“Our true nationality is mankind.”H.G.

አስደንጋጩ የብሔራዊ ባንክ ሪፖርት –

በባለፉት ሁለት አስር ዓመታት አማራን በተገኘው ነገር ሁሉ ማዳከም አንዱና ዋናው የሕውሃት ፖሊሲ እንደነበር የአደባባይ ሚስጥር ነው። የብዙ አገር መንግስታት ትላልቅ ፖሊሲወችን ሲያወጡ ብዙ ገንዘብ አውጥተው ጠቃሚነቱን እና ጉዳቱን ያስጠናሉ።

ወያኔ ግን የሚያስጠናው ፖሊሲው ምን ያክል አማራን ይጎዳል? ወይም ያዳክማል? በሚል ነበር። ለዚህም አንድ ማሳያ ሕውሓት ስልጣን ሊወጣ አካባቢ ፖል ሄንዝ (Paul Henze ) ከተባለ የCIA ኤጀንት ጋር በ1990 ያደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ፖል ሄንዝ መለስን ስለመሬት ፖሊሲ ጠይቆት ነበር። መለስም ሲመልስ ፣”አሁን መሬትን በመንግስት ሥር አድርገን ነው መቀጠል የምንፈልግ፣ ምክኛቱም መሬት የግል ከሆነና መሸጥ መለወጥ ከተጀመረ መሬቱን የሚገዙት አማራወች ናቸው፤ ይህ እንዲሆን ደሞ አንፈቅደም” ነበር ያለው።

በዚህም የተነሳ አማራ በሚባለው ክልል በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ፣ በመብራት እና በመሳሰሉት ማንኛውም መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ተደራሽነት ከሁሉም ክልሎች እና አካባቢ በመጨረሻ ደረጃ እንደሚገኝ አለም ባንክ ፣ አልጀዚራ እና የመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም የመሰከሩለት ስለሆነ ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈለግም።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

እነዚህ ለኢንቨስትመንት ፍሰት አመች የሆነ መሰረተ ልማቶች (መብራት፣ ውሃ፣ መንገድ ) ባለመሟላታቸው አማራ አካባቢ መጥቶ መዋለ ንዋይ የሚያፈስ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ባለሀበት የለም። እንዲያውም የአማራው ባለሀብቶች ሳይቀሩ፣ በተንዛዛ ቢሮክራሲና በሌሎችም ክንያቶች ክልሉን ለቀው ይወጣሉ። የዓባይን ልጅ ውሃ ጠማው እንድሚባለው የተገላቢጦሽ ብሂል አማራ ጣና በለስን እና ጭስ አባይ የኃይል ማመንጫ እያሉት፣ ከአገሪቱ ክልሎች ባነሰ የኃይል ስርጭት ያለበት ክልል ነው። አይደለም ፋብሪካ የሚያንቀሳቅስ የኤሌክትሪክ ኃይል ይቀርና፣ የእህል ወፍጮ እንኳን በደንብ አይፈጭም።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ለዚህ መራራ ሀቅ ዋና ምስክር እራሱ የመንግስት ሪፖርት ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣው አመታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ2014/15 በአገሪቱ በአጠቃላይ 4 ቢሊየን ብር በላይ ያስመሰገቡ 407 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተዋል፤ 304 ፕሮጀችት ኦሮሚያ ክልል ቀዳሚነቱን ፣ በ49 ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ትግራይ ክልል በሁለተኛነት፣ አዲስ አበባ ደሞ 31 ፕሮጀክቶች ሶስተኛነት ሲይዝ ሚስኪኑ የአማራ ክልል ግን 4 ፕሮጀችት ብቻ ናቸው ወደ ስራ የገቡት። በእውነቱ ከሆነ ይህን ማመን በጣም ይከብዳል፣ ግን እውነቱ ይህ ነው። ይህን ሪፖርት ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ነው።

በ2015/2016 ብናይ ደሞ ምንም መሻሻል አልታየበትም። በአገሪቱ በአጠቃላይ 7 ቢሊየን ብር አካባቢ ያስመዘገቡ 852 ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተዋል፤ ከነዚህም ውስጥ አዲስ አበባ 755 ፕሮጀክቶች፣ ትግራይ 45 ፕሮጀክቶች ፣ኦሮምያ 26 ፕሮጀክቶች ሲኖሩት የፈረደበት አማራ ክልል ግን 7 ፕሮጀችት ብቻ ናቸው ወደ ስራ የገቡት።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ይህን ለባለፉት ዓመታታ ሆን ተበሎ በተጣናበት መንገድ ህብረተሰቡን አደህይቶና አደንቁሮ የመግዛት ፖሊሲ ሊቆም ይገባል። ስለዚህ የሚመለከታቸው የክልሉ እና የፌደራል መንግስት አካላት አማራን ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረገ መረባረብ አለባቸው። በተለይ አዲሱ አዴፓ አመራሮች ከፌዴራል መንግስት ለባለፉት ሁለት አስር አመታት ክልሉ በመንገድ፣ መብራት እና በመሳሰሉት መሰረተ ልማቶች ወደሗላ ስለቀረ ፣ተጨማሪ የበጀት ድጎማ ያስፈልገዋል። አማራ ክልል በመሰረተ ልማቶች እንደ ትግራይ እና ኦሮምያ ለመሆነ ተጨማሪ ድጎማ ያስፈለገዋል፣ እንደዛም ሁኖ ብዙ ዓማታት ይፈጃል የሚል ግምት ነው ያለው።

ሙሉቀን ተስፋው

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0