“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ወይስ አትላንቲክ ውቅያኖስ ? “Aethiopia Ocean ” ስማችን ይመለስ

አትላንቲክ ውቅያኖስ ..በጥንት ዘመን. የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይባል ነበር ። “ኢትዮጵያ” ማለት ለእግዚአብሄር የሚሰጥ ቢጫ ወርቅ ማለት ነው፡፡ ይህ ስም የተሰጠው ለኢትዮጵያ መስራችና የኢትዮጵያውያን አባት ለሆነው ለ ኢትዮጵ ነው፡፡ እንግዲህ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ወርዶ፣ ወርዶ ወደ እኛ የደረሰው ከሱ ስም ነው ማለት ነው፡፡

:

✦ “ኢትዮጵያዊ” ማለት በግሪክ ቋንቋ የተቃጠለ ፊት ነው የተባለው የነጭ ውሸት ነው። በግሪክ መዝገበ ቃላት ውስጥ እንደዚህ የሚል ቃል ፈፅሞ የለም። ደሞም የኛ ፊት የተዋበ እንጂ የተቃጠለ አይደለም።

የዛሬን አያድርገውና የአባታችንን የኢትዮጵን ስም የተሸከመችው ኢትዮጵያ በመላው ዐለም ገናና ነበረች።

:

✦ ከጥንት ጀምሮ ከአባታችን ከኢትዮጵ በኋላ የተክተሉት ነገሥታት ልጆቹ የኢትዮጵያን ስልጣኔ በመላው አፍሪካ አስራጭተው ዛሬ አፍሪካ የሚባለው ሰፊ ምድር እስክ ዛሬ ሁለት መቶ ዐመታትት ድረስ ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራ ነበር።

:

✦ LOWER እና UPPER ETHIOPIA ብለው ከፍለውት ነበር። ከእዚህም በላይ የህንድ ውቅያኖስ እና ከ ምእራብ አፍሪካ ብብት ስር ያሉት ውቅያኖሶች ሁሉ የኢትዮጵያ ውቅያኖሶች በላቲን Mar di Aethiopia በእንግሊዝኛ ደግሞ Ethiopian Ocean ተብሎ ይጠራ ነበር።

:

✦ አውሮፓውያን በሳሉት በዚህ ካርታ ላይ በደቡብ አሜሪካና በ ምእራብ አፍሪካ መሀል ያለው ውቅያኖስ ላይ በላቲን Oceanus Aethiopicus እንዲሁም የአፍሪካ ደቡባዊ ክፍል ጨምሮ የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይላል። ዛሬ Indian Ocean የህንድ ውቅያኖስ የተባለውም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ Ethiopian Ocean ይባል ነበር።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

:

✦ ከላይ የምናየው ምስል በእንግሊዝኛ የተጻፈው ማቲው ካሪ Mathew Carey የተባለ ባለሞያ እኤአ በ 1795 የሳለው ካርታ ነው.። ቅዱስ ስሟን ለመፋቅ ወይም ለመቀየር የተመኙ ሁሉ የኢትዮጵያ ስም ከእግዚአብሄር ጋራ የተያያዘ በመሆኑ ምኞታቸው ከሽፎ ቀርቷል። ኢትዮጵያን ሊያገንን የተነሳ ሁሉ ይገንናል። ኢትዮጵያን የሚያከብር ሁሉ ይክብራል።

:

✦ኢትዮጵያን ያኮሰሰ ሁሉ ይኮስሳል። ኢትዮጵያን ያንቋሸሸ ሁሉ ይንቋሸሻል። የእግዚአብሄር ዐይኖች ኢትዮጵያ ላይ ተተክለዋል። በቅዱስ መፅሃፉ ውስጥ እግዚእብሄር ኢትዮጵያን ደጋግሞ የሚጠራት ያለ ምክንያት አይደለም። ከማንም ይልቅ ኢትዮጵያን ስለሚወዳት ነው።

:

✦ ክ 200 ዐመታት በፊት መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ይባል ነበር። የእዚህ ምክንያቱ የኢትዮጵ ተወላጆች በመላው አፍሪካ ተሰራጭተው፣ አፍሪካን አሰልጥነው ስለኖሩበት ነው። የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን በቅኝ መግዛት ከጀመሩ ወዲህ ግን ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ቀርቶ ድሮ በንግድና የመርከብ ግንባታ በታወቁ ኢትዮጵያውያን አህጉሩ አፍሪስካውያን በተባሉት አፋሮች አፍሪካ መባል ጀመረ በእዚህም እንኮራለን።

:

✦ Mapping Africa Problems of Regional Definition and Colonial/National Boundaries by Ralph A. Austen በተሰኝው መፃህፍም ኢትዮጵያያን አፍሪካን እንደ ሰየሞዋት እና አትላንቲክ ውቅያኖስ እና ህንድ ውቅያኖስ ..በጥንት ዘመን. የኢትዮጵያ ውቅያኖስ ይባል እንደ ነበር ። እንዲህ በማለት ያብራራሉ” I’ve also learned that the old name of the south Atlantic Ocean was “The Ethiopian Ocean”.

