
በካንዳ ነጭ ሰፋሪዎች እ.አ.አ በ1876 “Indian Act” # የትምህርት ፖሊሲ በማውጣት እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ የነባር ህዝቦችን ልጆች ከወላጆቻቸው በግድ በመቀማት በአዳሪ ትምህርት ቤት እንዲማሩ ያደርጉ ነበር፡፡ በዚህ መልኩ 150,000 ህፃናት ከወላጅ-ዘመዶቻቸው ባህልና እሴት ውጪ እንዲያድጉ የተደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 6,000 ህፃናት በአድሃሪ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሞተዋል፡፡ አሁን ላይ ከጠቅላላው የካናዳ ሴቶች ውስጥ የነባር ህዝቦች ድርሻ 2.5% ብቻ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግን 25%ቱ “Canadian Eugenics laws (Sexual Sterilization Act of Alberta) በሚባል አዋጅ ያለ ፍቃዳቸው #መሃን እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በተመሣሣይ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች በአውስትራሊያ ነባር ህዝቦች ላይ አሰቃቂ ግፍና ዕልቂት ፈፅመዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ እዚሁ አፍሪካ ኮንጎ (ዛዬር) ውስጥ የቤልጂዬም ግዢዎች 10 ሚሊዮን ጥቁሮችን ጨፍጭፏል!!! በአጠቃላይ ከ15ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ጀምሮ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ድረስ ባሉት አራት ክፍለ ዘመናት የደቡብ አሜሪካ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ የአውስተራሊያና አፍሪካ ነባር ህዝቦች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ በጦርነትና በበሽታ ምክንያት ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ ተደርገዋል፡፡
ይህ የዕልቂትና ጥፋት ዘመን፣ የሰው ዘር ስቃይና ሰቆቃ የተገታው በኢትዮጵያ ጀግኖች ትግል፣ በአደዋ ድል ነው!!! ይህን ሃቅ ለመረዳት ካሻህ “Genocide of indigenous peoples” የሚሉትን ቃላት ለGoogle ስጠውና የዓለምን ታሪክ ጎልጉሎ ያወጣልሃል፡፡ ጎጉል ያመጣልህን የታሪክ ማስረጃዎች ዝም ብለህ አንብብና የቀድሞ አባቶችህን አመስግን፣ ይህን እንዲሆን ላስቻሉ የኢትዮጵያ ጀግኖችን አክብር፥ አመስግን፣ በኢትዮጵያዊነትህ ኩራ…!!! ከምንም በላይ ደግሞ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአፍሪካ፣ ከአፍሪካም አልፎ በመላው ዓለም ለአራት ክፍለ ዘመናት የቆየውን የሽንፈትና ውርደት፣ የዕልቂትና ሰቆቃ ዘመን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመግታት የተደረገውን ታላቅ ትግል ከፊት ሆኖ ለመራው ንጉስ #ዳግማዊ_አፄ_ሚኒሊክ ክብርና ፍቅር ይኑርህ!!! ለእሱ ፍቅር ባይኖርህ ውለታው አለብህ!!! አፄ ሚኒሊክ ለሀገሩና ህዝቡ የዋለው ውለታ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካን ያኮራል፣ በዓለም የሰው ልጆች ታሪክ በደማቅ ቀለም ተፅፏል፡፡
መላው ዓለም በሚደመምበት አኩሪ ታሪክ መኩራት ከተሳነህ የበታችነት ስሜት የተጠናወተህ መሆኑን በራስህ ላይ መሰከርክ እንጂ በዳግማዊ ሚኒሊክ ታሪክ ላይ ቅንጣት ያህል አትጨምርም አሊያም አትቀንስም፡፡ ከደቡብ አሜሪካ እስከ ሰሜን አሜሪካ፣ ከአውስተራሊያ እስከ አፍሪካ ያሉ የሰው ልጆችን ከዕልቂትና ውድቀት የታደገ አኩሪ ታሪካዊ መሪ ገድል ካሳፈረህ በራስህ የምታፍር ድኩማን መሆንህን መሰከርክ እንጂ ሌላ አዲስ ነገር አልጨመርክም፡፡ ይሄ እውነት ካልተዋጠልህ ከዕውቀት እጥረት የተነሳ የድንቁርና ምች የመታህ በሽተኛ ነህና እባክህን #ታከም!!! ክብር ለኢትዮጵያ ጀግኖች! የሚኒሊክ አምላክ ይመስገን! አሜን!