“Our true nationality is mankind.”H.G.

” መሽጎ ብርድ ብርድ ሲለው የሶማሊ ክልልን ይዞ ሊገነጠል ያሰበ…” አቶ ሙስጣፋ ህወሃትን ጎሸሙ

“እኛ” አሉ አቶ ሙስጣፋ አስረግጠው በሚታይ ንፅፅር ሲያስረዱ ” የመከላከያ ሰራዊትን እንቅስቃሴ አልገታንም፣ ፓርላማና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚያወጣውን ህግ አይመለከተንም አላልንም፣ በህግ የፌደራል መንግስት የሚፈልጋቸውን ወንጀለኞች አናስረክብም ብለን አልመሸግንም…” የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አጠንክረው ” መሽገው ብርድ በርድ ሲላቸው ሶማሌን ይዘው ለመሄድ ይመኛሉ” ሲሉ ብትራቸውን በቀጥታ ህወሃት ላይ አሳረፉ። ማንም ባላደረገው መልኩ ህወሃትን ከገደምዳሜ ንግግር አልፈው በግልጽ ” ለመገንጠል ያሰቡ፣ ብርድ ብርድ ያላቸው ” ሲሉ አናናቁ።

የሶማሌ ክልል ህዝብ በራስ መተማመኑንን እንዲያሳድግ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ተከትሎ ክልሉ ለአክራሪዎች ተላልፎ እንደተሰጠ፣ ክልሉ ሊገነጠል እንደሆነ ተደርጎ በስፋት የሚነዛውን ቅስቀሳ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አቶ ሙስጣፋ ፣ቀሳውስትን ያረዱ፣ ህዝብን የፈጁ፣ አምልኮ ቤቶችን ያነደዱና ይህንን ያደራጁ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ተደርገው እንዲሳሉ መታሰቡን ተራ አድርገው አቅርበውታል። ይልቁኑም ይህንን ሁሉ በመቀልበስ ህዝብ አብሮ የፈለገውን እምነት እያራመደ እንዲኖር ማደረጉ፣ ህዝብ ከስጋት መላቀቁ ከአሉባልታው በላይ እንደሚያኮራቸው አመልክተዋል።

” ጸረ ለውጥ ሃይሎች” ሲሉ ህወሃትን ከላይ በማስቀመጥ መግለጫቸውን የሰጡት አቶ ሙስጣፋ ከሰላሳ ጊዜ በላይ የብሄር ግጭት እንዲነሳ ከፈተኛ ዘመቻ መካሄዱንና ይህ ሁሉ ሙከራ እንደከሸፈ አስረድተዋል። “የሃምሌ ሃያ ስምንቱ አይነት እልቂት ሊደገምባችሁ ነው” በሚል ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማባለት፣ ጅግጅጋና ድሬደዋ  የሶማሌ ብቻ ናቸው በማለት ተመሳሳይ ግጭት እንዲነሳ ከፍተኛ ዘመቻ ሲካሄደ እንደነበርም አውስተዋል። ይሁን እንጂ የታሰበወ አልሆነም። ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና የሃይማኖት አባቶች በህበረት ሆነው ከአስተዳደራቸው ጋር በመስራት አምክነውታል።

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

” ኢትዮጵያን ሲገጡ የነበሩ” ሲሉ የሚጠሩዋቸው ክፍሎች የክልሉ ልዩ ሃይል የመከላከያ ሰራዊትን እንደ ጠላት እንዲያ አድርገውት እንደነበር አቶ ሙስጣፋ በመግለጫቸው አውስተዋል። ዛሬ ግን ልይቱ ሃይል፣ የፌደራል ፖሊስ፣ መከላከያ ሃይል ሁሉም አንድ ዓላማ ያላቸውና ኢትዮጵያን የሚያገለግሉ መሆናቸውን አምነው እንደ ወንድማማች አብረው እየሰሩ መሆኑንን ገልጸዋል። ይህንንም እንደ አንድ ትልቅ ስኬት መክር ቤታቸው አድንቆ እንድተቀበለው ተናግረዋል።

የሶማሌ ህዝብ ከሁለት ሺህ በላይ የኢትዮጵያን ድንበር ሲጠብቅ የኖረ መሆኑንን ያመለከቱ አቶ ሙስጣፋ “ዛሬም ሆነ ነገ የምናደርገው ይህንኑ ነው” ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ግተናገረዋል። የስድሰት ወር የምክር  ቤት ሪፖርት አስመልክቶ መግለጫ የሰ|ጡት ፕሬዚዳንቱ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ሃይል ትጥቁን ፈቶ ሙሉ በሙሉ እጁን ለመንግስት መስጠቱን በኩራት አብስረዋል። አንድ ሺህ ሰባት መቶ አርባ ታጣቂዎች ትጥቅ አውርደው መንግስት እጅ ገብተዋል።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ይህ ለዓመታት የትጥቅ ትግል ሲያካሄድ የነበረ ድርጅት መተማመን ተፈጥሮ ወደ ሰላሙ መንገድ እንዲገባ እጅግ አድካሚና እልህ አስጨራሽ ስራ መሰራቱን አቶ ሙስጣፋ አልሸሸጉም። አሁን ለአተራማሽና ለጸረ ለውጥ ሃይሎች መንገድ እላመኖሩን አመልክተዋል። በቀጣይ በሞያሌና በቱሉ ጉሌድ ተከስቶ የነበረው ግጭት የጣለውን ጠባሳ ለማሰወገድ ከኦሮሚያ ክልል ጋርበስፋት እየተሰራ መሆኑንን እና ይህ አብሮ ለዘመናት የኖረ ህዝብ ተመልሶ ወደ ግጭት እንዳይገባ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ይፋ አድርገዋል።

ፈርሰው የነበሩት የቀበሌና የወረዳ እንዲሁም የዞን መዋቅሮች በተማሩ የክልሉ ነዋሪዎች ሁሉን ባሳተፈ መልኩ በአምስት ወር ውስጥ ዳግም መዋቀሩንና ህዝብ ደስተኛ መሆኑ አቶ ሙስጣፋ አስታውቀዋል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳሻው አስተያየት የመስጠት እድል ያገኘው የክልሉ ምክር ቤትም ይህንኑ ተግባር በግልጽ ማድነቁን አለመልክተዋል።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

የሶማሌ ህዝብ ውስጣዊ አንድነቱን አብልጦ በመግንባት፣ ከአጎራባች ክልሎች ጋር መልካም ወዳጅነት በማጠናከር ኢትዮጵያ በሰላም ወደ ልማት እንድትሸጋገር አስፈላጊወ ሁሉ እነሚደረግ በማጠቃለያቸው ተናገረዋል። አቶ ሙስጣፋ ክልላቸው ከማይደራደርባቸው ጉዳዮች አንዱ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት መሆኑንን ወደ ሃላፊነት እንደመጡ መናገራቸው ይታወሳል።

በስማሌ ክልል የጄል ኦጋዴንን የዘጉት አቶ ሙስጣፋን ከአብዲ ኢሌ በማሳነስ ” ፍትህ ለአብዲ” በሚል ዘመቻ የሚያካሂዱትን ” ህወሃት” ሲሉ ባይጠሩም ” አገሪቱን ሲግጡ የኖሩ፣ መሽገው ብርድ ብርድ ያላቸው” ሲሉ የህወሃትንና የስማሌ ክልል ፓርቲ ፍቺ አደባባይ አውጥተውታል። ዶክተር አብይ በሶማሊ ክልል የተሰራው ጥበብ የተሞላበት ተግባር ወደ ሃላፊነት ከመጣን ጀመሮ የተሰራ ታላቅ ጉዳይ እንደሆነ መናገራቸው አይዘነጋም።

አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ግለሰቦችና ሰባት ኩባንያዎች በህግ እየተጠየቁ ሲሆን ፣ የስላሳ ተጠርጣሪዎች የባንክ አካውንት መታገዱን እንዲሆም የክልሉ ምክር ቤት የበርካታ ተጠርጣሪዎችን ያለመከሰስ መብት ያነሳ መሆኑና አገር ውስጥ ያሉ በቁትትር ስር መዋላቸው የክልሉ መገናኛ በተመሳሳይ ቀን ይፋ አድርጓል።

 

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0