“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሁሌም እውነት ይነገር – ጓንጉል ተሻገር

… ጉድ አልን። ራሳችን ይዘን በወቅቱ በተነገረው ውሸት አዘንን። ይሄ መቸም አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው። በሬ ወለደ ነው። ባህላችን “ሙት ወቃሽ አታድርገኝ” ይላል እኔ ግን ይህንን ቅጥፈት ሳላጋልጥ መተው አልፈልግም። ቅጥፈት ቆሻሻ ነገር ነው።

ውሸት/ቅጥፈት/ ቆርጦ ቀጥልነት የግለሰብ በሽታ ብቻ አይደለም። የቡድን በሽታም ነው። ቅጥረኛውንና አገር ሻጭ ባንዳውን ሳይጨምር እኛ ኢትዮጵያውያን ደግ አዛኝ ክፋት የሌለብን፣ ቅጥፈት የምንጠየፍ ከሁሉ በላይ ጀግኖች ነን። የአድዋ የማይጨው ወዘተ ጀግንነት ታሪካችን እስካሁን ድረስ በየዓመቱ ይከበራል። ድላችን የመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት ነው። ዓለም በአድናቆት መስክሮልናል። እኛ ኢትዮጵያውያን የድል ቀን/በዓል/ እንጂ የነፃነት ቀን አናከብርም። ቅኝ ስላልተገዛን ነፃ የወጣንበት ቀን የለም፣ ቅኝ ሊገዛን የሞከረ በወቅቱ የአውሮፓ ትልቅ ኃይል የነበረውን ድባቅ የመታንበት፣ ወደ ትብያነት የቀየርንበት የድል ቀን ነው የምናከብረው። ይሄ አንፀባራቂ ማንነታችን ነው። 


ወደተነሳሁበት ልመለስ። ውሸት ሰብሰብ ተብሎም በቡድን ይዋሻል። የፖለቲካ ቡድን ይዋሻል።መንግስት ተኩኖም ይዋሻል። ህዝብ በረሀብ እያለቀ 11% አድገናል ተብሎ ይነገራል። ይቀጠፋል።የጋምቢያ መሪ የነበረው ሙዝ ቆራርጦ እያጎረሰ የኤድስ ሕሙማንን ፈወስኳችሁ መድኃኒት አትውሰዱ ብሎ ከልክሏቸው በርካታ ሕሙማን አልቀዋል። ዓለምን ያስደነገጠው ግን ሙዝ አብልቶ ድናችኋል ያለው እብድ መሪ ሳይሆን የካምብሪጅ የሜዲሲን ምሩቅ የሆነው የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በቢቢሲ ተጠይቆ ልክ ነው የጋምቢያ ፕሬዝዳንት የኤድስ መድኃኒት አላቸው። ብዙ ታማሚ ፈውሰዋል ማለቱ ነው። ይሄ ዓለምን አስደንግጧል። 
በኛ ሀገር ስብስብ ብለን የምንዋሽበት አጋጣሚ የቀብር ስነ ስርአት ላይ የህይወት ታሪክ ሲነገር ነው። በቃ አንዴ ላይመለስ ሄዷል በሚል አረመኔ ነፍሰ ገዳይ የነበረው ሁሉ “ደግ ሩህሩህ አዛኝ የተቸገረ የሚረዳ” ይባልለታል። አንድ አምታች የነበረ ድፍን የአዲስ አበባን ህዝብ ውጭ ሀገር ልላካችሁ እያለ በርካታ ሺዎች ብር ከያንዳንዱብየተቀበለ አብሮ አደግ ሲሞት የህይወት ታሪክ እናነባለን ሲባል፣ አንድ አጠገቤ የነበረ ሰው ቀስ ብሎ ሰው ሳይሰማው ምን የህይወት ታሪክ አለው ያጭበረበራቸው ሰዎች ስም ዝርዝር ይነበብልን እንጂ ሲል ቀብር ላይ ሳቅ መቆጣጠር አቃተን። ከጎናችን የነበረ አንድ ሰው ነውር ነው ‘ሙት ወቃሽ አትሁን’ ብሎ ጓደኛችንን ገሰፀው። እሺ እሺ ተባባልን የህይወት ታሪክ የተባለውን አዳመጥን “ደግ አዛኝ ሩህሩህ” ተብሎ ተነበበ። አለቀ።

This image has an empty alt attribute; its file name is gwangule-teshagere-1.jpg
አቶ ጓንጎል ተሻገር


ታዋቂ ሰው ሲሞት ውሸቱ በጣም ይበዛል። ቀብር ቦታ ብቻ ሳይሆን በሬድዮ በቲቪ ሁሉ ይዋሻል።ይቀጠፋል።ቅጥፈቱ ለአንድ ቀን ሳይሆን ለወር ሊሆን ይችላል ። ህዝቡ አዝኗል ዘፈን እንዳይዘፈን ይባላል። ሬድዮ ቱቪ ወር ሙሉ ክላሲካል ብቻ ይሆናል። ሰውም ለዚህ ቅጥፈት ይተባበራል። ድንኳን ተደኩኖለት የሟች ፎቶግራፍ ፊት ለፊቱ ተለጥፎለት እዬዬውን ያቀልጠዋል። ጥቁር ልብስ ለወራት ይለብሳል።
በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ የንጉሱ ሚስት እቴጌ መነን እና ልጆቻቸው በተለያየ ጊዜ ሲሞቱ አብሬ ካልተቀበርኩ ብሎ ጉድጓዱ ውስጥ ገብቶ ያስቸገረ ብዙ ሰው እንደነበር የድሮ ሰዎች ሲያወሩ ሰምተናል። ለቀስቶኛውም ሰውየው አፈር መለስ ማድረግ ቢጀመር በሮ እንደሚወጣ እያወቀ ኧረ ከጉድጓዱ አውጡት ብሎ የውሸቱን ያጫጭሳል ፣ ያለቅሳል ይጯጯኃል።መለስ ዜናዊ የሞተ ጊዜ የሆነውን አይተናል። መድገም አያስፈልግም። ህዝባችን ግምት ውስጥ ወድቋል። ህዝብ ንና በሩጫ የምናከብራቸው ሰዎችም በውጭ ሚድያ መሳቂያ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ሰሜን ኮርያ ሆነች ሁሉ ተብሏል
በቅርቡ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሞተዋል። ያው ብዙ በርካታ ነገር ተብሏል። እኔ አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። እነሆ!!! መቶ አለቃ ግርማ ጥላሁን ገሠሠ የሞተ ጊዜ ስለ ጥላሁን ተጠይቀው ጥላሁንን ሲያደንቁ እንደሚከተለው ብለው ቀጥፈዋል፣ ነጭ ውሸት ዋሽተዋል። እንዲህ አሉ
” ጥላሁን ኦሮምኛ መዝፈን 
በተከለከለበት በደርግ
እና በንጉሱ ጊዜ በኦሮምኛ
ዘፍኗል

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

አሉ። ጉድ አልን። ራሳችን ይዘን በተነገረው ውሸት አዘንን። ይሄ መቸም አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው። በሬ ወለደ ነው። ባህላችን ሙት ወቃሽ አታድርገኝ ይላል እኔ ግን ይህንን ቅጥፈት ሳላጋልጥ መተው አልፈልግም።ቅጥፈት ቆሻሻ ነገር ነው።

አዘጋጁ – ይህ ጽሁፍ የአቶ ጉዋንጉል ተሻገር ሃሳብ ነው። ማንናውም ዓይነት ስርዓትን የተከተለ አስተያየት ቢላክልን እናትማለን

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0