ሰሞኑን ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ የተባለውን “ያልተገባ” ንግግር ተከትሎ ብዙ ወቀሳዎች ተሰንዝረዋል፡፡ወቀሳው ተገቢ ነው፡፡ ለምን ቢባል ከእሳቸው ከአቶ ለማ መገርሳ የሚጠበቅ ንግግር ሳልነበረ ነው፡፡ አቶ ለማም በተሰዘረባቸው ወቀሳ ከመከፋት ይልቅ ደስ ሊላቸው ይገባል፡፡ለምን ቢባል ህዝብ ተስፋ ባይጥልባቸው እና እምነት ባይኖረው ኖሮ ወቀሳ ባላበዛባቸው ነበር፡፡ነቀፌታ ህዝብ ለአንድ “መልካም ሀላፊነት ለሚሰማው ዜጋ” የሚቸረው ተግሳጽ ነው፡፡
አቶ ለማን የሚወቅሱ ዜጎች ደግሞ ከመጠን ያለፈ ወቀሳ ሊሰነዝሩ አይገባም፡።ፖለቲከኛ ሁልጊዜም ይሳሳታሉ፡፡በአንድ ስህተት በአንዴ ሙልጭ ያለ ጭራቅ ማድረግ/መፍጠር ደግሞ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ስህተትም ነው፡፡ ተችዎችም እኮ እንሳሳታለን፡፡ንጹህ ነን የምንል የመጀመሪያውን ድንጋይ አስኪ አንወርውር?
ተቺዎች አቶ ለማ ያሉበትን አጣብቂኝ ሁኔታ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡አቶ ለማ ያልተገባ ንግግር ያደረጉት፣ መጤዎች እነ ጆሃር ለአመታት በኦሮሞ ዙሪያ ወጣቱን በሚፈልጉት ሌጣ ሜዳ ላይ ነድተው በገነቡት በተሳሳተ “ነጻዋ ኦሮሚያ ቀመር” የተገራ ተሰብሳቢ/Hostile Audience መሀከል መሆኑን መረሳት የለበትም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ የትግሬው ቡድን/ኢህአዴግ የሚባለው የደንቆሮዎች ድርጅት አባል የነበረ ሰው ነኝ የሚል ሁሉ፣ የተሰብሳቢው ፍላጎት ገምግሞ ስህተትም ቢሆን የተሰብሳቢውን ፍላጎት ለማርካት ሲባል ተሰብሳቢው የሚፈልገውን ነገር ተናግሮ የመውጣት ነገር የተለምዶ አባዜ መኖሩን መረሳት የለበትም፡፡አቶ ለማም ያደረጉት ይህን ነው፡፡
በትግሬው ኢህአዴግ የተገራ ቅውል ባለስልጣን ምንም ቢሰለጥን በህዝብ ፊት እንደ ተራ ካድሬ ለመዋሸት ወደ ኻላ አይልም፡፡የቆየ ልምድ ስለሆነ የኢህአዴግ ምርቆች ይህን ባህሪ በአንዴ ሊረሱት አይችሉም፡፡ችግራቸውን እነረዳ ለማለት ነው፡፡
አቶ ለማ መገርሳ ይህ የመጀመሪያ ስህተታቸው መሆኑን ተረድተን ይቅር ልንል ይገባል፡፡እሳቸውም የህዝብ ተጠሪ መሆናቸውን በሚገባ ተገንዝበው ሀላፊነታቸውን በጥንቃቄ ሊወጡ ይገባል፡፡
ወያኔ የሚባል ጥቁር ጣሊያን በጅብ-ጅማት በተሰራ ክራር ጦርነት አየጎሰመ ባለበት ሆናቴ በትንሹ በትልቁ በለውጥ ፈላጊው ጎራ መሀከል መነታረክ አይገባም፡፡
ታከሉ ኡማን በተመለከተ፣ በኗሪነት ፈቃድ ዙሪያ ከሚነሳበት አደገኛ ክስ ውጭ የሚሰራው ስራ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ጎበዝም ነው፡፡ ሊበረታታም ይገባል፡፡ አዲስ በህዝብ ድምጽ የተመረጠ ከንቲባ እስኪመጣ ድረስ በትእግስት አንደግፈው፡፡ አቶ ታከለ ያለ አግባብ መታወቂያ ማደል ማለት ከፍተኛ ወንጀል መሆኑን ተረድቶ በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል፡፡የወደፊት የፖለቲካ እድሉንም ሊወስነው ይችላል፡፡
ማሳሰቢያ – ይህ ጸሁፍ የጸሃፊውን እንጂ የአዘጋጁን አቋም አይወክልም