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

:

✦ ሄካታዮስ ዘሚሌቶስ (500 ዓ.ዓ.) ደግሞ ስለ አይቲዮፒያ አንድ መጽሐፍ እንደ ጻፈ ይነገራል፤ አሁን ግን ጽሁፉ በአንዳንድ ጥቅሶች ብቻ ይታወቃል። አይቲዮፒያ ከአባይ ወንዝ ወደ ምሥራቅ እስከ ቀይ ባሕርና እስከ የዛሬው ሕንድ ውቅያኖስ( የኢትዮጵያ ውቅያኖስ) ያጠቃልል ነበር ይለናል።

:

✦✦✦ይህችን ሀገር ነው እንግዲህ ተራ የምንላት። ደግሞ የሚገርመኝ ሀገሪቱን የሚያቃልሏትና የሚያዋርዷት የራሷ ልጆች መሆናቸው ነው። ነጮቹማ ምን ያህል ምስጢራዊ ምድር እንደሆነች ስላወቁ ነው ከጥንት ጀምረው በዐይነ ቁራኛ የሚከታተሏት። ግን እስከ መቸ የኛ ሊቃውንት(የታሪክ ተመራማሪዎች) ንግስተ ሳባ የሰለሞን ጥበብ ለማየት ወደ እየሩሳሌም ሄደች ስንል ተረት ተረት ይመስለናል

:

✦✦ ፈረንጅ ደግሞ ሮምን የመሰረቷት ሮሙለስና ሙለስ የተባሉ ተኩላ ያሳደጋቸው ልጆች ናቸው ሲሉን አምነን እንቀበላለን። የኛ የታሪክ ተመራማሪዎች እኮ ስለ እያንዳንዱ ነገር ማስረጃ አላቸው እኛ ግን ትክክል እንዳልሆኑ ማስረጃ የለንም። ስለዚህም እባካችሁ ወደ ራሳችን ማንነት እንመለስ ። ፈረንጅ አምላኪ አንሁን።

:

✦ #ኢትኤልን ከጥንት ጀምሮ በምቀኝነትም ተነስተው ብዙ ጊዜ ፈትነዋታል አልሸነፍ ስትላቸው አሁን ደግሞ አባቶቻችን አጥንታቸው ከስክሰው ያቆዩልንን ሀገር በእጅ አዙር(በዘመናዊ ባርነት) ሊያምበረኩኩን የሚጥሩት። ነገር ግን ኢትዮጵያዬ እንደ ስሟ ወርቅ ናትና በእሳት ተፈትና አልፋለች፣ታልፋለችም አከተመ!!!።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

:

✦ የዛሬው የህንድ ውቅያኖስ በቀደመ ስሙ “የኢትዮጵያ ውቅያኖስ” ተብሎ ይጠራ ዘንድ የመንግስት አካላት ትኩረት እንዲሰጡት እንዲሁም ሁሉም ኢትያጵያዊ ይህን እውነት እንዲያውቅ #share_ሼር_share በማድረግ የቀደመችውን ኢትኤልን እንገንባ።ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሼር-share ሳያደርግ እንዳያልፍ። ይህን ስል ግን የጣና ጉዳይ እንዳይረሳ ይሰመርበት !!!

♡┈┈┈• ~~¦~~ •┈┈┈♡

●《 #ምንጭ…..》

፩) “የኦሮሞ እና የአማራ የዘር ምንጭ”መፃህፍትን በፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ

፪) የታሪክ ሊቁን ተክለ ፃድቅ መኩሪያ መፃህፍትን መመልከት ይቻላል

#ከውጭ ሀገራት

፩) https://en.m.wikipedia.org › wiki › Aethi…

፪) Aethiopian Sea – Wikipedia ,https://noonebu com/ancient-ethiopia-or-aethiopia-and-negroland-nigritia/

፫) https://en.m.wikipedia.org/wiki/Aethiopian_Sea

፬) The Naval Chronicle: Volume 14, July-December 1805: …

፭) Mapping Africa: Problems of Regional Definition and Colonial/National Boundaries by Ralph A. Au

፮) The Rediscovery of Africa, 1400-1900: Antique Maps & Illustrations William R. Jacobson

፯) https://www.bbc.co.uk/news/world-1267546 Rediscovering African Geographies.

✦ ለበለጠ መረጃ ከላይ የጠቀስ፟ኋቸውን የአማረኛ መፃህፍት መመልከት ይቻላል።

#ፔጁን(ኢትኤል) ከወደዱት ሌሎች አስደናቂ መረጃዎች እንዲደርሰዎ ሼር ፣፣፣፣፣ላይክ እንዲሁም ጓደኛዎን invit በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ!

#ጥንታዊነት_የዘመኑ_ፋሽን

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0