“Our true nationality is mankind.”H.G.

የፍትህ ሰቆቃ – በዚህ ግፍ ከማፈርና ከማዘን ይልቅ ጎራ ለይቶ መከራከር አውሬነት ነው !! የግል እስር ቤት ያላቸውስ…

ሰሞኑን ይፋ የሆነው “የፍትህ ሰቆቃ” የሚለው ዶክመንታሪ እጅግ የከፋ ስሜትን ፈጥሯል። መረጃው ስሜትን ክፉኛ አጎምዝዟል። ማንም ይሁን ማን ይህንን ክፉ ተግባር ከማውገዝ ይልቅ ጎራ ለይቶ ክርክር ውስጥ መግባታቸው መስማትና ማየት ከተፈጸመው ግፍ በላይ አሳዘኝና አውሬነት ይሆናል። ማንም ሰብአዊ ፍጡር ይህንን አውሬነት የተላበሰ አሳፋሪ ተግባር ለማስተባበል ሲሞክር ማየት እጅግ ያማል። ግን መንግስት ምነው የግል እስር ቤት ያላቸውን ምስለኔዎች ዝም አላቸው? የሚለው ጉዳይ ግን የፍትህ ሰቆቃን ጎዶሎ ያደርገዋል።

በአዲስ አበባ እንዳሻቸው የሚጋልቡ፣ ህግና ስርዓት የማይገታቸው፣ የራሳቸው ጥበቃ፣ እስር ቤት፣ ጡንቸኞች፣ ቅጥር ነብሰገዳዮች ያሉዋቸው እንዳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ጠንቅቀው ያውቃሉ። እሳቸው የመሩት የምርመራ ሪፖርትም አለ። ከዛም በላይ የዛሬ ሃብታም የቀድሞ ታጋዮች ይህንን ጉዳይ ጠንቅቀው ያውቁታል። አገር እንመራለን ሲሉ የነበሩት ለተገዙ ባለስልጣናት ሚስጢር አይደለም። በአንድ ቀጭን ስልክ ትዕዛዝ ንጹሃንን የሚያስገርፉ፣ የሚያሳስሩ፣ በቡድን የሚያስወነጅሉ እንዴት ዝም ይባላሉ። ሕዝብ በተሰበሰበበት ወጣቶችን በፊደራል ፖሊስ በትዕዛዝ ሲያስቀጠቅጡና አንዳንድ አመራሮችን ሲያሸማቅቁ የነበሩ እንዴት ፍትህ አናሰፍናለን ለሚሉ ሃይሎች ይከብዳል።

[wpvideo 96ODUEpX]

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ሚስቶቻቸውን የተነጠቁ፣ የእገሌን ውሽማ ለምን አየህ በሚል የተገረፉ እንዳሉ ሚስጡር አይደለም። ገንዝብ በህገወጥ የሚያጓጉዘው አውሬ ከመንግስት እይታ ውጭ ነው? ድሆችን በጥቂት ገንዝብ በመግዛትና በመደለል ወንጀል የሚያስፈጽሙ ወሮበላዎች ለኦህዴድ ባለስልጣናት ድብቅ ናቸው? ሲታገሏቸው የነበሩትን የኦህዴድ አንበሳ ታጋዮች ከድርጅትና ከሃላፊነት እንዲሁም ከስራቸው እንዲባረሩ ሲያደርጉ መኖራቸው ይረሳል? 

እስኪ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ወይም የእንባ ጠባቂ ኮሚሽን በኦፊሳል ጥሪ ያቅርብና ያጣራው። የዝግ ቤቶቹ ሚስጢርና የግል እስር ቤቶች ሚስጢር ገሃድ ይሆናል። የግል ሚዲያዎችም ይህንኑ ጉዳይ መርምሩ!!

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0