በምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት በነፍስ ግድያ፣ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ 138 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ ።

ሰሞኑን በዞኑ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት 37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር አስታውቋል ።

በተጨማሪም ተከስቶ በነበረው ግጭት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የቡድን የጦር መሣሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት መገኘታቸውን ነው የተገለፀው።

ጥይቶቹ የተያዙቱም በመተማ ዮሐንስ ከተማ በተቃጠሉ ግለሰቦች ቤት ውስጥ መሆኑን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም አርአያ ተናግረዋል ።

ከጦር መሳሪያ ጥይቶቹ በተጨማሪ ሀሰተኛ የብር ኖቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች፣ የቅስቀሳ መሣሪያዎች (ድምጽ ማጉያ) እና የተለያዩ ሰነዶች በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያሉት ።

ከዚህ ባለፈም የእጅ ቦንብም፣ የቅንቡላ፣ የአርፒጂ (የላውንቸር) እና የብሬንና ጥይቶችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም አንስተዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የጦር መሳሪያ ጥይቶችን ለታንክ እና ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ ሆነው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ብቻ የሚፈቀዱ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡

ክላሽ፣ ሽጉጦች፣ ስለታማ መሣሪያዎች፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ የደንብ ልብሶችም በተቃጠሉ ቤቶች ውስጥ መገኘታቸንም ነው ሌተናል ኮሎኔሉ ያረጋገጡት።

አሁን የተገኙት የቡድን መሣሪያዎቹ ጥይቶቹ መሆናቸውን የገለፁት ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም ሌሎች መሣሪያዎች አሁንም በግለሰቦቹ እጅ እንዳሉ እንደሚታመን ጠቁመዋል።

በቀጣይ የህብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ ከክልሉ ፖሊስና ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀናጅቶ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ሰላም ለማደፍረስ የሚሠሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር በሚውሉበት ጊዜ መንግሥት በቶሎ ለህግ አለማቅረቡን መገምገማቸውን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

አማራ ማስ ሚዲያን ጠቅሶ ፋና እንደዘገበው

Related stories   DR. ABIY AHMED ELECTED NEW CHAIRMAN OF EPRDF WITH DEMEKE MEKONNEN AS DEPUTY

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *