ዶ/ር አብይ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ እንደያዙ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በደስታ ባህር ዋኝቶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

በሚሊዮን የሚቆጠር የአዲስ አበባ ህዝብ በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ለጠ/ሚኒስትሩ ያሳየው ድጋፍ፣ በተከታታይ ጠ/ሚኒስትሩ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተዘዋወሩ ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ህዝቡ ያሳያቸው የነበረው ፍቅርና ድጋፍ በቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ያልታዬ ነው። ድጋፉና ፍቅሩም በደርግም ይሁን በህወሃት-ኢህአዴግ ዘመን እንደነበረው የግዳጅ ሳይሆን፣ ከልብ የመነጨ ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ መንግስታቸው የሚያከናውናቸውን ስራዎችና የሚያወጣቸውን ፖሊሲዎች ሁሉ ለህዝብ ግልጽ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸው በአገሪቱ ግልጽነት የተሞላበት አዲስ የፖለቲካ ባህል ለማስፈን ፍላጎት እንዳላቸው ማሳየታቸው ነው በሚል ምስጋና ሲቀርብላቸው ቆይቷል።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

በብዙ አገሮች ታሪኮች እንደታየው በመንግስትና በህዝብ መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች የሚጀመሩት ከሚስጢራዊነት ጋር በተያያዘ ነው። መንግስታት የሚሰሩዋቸውን ስራዎችና የሚያወጡዋቸውን መመሪያዎች ከህዝብ መደበቅ ሲጀመሩ ወይም በወረቅት ላይ የሚናገሩትና በተግባር የሚሰሩት የተለያዩ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በመንግስት ላይ ግልጽነት ሲጠፋ፣ የ ህዝብ ቀልብ ወደ አሉባልታዎችና የሴራ ትንተናዎች ይሳባል።
የዶ/ር አብይ መንግስት፣ መረጃዎችን በተገቢው ጊዜ ይፋ የማድረግ አሰራሮችን መከተል ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ አሰራሩ በፌደራል መንግስት ብቻ የታጠረና ወደ ክልሎች ያልወረደ እንደነበር ታይቷል።

በፌደራል ደረጃ የነበረውም አሰራር ቢሆን ለረጅም ጊዜ ሊቀጥል አልቻለም። መንግስት በፍጥነት የማስተካከያ እርምጃ ካልወሰደ መጪው ጊዜ የሴራ ፖለቲካ ትንተና እንደ ሮኬት የሚወነጨፍበት ጊዜ እንደሚሆን ግልጽ ነው። የሴራ ፖለቲካ ትንተናዎች ሲበዙና አሉባልታዎች በንፋስ ፍጥነት ሲጓዙ በአገር ውስጥ የሚታየውን አለመረጋጋት ይበልጥ እንዲባባስ ማድረጉም አይቀርም።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

የአብይ መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ ከመታወቂያ እደላ ጋር በተያያዘ ለተነሳበት ተቃውሞ ፈጥኖ መልስ ለመስጠት አለመቻሉ፣ የኦሮምያ ክልል ባለስልጣናት በለገጣፎና በአዲስ አበባ ዙሪያ ከዜጎች መፈናቀል ጋር በተያያዘ የተነሳባቸውን ተቃውሞዎች እና ትችቶች በተገቢው መንገድ ለማስረዳት አለመቻላቸው፣ የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከሶማሊ ክልል ተፈናቅለው የመጡትን የኦሮሞ ተወላጆች በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ከተሞች ለማስፈር የፈለጉበትን ምክንያት ሲያስረዱ የተጠቀሙባቸው አወዛጋቢ አገላለጾች እና የቀረቡትን ትችቶች በተገቢው መንገድ ለማብራራት አለመቻሉ፣ በመንግስት ውስጥ ግልጽነት ይሰፍናል ብሎ ተስፋ ሰንቆ የነበረው ህዝብ ፣ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ፣ አሰራሩን በቃል ከመተቸት አልፎ ታሪካዊውን የአድዋ ድል ለማክበር በሚኒሊክ አደባባይ በተገኘበት ወቅት ተቃውሞውን በአደባባይ ገልጿል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

መንግስት እስከምን ደረጃ ግልጽ መሆን እንዳለበት ባለማወቁ እንዲሁም በክልሎች ውስጥ የሚታዬው የተለመደ የድብቅነት አሰራር መቀጠል፣ የሴራ ፖለቲካ የበላይነት ይዞ የአገሪቱ ትልቅ ፈተና ሆኖ እንደሚቀጥል የሚያመለክት ነው። አሁን ያለው የመረጃ ቴክኖሎጂ ማሰራጫዎች እድገት የሴራ ፖለቲካን ለማስፋፋት አመቺ ሁኔታ የፈጠረ ሲሆን፣ መንግስት ግልጽነትን የሚያሰፍንበትን አሰራር እያጠናከረ ካልሄደ በስተቀር ተጽዕኖውን በቀላሉ መቋቋም አይቻልም…

 

ፋሲል የኔአለም (ኢሳት ዜና ሀተታ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *