“Our true nationality is mankind.”H.G.

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከተፎካካሪ ፓርቲ ጋር ቀጠሮ ያዙ፤ ሜዳውም ፈረሱም ያው!!

ላለፉት ሶስትና አራት ወራት ከአንዳንድ ተፎካካሪ ድርጅቶችና ፍላጎታቸው በውል የማይታወቅ አክቲቪስት ነን ባዮች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለውይይት በራቸውን ዘጉ፣ ሃሳባችን አልተደመጠም፣ አገሪቱ ፍኖተ ካርታ ያስፈልጋታል፣ ተመልካች ሆን፣ የሽግግር መንግስት ያስፈልገናል ወዘተ በሚል ሲወቅሱ መቆየታቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ አሁን ለፊታችን ማከሰኞ ለውይይት ተጋብዘዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገና ወደ ሃላፊነት ከመጡበት ሰዓት ጀምሮ በግልጽ እንደተናገሩትና በተግባር እንዳሳዩት አገር ቤት ያሉትን ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭ ሆነው የተቆለፈባቸው ሳይቀሩ ወደ አገር ቤት እንዲገቡና ነጻ አውጪነታቸው ተረስቶ እነሱ ነጻ እንዲወጡ መደረጉን አብዛኞች በክፍተኛ አክብሮትና አድናቆት እየገለጹ ነው።

የተጀመረውን ለውጥ ለማጨናገፍ ከሚደረገው ጥረትና ሴራ ባልተናነሰ አንዳንድ ተፎካካሪ ፓርቲ የሚባሉና አቋማቸው በውል የማይታወቅ አክቲቪስቶች በየቀኑ ቆዳቸውን እየቀያየሩ የሚያሰራጩት ሃሳብ ህዝቡን ግራ እያጋባው እንደሆን የሚገልጽ፣ ለማክሰኞ የተጠራው ስብሰባ ለህዝብ ይፋ እንዲሆንና ህዝብ እንዲታዘብ ቢደረግ ሲሉ ይጠይቃሉ። ውይይቱ እንደሚካሄድ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮን ጠቅሶ ፋና ይህንን ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር በቀጣዩ ምርጫ ዙሪያ ሊወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን አሁን ላይ በሀገሪቱ ስለተጀመረው የዴሞክራሲ ለውጥ እና በሚቀጥለው ዓመት የሚደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ነፃ እና ፍትሃዊ ለማድረግ ሊወሰዱ በሚገባቸው አስፈላጊ ለውጦች ዙሪያ እንደሚወያዩ ነው የተገለጸው።

ውይይቱ በሚቀጥለው ማክሰኞ ህዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዳራሽ እንደሚካሄድም ታውቋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ እንደሚያመላክተው በውይይቱ ላይ የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

በሀገር ውስጥ የተመዘገቡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና በመንግስት ጥሪ ተደርጎላቸው ከውጭ ሀገር የተመለሱ ፓርቲወች በውይይቱ ይሳተፋሉ ተብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሰኞ ህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ድረ ገጽ መመዝገብ ይችላሉም ነው የተባለው።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››
0Shares
0