“Our true nationality is mankind.”H.G.

በማስረጃ እንሸናነፍ – ሀሮምሣ ቱለማ! በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው !!

ይህ የምንነጋገረው ነገር ግምትና ስሜት ላይ እንዳይሆን አስቀድሜ አሳስባለሁ፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ በማስረጃ እንሸናነፍ የሚል ነው፡፡እውነት ነጻነት ያወጣል እንደሚባለውም ውይይታችን በማስረጃና በምክንያት ብቻ መሆን አለበት፡፡ ቱለማ በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ብቻ ታጥሮ የነበረውን ንጉሳዊ ስርዓት የዘመነ ፖለቲካዊ ጥበብ በመጠቀም ዛሬ ወደሚገኝበት የቱለማ እምብርት ወደ ሆነችው አዲስ አበባ ያመጣ ነው፡፡ ሞጋሳና ጉዲፈቻን የሚህል ነገር ከማንም በላይ በመጠቀም በአካባቢው ባለመግባባት ሊከሰት የሚችልን ግጭትንና አለመተማመንን ለማስወገድ ስርዓትና ቅርጽ ያስያዘ ታላቅ ህዝብ ነው፡፡ ዛሬ ድረስ የሸዋ ህዝብ ወይም የቱለማ ቤተሰቦችና አጋሮች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት አስፈሪና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ናቸው፡፡ እስቲ ከዚህ በፊት ከነበሩት ተነስተን እስካሁን እንጥቀስ፡፡

የጁዎች ከቱለማዎች ጋር በመተባበር አጼ መኒሊክን በአጼ ቴዎድሮስ ከመገደል አስመልጠው ወደ ሸዋ የቱለማዎች ምድር አስመለጡት፡፡ አጼ ሚኒሊክ እራሱ በእናቱ ቱለማ ነበርና፡፡ ራስ ጎበና ዳጬ አባሙዳ ለመሆን አንድ ደረጃ ብቻ ይቀረው የነበረው የአካባቢው ጀግና እና ባለዝና አጼ ምንሊክን በመጠቀም ግዛቱን አስፋፋ፣አብዛኛው የማስፋፋት ስራ በቱለማዎች የዲፕሎማስ ጥበብ የተሞላ ነበር፡፡ወደ አድዋ ጦርነት አጼ ሚኒልክ የሄደው በዋናነት ከቱለማዎች ጋር ነበር፡፡ለምሳሌ ፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ተዓምር የሰሩ ሰው ናቸው፡፡ አጼ ሚኒሊክ ሲሞት ለአገሪቷ ንጉስ ፣ልጅ ኢያሱን የሾመው የቱለማው ታላቅ የፍትህ ሰውና የአድዋውም ታላቅ ጀግና ፊተአውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ነበር፡፡ በንጉሱ ሞት ምክንያት አገር እንዳይበጠበጥ ቀጥ ለጥ አድርጎ የመራውም ይህ ፊትአውራሪ ነበር፡፡

ሀይለስላሴ ስልጣን ይዘው መፈንቅለ መንግስት ተካሄዶባቸው ያከሸፈላቸው የቱለማው ጀግና ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ነበሩ፡፡ በመጨረሻም በደርግ ሲያዙ ሸፍትና ስርዓቱን አድን ብለው አጼ ሀይለስላሴ በሚስጥር የተናገሩት ጃጋማን ኬሎ ነበር፡፡

ደርግ ሲወድቅ ህወሓትን በከፍተኛ ሁኔታ በመቃወም ኢትዮጵያን ህዝብ ድምጽ የነበሩት የአዲስ አበባ ተማሪዎች ዋና ሞተሮቻቸው በከተማው የሰፈሩት የቀድሞ የቱለማ ወታደር የልጅ ልጆች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ 1997ዓ.ም ላይ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተነሳ ማለት አካባቢውም ሆ ብሎ ይነሳ ነበር፡፡ ይህንን ለመከላከል ህወሓት የዩንቨርስቲው ተማሪዎች እርስ በእርስ እንዳይተማመኑና እንዲጋጩ አደረገ፡፡ እቺን ከተማ የመሰረቱ የቱለማ ወታደሮች የልጅ ልጆችም በመልሶ ማልማት ስም ከአዲስ አበባ እንዲፈናቀሉ ተደረገ፡፡ አንዳንዶቹም ፎቅ ካልሰራችሁ እየተባለ መሬታቸው በጉልበተኞች ተነጠቀ፡፡ይህ ሲሆን የዛሬ የኦሮሞ ፖለቲካ አንቀሳቃሾች እያዩ እንዳላየ አለፉ፡፡ ቆይተው ግን የነሱ ጥቅም ሲነካ ተነሱ፡፡

ህወሓት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ በር ዘግተው ሽንጣቸውን ገትረው የተፋለሙት በቱለማዎችና በመጫ ልጆች በተመሰረተችው በአምቦ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቱለማዎች በሚገባ ከመጫዎች ጋር በመተባበር ከሰሯቸው ከተሞች መካከል ወሊሶና አምቦ የሚያክል የለም፡፡ስለዚህ ቱለማ ስንል እስከ አምቦ ማለታችን እንደሆነ ይታወቅ፡፡ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ከነሱ አግኝተናል፡፡ የጸጋዬ ዘመዳሞችና አሁንም ከቱለማዎች ጋር የነጻነት አጋሮቹ አጫሉ ሁንዴሳና ታከለ ኡማም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ዛሬ ታከለ ኡማ የቱለማዎችን ብሶት ይሰማል ብለን እየጠበቅነው ነው፡፡

ወደ ጀመርነው እንመለስና፣ ህወሓት ከስልጣን እንዲወርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ የተነሳው በሰሜን ሸዋ ነው፡፡ ህወሓት በመጨረሻ እጁን ሰጥቶ ሀይለማሪያም እንዲወርድ የተደረገው አራቱም የሸዋ-ቱለማ መግቢያ በሮች ጥርቅም በመደረጋቸው ነው፡፡

ዶ/ር ዐብይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆነው ቱለማዎች በሸዋ ዘመነ መንግስት ይጠቀሙበት የነበረውን ፍልስፍና በመጠቀም ነው፡፡ አቶ ለማም የቱለማዎች ጥበብና አስተሳሰብ በማራመዱ ነው ከጫፍ እስከጫፍ ተወዳጅነት ያገኘው፡፡ ቱለማዎች እጅግ በጣም ብዙ መልካም ነገር ያበረከቱ ናቸው፡፡ አሁንም በኢትዮጵያ ፖለቲካ አስተሳሰባቸውና ፍልስፍናቸው ተወዳዳሪ የለውም፡፡ባጭሩ ህወሓትን ከመነሻ የተነሱበትም አሁንም እየቀበሩት ያሉት ቱለማዎች ናቸው፡፡

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

የቱለማዎች አስተሳሰብና ፍለስፍና የበለጠ እንዲቀጥል ምን እናድርግ?
እንደሚታወቀው የኦሮሞ ፖለቲካ መሰረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያለው ጸረ ቱለማ ነው፡፡ የዘመኑ ኮከብ ጀግና የሆነውን ራስ ጎበና ዳጬን እርኩስና ጭራቅ አድርጎ ለትውልድ የሚያስተላልፍ ፖለቲካ እጅግ የጥላቻ ፖለቲካ ነው፡፡ ጎበና ዳጬ እኮ አይደለም እዚህ መሀል አገር እስከ ቀይ ባህር የተዘረጋና የገነነ የጦር ጥበብና ጀግንት የነበረው ሰው ነው፡፡ ዋናው ነገር ጎበና ዳጬ የወለደው የቱለማ አስተሳሰብ በባረንቱዎች አይወደድም፣ አብዛኞቹ ባረንቱዎች የግራኝ አህመድ ወታደሮች ነበሩና፡፡ ጠላትነቱ ለዚህ ነው፡፡ በኋላ ላይ ሀይማኖታቸውን ቀይረው ወደ ባሌ ተራራ ሄደው የባረንቱዎችን ተረት ተረት እየሰሙ ወለጋዎችም ተቀላቅለዋቸዋል፡፡ ባረንቱ ሲባል እነ ባሌ፣ አርሲ ሀረርጌ የመሳሰሉት አካባቢ ሰዎች ጸረ ጎበና ዳጬ ሊሆኑ የቻሉት ከግራኝ አህመድ ሌጋሲ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ምሳሌ የአኖሌ ሀውልት ነው፡፡የጎበና ዳጬን አመራር በክርስቲያንነትና የክርስቲያን ስርዓት ደገፈ በሚል ነው፡፡ ሌላ አይደለም፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ማድረግ የሚቻለው ጸረ ሚኒሊክ አቋማቸውን ነው፡፡ አንድ የሚኒሊክ ሀውልት እናፍረስ ሲሊ ምን ማለት ነው ቢባል አንድም ሀውልቱን አፍርሰን የግራኝ አህመድን ሀውልት እንተክልና ያኔ ያጣነውን ድል እንቀናጃለን ነው፡፡ አንድም በሚኒሊክ ሀውልት አካባቢ ያለውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን አፍርሰን የግራኝ አህመድ መታሰቢያ መስጊድ እንሰራለን የሚል ነው፡፡በሌላ አባባል የጅጅጋውን ትራዴጂ የናፈቃቸው ናቸው፡፡ ሌላው በኦሮሞ ብሄር ስም እነሱን እየተከተለ የሚያጨበጭበው ታሪክ የማያውቅና የስሜት ጋላቢ ነው፡፡ ጅማዎች(መጫ) እንደወሎና ሸዋ የተረጋጉና አርዓያ መሆን የሚችሉ ሙስሊሞች ናቸው፡፡በአሁኑ ሰዓት ባረንቱዎች ደጋፊ ለማብዛት ጅማና ወሎ ከሚሴ ሳይቀር እየገቡ በኦሮሞ ስም በቱለማ አስተሳሰብ ላይ እየቆፈሩት ያለው ምሽግ እናውቀዋለን፡፡ለዚህ ደግሞ ዋናው የባረንቱ ፖለቲካን በሚዲያ እየዘወረው ለው ጃዋር መሀመድ ነው፡፡በጣም ጥላቻ እየተዘራ ነው፡፡ ለምሳሌ ጣይቱ ቅልጥ ያለች የየጁ ጋላ ናት፡፡ ከክርስቲያን መንግስት ጋር ተባብራ ከነጎበና ዳጬ ጋር ወግታናለች፣ ልጅ ኢያሱ ሙስሊም ነው እያለች አሳምጻበታለች በሚል እነጃዋር ከፍተኛ ጥላቻ እያደረጉባት መሆኑ አንድ ማሳያ ነው፡፡እኔ ቤተሰቤ ውስጥ ሙስሊም አለ ግን ሙስሊም ስለሆኑ አንድም ቀን እንዲህ ጥላቻ ሲናገሩ ሰምቼ አላውቅም፡፡ እናም ይህንና የቱለማን ታሪክ፣ እሴትና እርስቶችን ከጥፋ ለመታደግ ምን እናድርግ ወደ ሚለው እንሂድ፡

1. በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያን ለገነቡ የቱለማ አባቶችና ቤተሰቦች የመታሰቢያ ማዕከልና ሀውልት ሊገነባላቸው ይገባል፡፡ለራስ ጎበና ዳጬ፣ ለጀነራል ጃጋማ ኬሎና ለፊትአውራሪ ሀብተጊዮርጊስና ለሌሎችም ለሚገባቸው በአንድ አደባባይ ላይ ሀውልትም ሊቆምላቸው ይገባል፡፡

2. የኦሮሞ ባህል ማዕከል ስሙ ተቀይሮ ራስ ጎበና ዳጬ የባህል ማዕከል መባል አለበት፣

3. የሜኪሲኮ አደባባይ ስሙ ተቀይሮ የቱለማ አደባባይ መባል አለበት፡፡

4. ቃሊቲ ዘመን የማይሽረው የአባ ሙዳዎች መፍለቂያ የነበረ ከመሆኑም አንጻር ልክ እንደ አሜሪካው ሆሊውድ ተከልሎ የተለየ በጀት ተመድቦለት ለዘመኑና ለትውልዱ የሚመጥን በዘመናዊ መልኩ የተገነባ የአባሙዳዎች ከተማ መደረግ አለበት፣

5. በአዲስ አበባ ከተማ ታካሪዊነቱን የጠበቀ ቤተ(መነ) ሙዳ መገንባት አለበት ፡፡ ልክ ቤተክርስቲያን ላይ መስቀል እንደሚደረግ፣ መስጊድም ላይ ጨረቃ እንደሚደረግ መነሙዳ ላይም ኦዳ ተደርጎ አንድ ቤተእምነት መቆጠር አለበት፡፡

6. አባቶቻችን ለሰላም፣ ለእርቅ፣ ለውይይት፣ ለብዙ ጥበብና መንፈሳዊ አላማ ይጠቀሙበት የነበረውን የኦዳ ምልክት ማነኛውም የፖለቲካ ድርጅት እንዳይጠቀም ማገድ፡፡

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

7. የአባሙዳን ምክርና ምርቃት ያልተቀበለ ሰው መሪ እንዲሆን አለማድረግ፡፡

8. ቄሮ በመባል የሚታወቀው ከቱለማ አስተሳሰብና ከአባሙዳዎች አመለካከት ጋር የሚጋጭ ነው፡፡ቄሮዎች የጂሀድ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው፡፡ ምክንያቱም የቄሮ መሰረት ምስራቅ ሀረርጌ ው፡፡ ቱለማዎች ጸረ ህወሓት ትግል ያደረጉ ወጣቶች (ዕድሜው ከ16-24) ፎሌ ብሎ ነው ሲጠራ የነበረው፡፡ አሁንም በቱለማ ምድር እስካሁን ሌላ ቦታ በቄሮዎች ተደረጉ እንደሚባለው ፎሌዎች ሰው መግደል፣ መዝረፍ፣ መስቀልና በርካታ ወንጀሎችን ነውሮች አልጸፈጸሙም፡፡ፎሌዎች ህዝብን የሚረዱ እንጂ የሚጎዱ አይደሉም፣ ሲጎዱም አልታዩም፡፡ምስጋና ይገባቸዋል፡፡በመሆኑም ቄሮ በቱለማ መሬት እና ህዝብ መካከል እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ፡፡ በአባሙዳዎች መወገዝ አለበት፡፡

9. የመጫና ቱለማ ማህበር በህጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሶ በነታደሰ ብሩ የታለመውን ህዝብን ማቀራረብ፣ የተጎዱትን የመርዳት፣ ከባህል፣ ከትምህርት ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ስራ እንዲሰራ ማድረግ ነገር ግን ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር እንዳይተባበር ማድረግ፡፡ በነገራችን ላይ መጫና ቱለማ አሁን በደንብ ጎልቶ እንዲወጣና እንዲታይ የማይፈለገው እነጃዋር በፈጠሩበት አሻጥር ነው፡፡

10. የነጀነራል ታደሰ ብሩ ታሪክ ሆነ ተብሎ ለፖለቲካ ፍጆታ ተጣሟል፣ ታደሰ ብሩ ልክ እንደነ መንግስቱ ነዋይ ማዕከላዊ መንግስትን በመቃወም መፈንቅለ መንግስት በማድረግና በማመጽ ስርዓቱን ለመለወጥ የታገለ እንጂ ለብሄር ታገለ የሚባለው ውሸት ነው፡፡ የነመንግስቱ ነዋይ አይነት በወታደሩ ውስጥ ከነበሩት ሽኩቻዎች አንዱ ነው፡፡ ይህንን የቅጥፈት ታሪክ በመፍጠርና የታደሰ ብሩን ታሪክ በማበላሸት የወቅቱ የብሄር ተኮር የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡የወቅቱን ስርዓትና በገበሬዎች ላይ ይደረግ የነበረውን በደል በመቃወም እንጂ በወቅቱ ኦሮሞ የሚለው ቃል በራሱ ብዙም ያልተለመደና መሰረት ያልያዘ ነበር፡፡ አክሊሉ ሀብተወልድ አሉት የተባለውም በማስረጃ ያልተደገፈና ሆነ ተብሎ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ተብሎ የተቀመረ ነው፡፡ መጫና ቱለማ ከፈረሰ በኋላ መጀመሪያ ያቋቋመው ድርጅት …የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት.. የሚል እንደነበር ታሪክ ዘግቧል፡፡ ኦነግ የተመሰረተው በጣም ቆይቶ ነው፡፡ የህብረተሰባችን የንባብ ልምድ ደካማነት ሽፋን በማድረግ የተለቀቀ የሀሰት ትክርክት ነው፡፡ለምሳሌ የባሌ አመጽ በወቅቱ የባሌ አመጽ እንጂ የኦሮሞ አመጽ በሚል አለመጠራቱ ነው፡፡ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ታደሰ ብሩም መፈንቅለ መንግስት እንዳያደረግ፣ እንዲሁም የባሌ አመጽ መሪም የዋቆ ጉቱን አመጽ አክሽፏል፡፡አሁን እንደሚወራው ቢሆን ኖሮ የወቅቱ ስርዓት በጃጋማ ኬሎ ላይ ይህን ያህል እምነት አድሮበት ከብዙ ወታደር ጋር ሰፊ ተልዕኮ አይሰጠውም ነበር፡፡ዊክሊክ ከዚህ በፊት በለቀቀው ማስረጃ

(https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=293921058087823&id=290727848407144&__xts__%5B0%5D=68.ARCIPZD4qlL7GEjBP8QRYIdr7EJvkkmJ2gxcCFb5RK_1x_er-G37kehiqKW8ef3hxADl10vcQy38h40OEMA2ZM9_iUsS-Yf4shzazEERIn5beJKnzO3RlKA)

መሰረት ታደሰ ብሩ ያደረጉት ትግልና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተለያዩ ናቸው፡፡ ኦነግ የተመሰረተው መጫ ቱለማ ከፈረሰ በኋላና አሁን ኦብነግ ከሚባለው ጋር በተቃኘ መልኩ ነው ያለው፡፡ስለዚህም የታደሰ ብሩ ትግልና የፍትህ ጥያቄ አሁን ካለው ኦሮሞነት ጋር አይገኛኝም፡፡ምንም ይባል ጀነራል ታደሰ ብሩ በታየው መልኩ ለቱለማ ገበሬዎችና የኑሮ መሻሻልና ለህዝቦች ላደረገው ታላቅ ትግልና አስተዋጽኦ ክብር ይገባዋል፡፡ አንድ የቱለማዎች የትግል አባት ተደርጎ መከበር አለበት፡፡ ኦነጎች ከታደሰ ብሩ ላይ እጃችሁን አንሱ፡፡

11. አባ ሙዳዎችንና የቱለማ ምሁራንን የጥናትና ምርምር ማእከል ማቋቋም፡፡

12. የቱለማ Media Network(TMN) ማቋቋም እንዲሁም የOromo media Network(OMN) የቱለማን ታሪክ፣ እሴትና አባቶችን ማንቋሸሽና ማጥላላት ካላቆመ ከቱለማ መሬት እንዲወጣ ማድረግ፣ እምቢም ካለ ከእርሱ ጋር ከሚተባሩት ሁሉ ላይ እርምጃ መውሰድ፡፡

13. የምስራቁ ክፍል (የባረንቱዎች በግራኝ አህመድ ሌጋሲ ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ) ፖለቲካና የወለጋ ( በጆሀን ክራፍ ሊጋሲን የማስቀጠል የጥላቻ) ፖለቲካ በቱለማ ሊጋሲ ፣ታሪክና ለምሰራቅ አፍሪካ ባበረከታው እጅግ ብዙ እሴቶች ላይ የማንቋሸሽና የማጥላላት ይዘት ያለው በመሆኑ እንዲታረም ማድረግ፣ በታሪክ፣ በእውነትና በምክንያት ላይ ያልተመሰረቱ ተረኮችና አባባሎች እንዲቆሞ ማድረግ ለዚህም ከባረንቱና ቦረና ጎሳዎች መካከል ነጻና ገለልተኛ ምሁራን አባ ሙዳዎች አባ ገዳዎች እና ሌሎችም የሀይማኖት አባላቶች ያሉበት ቡድን ተቋቁሙ እውነታውን እንዲያጣራና ለህዝብ እንዲቀርብ ማድረግ፡፡

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

14. ኦሮሞ የሚለው ቃል በነ1840 በጀርመናዊው ጆሀን ክራፍ የተፈጠረ ነው፡፡ ጋላ ማለት ደግሞ እምነቴን አልቀይርም ፣ ባህሌን አልተውም ማለት ነው፡፡ ይህ እውነት የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖረው የውይይትና የክርክር መድረክ እንዲዘጋጅ ማድረግ፡፡ አለበለዛ ግን ቱለማ ኦሮሞ የሚል ቃልን በመተው እራሱን ቱለማ ጋላ ብሎ እንደሚጠራ ማወጅና መጠቀም፡፡

15. የኦዳ ምልክት ያለበት ባንዲራ በመጠቀም ሰው የሚሰድቡ፣ ጥላቻን የሚዘሩ፣የአባሙዳን አስተሳሰብና ፍልስፍናን የሚያዋርዱ ማናቸውም ላይ በቱለማ መሬት ላይ ከተገኙ እርምጃ መውሰድ፡፡

16. የእስልምና ፣የኦርቶዶክስ እና የፕሮቴስታንት እና መሰሎቻቸው ለአባ ሙዳዎች ክብር እንዲሰጡ ማድረግ፣ጨሌ፣ቃልቻ እያሉ ባለማወቅ በቱለማ ባህልና የፍለስፍና እሴቶች ላይ የሚደረግ የማጥላላትና የማንቋሸሽ ተግባር እንዲያቆሙ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠየቅ፡፡

17. ኦዳ፣ሙዳ፣ኢሬቻ፣ሞጋሳና ጉዲፈቻ የቱለማ የጥበብና የፍለስፍና ውጤት የሆኑ በመሆናቸው ከዚህ ጋር በተያያዘ በትምህርት ተቋማትም ሆነ በሚዲያ ሲተላለፍ በግልጽ የቱለማዎች የጥበብ ውጤት ነው ተብሎ እንዲነገርና ለባለቤቶቹ ክብር እንዲሰጥ ማድረግ አለበለዛም ዘመቻ መክፈትና መቃወም፡፡

18. አፋን ቱለማና አማርኛ የቱለማዎች አንደኛ ቋንቋ ናቸው የበለጠ እንዲበለጽጉ ግን በምንም ተዓምር የላቲን ፌደልን አለመጠቀም፡፡የላቲን ፊደል የወለጋዎች የወረራ መሳሪያ በመሆኑ ቱለማዎች የማንም ወረራ አይቀበሉም፣ዝም ብለውም አያዩም፡፡

19. ኦህዴድ የወለጋዎችን ባህልና ቋንቋ መሰረት አድርጎ በሚዲያም ሆነ በትምህርት ተቋማት የሚጠቀማቸው ስርዓቶች እንዲቀይር አለበለዛ ግን ቱለማ እንደማይወክል ማሳወቅ፡፡
20. በሂደት ቱለማዎች አዲስ አበባን ዋና ከተማ መባድረግ የቀድሞ የሸዋ ግዛትና የቱለማ አስተዳደር እንዲሆንና በዚህም እሴታቸውን፣ ታካሪቸውንና ከአባቶቻው የወረሷቸውን መንፈሳዊና ቁሳዊ እርስቶችን እንዲያበለጽጉ መትጋት፡፡

21. በአዲስ አበባ መልሶ ማልማት ሰበብ የተፈናቀሉ ቱለማዎች አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ካሳ እንዲከፈላቸው መታገል እንዲሁም ያለ ቱለማ ህዝብ ፈቃድ በአዳማ የሰፈሩ ከሶማሌ የተፈናቀሉ ባረንቱዎች እንዲነሱ መጠየቅ ምክያቱም በሂደት ከሀይማኖትንና ከባህል ጋር በተያያዘ ግጭት ቢነሳ ቱለማዎች በገዛ እርስታቸው በደል እንዲደርስባቸው አይፈልጉም፡፡እንዲሁም ቱለማዎችና ታሪካዊ ባለቤቶቹ( ለምሳሌ በምዕራቡ በኩል መጫዎችም የቱለማዎች የቤተሰብ አጋር ስለሆኑ) ሳይፈቅዱ በማነኛውም አይነት ለፖለቲካዊ ሸርና ተንኮል ቱለማዎች በመሬታቸው ላይ ህዝብ እንዲሰፍር አይፈቅዱም፡፡

22. ሱሉልታ ላይ ከዓመት በፊት የተመረጠ የቱለማዎች አባ ሙዳ አለ፡፡ ኦህአዴድ ግን ግለጽ በሆነ መልኩ አድሎ በማድረግ አስሮት ነበር፣ አሁንም አግልሎታል፡፡ ይህ የለየለት በቱለማዎች ላይ የተከፈተ ጥላቻ ነው፡፡ በአስኳይ ለአባ ሙዳችን የሚገባውን ክብር እንዲሰጠው እንጠይቃለን፡፡

በአጠቃላይ በቱለማዎች ላይ የተከፈተው የተቀናጀ የማጥላላትና የማንቋሸሽ ዘመቻና ተግባር ይቁም፡፡
Make_ቱለማ_Great_Again!
I amቱለማ First!
እስካሁን ተጠይቀው መልስ ያልተሰጠባቸው ስለቱለማዎች ጥያቄዎችና ክርክሮች ማንበብ ከፈለጉ(በተለይ ስለ ኦሮሞ ምንነትና ኦነግ ) እነሆ፡

ማሳሰቢያ  – ጽሁፍ የዝግጅት ክፍሉን አመለካከት አይወክልም። ሙሉ በሙሉ የባለጉዳዮቹን አምነትና ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነው። መቃወሚያም ሆነ የድጋፍ ሃሳብ ያለው አካል አስተያየቱን ቢልክ ይስተገዳል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0