“Our true nationality is mankind.”H.G.

ሳዑዲ ከተዘረፈችው ሃብት ከመቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ አስመለሰች – ስንት ቀራቸው?

ሳዑዲ በሌብነት ያሰረቻቸው ባለስልጣናትና ” ባለሃብቶች” 70 በመቶ የሚሆነውን ሃብታቸውን አሳልፈው በመስጠት ከእስር ለመፈታት እየተደራደሩ መሆናቸውን ፋይናንሺያል ታይምስ ዜናው ትኩስ በነበረበት ወቅት ዘግቦ ነበር። ዜናው በሳዑዲ ባለስልጣኖች በይፋ ማረጋገጫም ይሁን ማስተባበያ ባይቀርብበትም ትናንት የተሰማው ዜና አገሪቱ በሙስና ከተዘረፈችው ሃብት ውስጥ ከአንድ መቶ ቢልዮን ዶላር በላይ አስመልሳለች።

የአገሪቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ከ2017 ጀምሮ በተካሄደው የጸረ ሙስና ዘመቻ ነው የተጠቀሰውን ከፍተኛ ሃብት ማስመለስ የተቻለው። ክብራቸውን ከሚነካ የመኝታ ሁኔታ እስከ ስቅየት (ቶርቸር) ደርሶባቸዋል ሲባልላቸው የነበሩት ታሳሪዎችን ንብረት መንግሥት እንዲቆጣጠረው እንደሚደረግ የሳዑዲው አቃቤ ሕግ ተናግሮም ነበር።

በድርድርም ሆነ በውርስ መሃመድ ቢን ሳልማን ስልሳ ደቂቃ በፈጀው ቃለ ምልልሳቸው አገሪቱ ከተዘረፈችው ሃብት ውስጥ የተጠቀሰው ገንዘብ መመለሱን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ እንዴትና እነማን ምን ያህል እንደከፈሉ ጥርት አድርገው አላብራሩም።

ሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲንን ጨምሮ ሳዑዲ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ባለስልጣናትና ቱጃሮች ጉዳዩ ከጀርባው ፖለቲካ እንዳለበት ቢታመንም በዋናነት የመንግሥትን ሃብት አለአግባብ በመጠቀም በሚል በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የሳውዲ ልዑላንና ሌሎች ታላላቅ ባለሥልጣናት ከእስር ለመውጣት እስከ 70 በመቶ ሃብታቸውን ለመንግሥት ለማስረከብ መደራደራቸው እውነት ነው። ፋይናንሺያል ታይም በአፍላው የዘገበው ዘገባ ዛሬ ላይ በተዘዋዋሪ መንገድ ተረጋግጧል።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

አላሙዲ አልታሰሩም በሚል ደረቅ ክርክር ሲያሰራጩ የነበሩ፣ መለስ ብለው ደግሞ ተፈቱ፣ ዛሬ አገር ቤት ይገባሉ ሲሉ የነበሩ፣ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና ወዳጅ ባለስልጣናት ብዙ ቢሉም ሳዑዲ ጉዳይዋን ጨርሳ ከዓመት በላይ እስር በሁዋላ መፈታታቸውን ይፋ አድርጋለች።

ሰባ ሺህ የሚጠጉ ሰራተኞች በድርጅቶቻቸው ስር ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን ዋልታ እንደዘገበው መቻሬ ሜዳ መፈታታቸውን ተከትሎ ሰራተኞች እስክስታ ሲወርዱ ታይቷል። ለአራተኛ ጊዜ የተሞሸሩት የሚድሮክ ስራ አስፈጻሚም ቀኑንን ቆርጦ መናገር ባይቻልም በቅርቡ ወደ አገር ቤት እንደሚመጡ ደስታቸውን ሲገልጹ አክለው አስታውቀዋል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀመንበር አብነት ገብረመስቀል ግን በይፋዊ ሚዲያ እስካሁን ምን እንዳሉ አልተሰማም።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

እንዳንድ መርጃዎች አላሙዲ ክፈሉ የተባሉትን ሰባ ከመቶ ባለመክፈላቸው እስካሁን እስር ላይ እንደቆዩ ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ በስተመጨረሻ በድርድር የተጠቀሰውን ከፍለው እንደወጡ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንዳስፈቷቸው በኦፊሳል ቢገለጽም፣ የአቶ በረከት እስር ቤት መግባትና የሳቸው መፈታት አካሄዱ የተጠና እንደሚመስል አመላካች ነው ባይ ናቸው።

ከለውጡና ከለውጡ መሪ አብይ አህመድ ጎን ሃያላኑና የሃያላኑ የቁጥጥር መረብ አብሯቸው በመሆኑ አካሄዱ ብዙም እንደማይገርም የሚገልጹ ክፍሎች የአላሙዲ ስም በአፍሪካ ምርጥ ሃብታሞች ዝርዝር ውስጥ አለመታየቱን የዚሁ አስተያየት ማጠናከሪያ አድርገው ይወስዱታል። ግን ጉዳዩ ውሎ አድሮ ይፋ የሚሆን መሆኑ የአስተያየት ሰጪዎቹ እምነት ነው።

ሳዑዲ በሙስና ተግባር ውስጥ ተሳትፈው በተገኙ ባለሃብቶችና ነጋዴዎች ላይ ክስ መመስረቱን ገልጻለች። ላለፉት ሁለት ዓመታት ሌብነትን ለመዋጋት ያደረገችው ዘመቻ እጅግ የተሳካ መሆኑንም ተናግራለች። ላለፉት ሁለት ዓመታት የተከናወነው  የፀረ ሙስና   ዘመቻ መጠናቀቁን ይፋ አድርጋለች።

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

የፀረ ሙስና ዘመቻ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ከ200 በላይ የልዑላን ቤተሰብ ባለሃብቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ታዋቂ ከበርቴዎችና ነጋዴዎች ሪያድ በሚገኘው ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ታስረው እንደነበር ይታወሳል።

ከየመን አባት የሚወለዱት አላሙዲ ገና እግራቸው ወደ አገር ቤት ሳያቀና የህግ ተጠያቂነት ጉዳይ እየተነሳባቸው ነው። ጃዋር መሐመድ የሚመራዊ ሚዲያም በስፋት እሳቸውን በወንጀል የሚያስጠይቅ ዘገባ እያደራረበ በማቅረብ ላይ ይገኛል።

መንግስት አላሙዲን አጥረው የያዙትን መሬት ወርሷል። በጅማ ሆራይዞን የቡና እርሻ የእሳቸው ነው ቢባልም ባለቤቱ ማን እንደሚሆን የሚገልጽ ሰነድ አልተገኘም። በተላያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ሰፋፊ ልማት ላይ ሳይውሉ የቆዩ መሬቶች፣ እንዲሁም መንግስት ዋስትና ሰጥቷቸው ባለሃብቱ የወሰዷቸው ዓለም አቀፍ ብድሮች፣ የአገር ውስጥ የግብርና የቀረጥ ጉዳይ እና አንዳንድ ፈራቸውን ለቀው የነበሩ አሰራሮችን አስመልክቶ የዶክተር አብይ መንግስት የሚወስደው ርምጃና ማስተካከያ አድሮ የሚታወቅ ይሆናል።

አላሙዲ ስንት ከፍለው ስንት ቀርቷቸው ይሆን ?

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0