምምነት እንዲደርሱ ሆኗል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው በዛሬው ውይይት ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀናጀት በክልሉ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈንና ለማጠናከር እንዲሁም ጎን ለጎን ሌሎች ችግሮችን ለመቅረፍ ከስምምነት መደረሱን ይፋ አድርጓል።አቀፍ ደረጃ የተጀመረዉን ለዉጥ በአፋር ክልልም በመተግበር ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድርግ ስራ እንደሚጀመር መግባባት መፈጠሩ ይፋ ሆኗል። ይህ ብቻ አይደለም አገራዊ ለውጡ የክክሉን ወጣቶች በሚያሳትፍ መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆን እቅድ ወጥቷል። አሁን የቀረው ልክ እንደ ሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አይነት ሰው አፋርን እንደሚያስተዳድር ይፋ ማድረጉ ብቻ ነው።

ቀጣዩ ክልል ቢኒሻንጉል እንደሚሆንና ቤኒሻንጉል ላይም ስራ እየተሰራ መሆኑ ታውቋል። የቤኒሻንጉል ጉዳይ ከተቋጨ መንግስት ወደ ድንበርና ማንነት ውዝግብ እንደሚያመራ ነው ውስጥ አዋቂዎች የሚናገሩት። እንደ እነዚህ ሰዎች ገለጻ ህዝብ የሚያምነውን መሪ በማስተዋል መከተልና እገዛ ማድረግ፣ አፍራሽ ሃሳቦችን በመጠየፍ ለውጡን በሙሉ ልብ መደገፍ፣ ለመሪውና ለእቅዶቹ ጊዜና አክብሮት መቸር ብቻ ነው። አለበለዚያ በስሜትና በአጉል ምኞትና በስልጣን ጥማት በሚሰራ

 

0Shares
0