የኢፌዲሪ አየር ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ የሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የኢፌዲሪ አየር ሃይል ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች በፈፀሙት ለ44 ደቂቃ የዘለቀ ድብደባ 35 የአልሻባብ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል፡፡
ከዚህ ውስጥም በስፍራው የአልሸባብ የኦፕሬሽን ሃላፊና የፈንጂ ቡድን ሃላፊው በድብደባው መገደላቸው ተረጋግጧል ነው ያለው፡፡
Related stories ልዩ ዜና – በትግራይ ሰላም አስከባሪ ለማስገባት የተያዘው ዕቅድ ሳይሳካ ቀረ፤ ስዬ ጦርነቱ አላለቀም አሉ
Powered by Inline Related Posts
በዚህ የአየር ድብደባ ሁለት የቴክኒክ፣ አንድ የጭነት፣ አንድ ፈንጂ የጫነ በድምሩ አራት ተሽከርካሪዎች እንዲሁም አምስት ካሊበር መሳሪያዎች ወድመዋል፡፡
ከዚህ በፊትም የመከላከያ ሠራዊቱ በአልሸባብ ልዩ ልዩ ይዞታዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ የሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዳደረሰበት መግለጫው አስታውሷል፡፡
ዘገባው የፋና ነው