“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ዐብይ ከኢሳያስ ጋር ህውሃትን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ቢያሴርብን፤ … ትክክል አይሆንም ምክንያቱም አይሳካለትም”

 አንዳንድ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። ቅር ስለተሰኙ የህውሃት፣ ኦዲፒ ወይም አዴፓ አካላት ሁሉ መናገር ባልችልም። እኔ ግን ከዐብይ ጋር ችግር የለብኝም። አንተ እንዳልከው ግን ዐብይ ከኢሳያስ ጋር ህውሃትን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ቢያሴርብን፤ ከወሰናቸው ውሳኔዎች መካከል ትክክል አይሆንም ምክንያቱም አይሳካለትም።

BBC – በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና በህውሃት ተሳትፎ ዙሪያ የቢቢሲው ጋዜጠኛ አለን ካሱጃ መቀሌ ተጉዞ አቶ ጌታቸው ረዳን አነጋግሯል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከአለን ጋር በነበራቸው ቆይታ በህውሃት እና በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም ጠቅላይ ሚንስትሩ ዙሪያ የአቶ ጌታቸው የግል አመለካከት ምን እንደሆነ ጠይቋል።

አለን ስለ ስለ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ምን ያስባሉ ሲል ነበር ለአቶ ጌታቸው የመጀመሪያውን ጥያቄ የሰነዘረው።

አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ ተነሳሽነቱን እና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያለውን ድፍረት አደንቃለሁ።

አለን፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣሁ ወዲህ ከሰማኋቸው ነገሮች መካከል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ጋር እርቅ ያወረዱት የህውሃት ሰዎች [እናንተ] ችግር እንዳትሆኑበት በማሰብ ነው የሚሉ አሉ . . .

አቶ ጌታቸው፡ እኛ ችግር ሆነንበት አናውቅም

ብዙ ለማሳካት የሚጥር ሰው ነው። የህዝቡን ዋነኛ ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ሁሉን ለማሳካት ጥረት ሲያደርግ ያለውን ሁሉ ሊያጣ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ።

አለን፡ እውነቱን ንገረኛ

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

አቶ ጌታቸው፡ እውነቱን እየተናገርኩ ነው።

አለን፡ የህውሃት መስራቾች ሁሌም ችግር ሆነውበታል [ጠ/ሚ ዐብይ ላይ]።

አቶ ጌታቸው፡ አንዳንድ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። ቅር ስለተሰኙ የህውሃት፣ ኦዲፒ ወይም አዴፓ አካላት ሁሉ መናገር ባልችልም። እኔ ግን ከዐብይ ጋር ችግር የለብኝም። አንተ እንዳልከው ግን ዐብይ ከኢሳያስ ጋር ህውሃትን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ቢያሴርብን፤ ከወሰናቸው ውሳኔዎች መካከል ትክክል አይሆንም ምክንያቱም አይሳካለትም።

አለን፡ በትክክል አድርጓል እያልኩ አይደለም። ምናልባት ሰዎች የሚሉትን አንተም ሰምተኽዋል ብዬ አስባለሁ።

አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ ይህን አይነት እርምጃ ይወስዳል ብዬ አላስብም።

ዐብይ ከኢሳያስ ጋር ህውሃትን ከጨዋታ ውጪ ለማድረግ ቢያሴርብን፤ ከወሰናቸው ውሳኔዎች መካከል ትክክል አይሆንም ምክንያቱም አይሳካለትም።

አለን፡ ይህን ያልከው በጣም በተቆጣ ፊት ነው።

አቶ ጌታቸው፡ አዎ በትክክል። ዐብይ በአጋር ፓርቲው ላይ እንዲያሴር ምንም አይነት ምክንያት አይታየኝም።

አለን፡ እንደዚያ ቢያደርግ ትታገላለህ?

አቶ ጌታቸው፡ ማድረግ ካለብኝ አዎ።

አለን፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ለየትኛዎቹ ጉዳዮች ምላሽ መስጠት አለበት ብለህ ታስባለህ?

አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር መሆን ይኖርበታል።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

አለን፡ እየሆነ አይደለም?

