በህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንከር ያለ ህጋዊ ቅጣት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ። ረቂቅ አዋጁ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን የሚገዙ፣ የሚሸጡ፣ የሚያዘዋወሩና የሚያከማቹ አካላት፥ እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ የሚያደርግ መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደገለጹት፥ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩን ለመግታት በተለይም በድንበር አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥጥር ሲያደርግ ቆይቷል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚህ ሳቢያም አሁን ላይ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ስርጭቱ እየቀነሰ መጥቷል ነው ያሉት።

ለዚህም ከጉምሩክና ከህዝቡ ጋር በትብብር የተከናወነው ስራ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት በጦር መሳሪያ አያያዝ ዙሪያ ህግ እንደሚወጣ የሚደነግግ ሲሆን፥ በድንጋጌው መሰረት ረቂቅ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር አዋጅ መዘጋጀቱን አቶ ዝናቡ ይናገራሉ።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ከዚህ ቀደም የጦር መሳሪያን ይዞ የሚገኝ ሰው በአነስተኛ እስራት አልያም በዋስ ይፈታ የነበር ሲሆን፥ መሳሪያው ወንጀል እስካልተፈፀመበት ድረስም ከባድ ቅጣት ያስቀጣ እንዳልነበረ ነው አቶ ዝናቡ የሚናገሩት፡፡

ከዚህም ባሻገር ረቂቁ መሳሪያ የማይያዝባቸውን ስፍራዎችና የእደሜ ገደብ በማስቀመጥ፣ የጦር መሳሪያ ፈቃድ አሰጣጥ፣ ፈቃድ ማደስ፣ መሰረዝና መሳሪያን ማውረስ የሚቻልባቸውን ሁኔታዎችን ስርአት በግልፅ ማስቀመጡን አስረድተዋል፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በዚሁ የጦር መሳሪያ አያያዝ ረቂቅ ላይ ህዝባዊ ውይይት መጀመሩንም ከጠቅላይ አቃቢ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

በፋሲካው ታደሰ

FBC

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *