“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከኳታርና መልስ ሱዳን ድንበሯን ለኤርትራ ክፍት አደረገች ፤ ” ኤርትራውያን ወንድሞቻችን እና ህዝባችን ናቸው፤ ፖለቲካ አይከፋፍለንም” በሽር

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ሀገራቸውን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር መከፈቱን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በዛሬው እለት እንዳስታወቁት፥ ሀገራቸው ለ1 ዓመት ዝግ አድርጋ የቆየችውን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ተከፍቷል።ሱዳን ከኤርትራ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ባሳለፍነው ዓመት ጥር ወር ገደማ መዝጋቷ ይታወሳል።

ሀገሪቱ ከኤርትራ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር የዘጋጅውም ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር በካሳላ እና በሰሜን ኩርዱፋን ክልሎች ለ6 ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን ተከትሎ ነበር።

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

በዛሬው እለት ደግሞ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በካሳላ ክልል ተገኝተው በቴሌቪዥን ባስተላለፉት ምልዕክት ነው የድንበሩን ዳግም መከፈት ያበሰሩት።

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው፥ “ከዛሬ ጀምሮ ከኤርትራ ጋር የሚያዋስነን ድንበር ተከፍቷል፤ ምክንያቱም ኤርትራውያን ወንድሞቻችን እና ህዝባችን ናቸው፤ ፖለቲካ አይከፋፍለንም” ብለዋል። ሲል ፋና ሮይተርስን ጠቅሶ ዘግቧል።

በሽር የተነሳባቸውን ቁጣ ለማባረድ ወደ ኳታርና ግብጽ አቅንተው እንደነበር ይታወሳል። ከጉዟቸው እንደተመለሱ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ለበርካቶች ስሜት የሚኮረኩር ሆኗል።

0Shares
0