አቶ ጌታቸው፡ እኔ ከምጠብቀው በታቸው ቢሆንም ለመሆን እየሞከረ ነው።

አለን፡ ምን እያደረገ አይደለም?

አቶ ጌታቸው፡ የህዝቡን ፍላጎት መመልከት ይኖርበታል። የትግራይ ህዝብን ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብንም ጭምር።

አለን፡ ለምሳሌ የትኛውን?

አቶ ጌታቸው፡ ዐብይ ወደ ስልጣን የመጣው ወጣቱ ሥራ አጥነት ስላማረረው ነው። ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ የነበረች ቢሆንም በርካቶች ሥራ አጥ ነበሩ። አሁንም ቢሆን የዐብይ ትልቁ ኃላፊነት ለወጣቱ ምላሽ መስጠት ነው። በቃል ብቻ ተስፋ መስጠት ለችግሩ መፍትሄ ሊሆን አይችልም።

አለን፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩት መንግሥታት ይልቅ አሁን በኢትዮጵያ የተሻለ ነጻነት አለ ብለህ ታስባለህ?

አቶ ጌታቸው፡ አዎ አለ። አሁን ላይ በርካቶች አደባባይ እየወጡ ድምጻቸውን ያስማሉ። ይህ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት የሚቻል አልነበረም። ዋናው ነገር ግን በሁላችንም መካከል የሞራል ልዕልና ተፈጥሮ ሁሉም ለበለጸገች እና ለተረጋጋች ኢትዮጵያ ልንሰራ ይገባል።

አለን፡ ከአናተ ጋር በነበረኝ ቆይታ የተረዳሁት ዐብይ ብዙ የተባለለት ሰው አድርገኽዋል?

በዐብይ ህልም እና ተነሳሽነት ችግራችንን በአንድ ላይ ልናልፍ እንደምንችል ይሰማኛል። ይሁን እንጂ እንደምናስበው ሁሌም መልካም ሃሳቦች ወደ ፈቀድነው ላያመሩን ይችላሉ፤ እንደሚባለው የቁልቁለት ጉዞ ምንም ጊዜም የሚጀመረው በበጎ ሃሳብ ነው።

አቶ ጌታቸው፡ ስለ እሱ ብዙ ነገር ልልህ እችላለሁ። ዐብይ እራሱ የሚያውቀው ይመስለኛል። ዓለም አቀፉ ማህብረሰብ በተለይም ደግሞ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እጅግ አሳሳች ተቋሞች ናቸው። እጅጉን ጎበዝ የሆንክ መሪ አድረገው ይነግሩሃል።

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

ጥሩ መሪ መሆንህን ማወቅ ያለብህ ግን ከህዝብ ጋር – ከወጣቱ ጋር – ጥሩ ግንኙነት ሲኖርህ ነው። እነሱ ናቸው ችግር ሊያስከትሉብህ የሚችሉት። አልጀዚራ፣ ቢቢሲ ወይም ሲኤንኤን ምንም ያክል ቢያወድሱህ ለዜጎች የሥራ እድል ትፈጥራለህ ማለት አይደለም። ዐብይ ለወጣቱ ሥራ መስጠት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እፈልጋለሁ።

አልን፡ ዐብይ አህመድ ምን አይነት ሰው ነው?

አቶ ጌታቸው፡ ብዙ ለማሳካት የሚጥር ሰው ነው። የህዝቡን ዋነኛ ችግሮች ለመቅረፍ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ሁሉን ለማሳካት ጥረት ሲያደርግ ያለውን ሁሉ ሊያጣ ይችላል የሚል ስጋት አለኝ።

በዐብይ ህልም እና ተነሳሽነት ችግራችንን በአንድ ላይ ልናልፍ እንደምንችል ይሰማኛል። ይሁን እንጂ እንደምናስበው ሁሌም መልካም ሃሳቦች ወደ ፈቀድነው ላያመሩን ይችላሉ፤ እንደሚባለው የቁልቁለት ጉዞ ምንም ጊዜም የሚጀመረው በበጎ ሃሳብ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0