በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ችግር የተጠረጠሩ 171 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ። በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ገንዘብም በቁጥጥር ሥር እንዲውል መደረጉ ተመልክቷል፡፡

የአካባቢውን ሠላም ለመመለስ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አባልና በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምዕራብ ዕዝ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ እንደገለጹት፥ ኮማንድ ፖስቱ ታህሳስ 11 2011 ዓ.ም ከተቋቋመበት ጊዜ አንሰቶ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየሰራ ነው።

በእዚህም በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች በታጠቀ ኃይል ተፈጥሮ በነበረ የፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ በጠፋው የሰው ህይወትና በወደመው ንብረት የተጠረጠሩ 171 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስረድተዋል።

Related stories   ክቡር ገና በመጪው ምርጫ ኢዜማን ወክለው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ለመወዳደር በዕጩነት ቀረቡ

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ግጭት ከተከሰተባቸው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ካማሽ ዞን እና ቶንጎ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ደግሞ ምዕራብ፣ ምስራቅና ቄለም ወለጋ፣ ሆሩ ጉድሩ፣ ኢሉ አባቦራ እና ቡኖ በደሌ ዞኖች መሆኑንም ተናግረዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እንደሚገኙበት ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

የታጠቀው ኃይል ለግድያ እና ሌሎች ጥፋቶች ሲጠቀምባቸው የነበሩ 49 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎችና 1 ሺህ 31 የተለያዩ ጥይቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኮሎኔል ጌትነት ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Related stories   ከንቲባ አዳነች የአዲስ አበባን ጉድ ለሚመሩት ሕዝብ ይፋ አደረጉ፤ ሪፖርቱን በርካቶች ከሳቸው ሲጠብቁት ነበር

ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቦቹ በህገ-ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቀሱት የነበረ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር እና 12 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ኮማንድ ፖስቱ መያዙን ነው ያስረዱት።

እንደ ኮሎኔል ጌትነት ገለጻ፥ የጥፋት ኃይሎቹ ተጨማሪ ጥቃት ለመፈጸም ያዘጋጁት ሰባት ጸረ-ተሸከርካሪ ፈንጂዎች፣ 215 ቀስቶች እና የተለያዩ ኮምፒዩተሮችም ተይዘዋል።

ታጣቂ ኃይሉ ከመንግስት መዋቅሮች እና ከግለሰቦች አስገድዶ በመውሰድ ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበሩ 9 አምቡላንሶች፣ 4 አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ 3 ቶዮታ ፒክአፕ መኪኖችም ኮማንድ ፖስቱ ማስመለሱን ነው የገለጹት።

Related stories   ልዩ ዜና – በትግራይ ሰላም አስከባሪ ለማስገባት የተያዘው ዕቅድ ሳይሳካ ቀረ፤ ስዬ ጦርነቱ አላለቀም አሉ

ቡድኑ ለጥፋት ሲጠቀምባቸው የነበረውን ንብረት ከማስመለስ ጎን ለጎን በጉዳዩ ላይ ሕብረተሰቡን የማወያየት ሥራ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ኮሎኔል ጌትነት አስረድተዋል፡፡

የጸጥታ ችግር ሲከሰትባቸው በነበረባቸው ዞኖች በአሁኑ ወቅት ግጭት ሙሉ ለሙሉ ቆሞ ወደ ሠላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን ጠቅሰዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *