“Our true nationality is mankind.”H.G.

ከሃምሳ አንድ ሺህ በላይ የመኖሪያ ቤቶች ረቡዕ በእጣ ሊተላላፉ ነው

 

ስለ ጋራ ቤቶች ዝርዝር ጉዳይ ጌጡ ተመስገን እንደሚከተለው አስፍሮታል።

የኮደሚንየም ተመዝጋቢዎች …

የካቲት 27 ቀን 2011 በእጣ ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፈው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዝርዝር እና በዕጣው ለመግባት የሚያስፈልገው የቁጠባ መጠን

ሀ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዝግጁ የሆኑ የቤቶች ዝርዝር በቁጥር

1. ባለ 1 መኝታ = 3,060
2. ባለ 2 መኝታ = 10,322
3. ባለ 3 መኝታ = 5,194
በጠቅላላ ለ2ኛው ዙር ለዕጣ ዝግጁ የሆኑ 18,576 የ40/60 ቤቶች ናቸው

ለ. በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ያሉ ተመዝጋቢዎች

1. በባለ 1 መኝታ = 11,699
2. በባለ 2 መኝታ = 57,277
3. በባለ 3 መኝታ = 56,138
በጠቅላላ 125,114 ተመዝጋቢዎች በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም እየቆጠቡ ይገኛሉ።

ሐ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን (ለሁሉም የመኝታ ዓይነት በምዝገባው ወቅት ከነበረው ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ 40% እና ከዚያ በላይ የቆጠቡ ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ)

1. ለባለ 1 መኝታ = 162,645×0.4 = 65,058 ብር
2. ለባለ 2 መኝታ =250,000×0.4 = 100,000 ብር
3. ለባለ 3 መኝታ = 386,400×0.4 = 154,560 ብር

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

መ. ለ2ኛው ዙር የ40/60 የዕጣ ፕሮግራም ብቁ (ዝቅተኛ የቁጠባ መጠንን ያሟሉ) ሆነው ለዕጣው ተወዳዳሪ የሚሆኑ የተመዝጋቢዎች ብዛት በቁጥር

1. በባለ 1 መኝታ = 5,502
2. በባለ 2 መኝታ = 25,634
3. በባለ 3 መኝታ = 26,126

በጠቅላላ 57,262 ብቁ ተመዝጋቢዎች ለ18,576 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕጣው ተወዳዳሪ ይሆናሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ በበኩሉ የጋዜጣ መግለጫውን ተከታትሎ የሚከተለውን ዘግቧል።

በአዲስ አበባ የፊታችን ረቡዕ 51 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ እንደሚወጣባቸው የከተማዋ አስተዳደር ገለፀ።

ጉዳዩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳድር ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም 52 ሺህ 229 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የፊታችን ረቡዕ ለባለ ዕድለኞች በዕጣ የሚተላለፉ መሆኑን ነው የገለፁት ።

በዕጣ ከሚተላለፉ ቤቶች ውስጥም 32 ሺህ 653 ቤቶች የ20/80 ቤቶች ሲሆኑ፥ ቀሪዎቹ 18 ሺህ 576 ደግሞ የ40/60 ቤቶች ናቸው ብለዋል ።

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

በዚህ መሰረትም በዕጣ ከሚተላለፉ የ20/80 ፕሮግራም ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 248 ስቲዲዮ፣ 18 ሺህ 823 ባለ አንድ መኝታ ፣ 7 ሺህ 127 ባለ ሁለት መኝታ እና 5 ሺህ 455 ቤቶች ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ ናቸው ተብሏል።

በእነዚህ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ውስጥ የሚካተቱትም በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው በ2005 ዓ.ም በነባር መደብ የተመዘገቡና በ2005 ዓ.ም የአዲስ ባለ ሶስት መኝታ ተመዝጋቢ ደንበኞች ብቻ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባለፈም ነባር መደብ ተመዝጋቢዎች ዕጣ ውስጥ ለመግባት 40 ተከታታይ ወራት መቆጠብ ሲጠበቅባቸው ፦ ባለ ሶሰት መኝታ አዲስ ተመዝጋቢዎች ደግሞ ለ60 ተከታታይ ወራት መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል ።

በ20/80 የቤቶች ፕሮግራም ውስጥ ለአካል ጉዳተኞች 5 በመቶ፣ ለመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ፣ለሴቶች ደግሞ 30 በመቶ የተለየ ኮታ ተሰጥቷቸዋል።

የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራም ውስጥ የሚገኙ ቤቶች ስፋት ስቲዲዮ 30 ካሬ ሜትር፣ባለ አንድ መኝታ 55 ካሬ ሜትር ፣ባለ ሁለት መኝታ 75ካሬ ሜትርና ባለ ሶስት መኝታ ደግሞ 105 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም ለዕጣ ከከቀረቡ 18 ሺህ 576 ቤቶች ውስጥ 3 ሺህ 60 ባለ አንድ መኝታ፣ 10ሺህ 322 ባለ ሁለት መኝታ፣ 5ሺህ 194 ቤቶች ደግሞ ባለ ሶስት መኝታ መሆናቸው በመግለጫው ተጠቅሷል።

በእነዚህ የቤቶች ፕሮግራም ዕጣ ውስጥ ለመግባትም ሁሉም ደንበኞች በመጀመሪያ ምዝገባ ወቅት ከነበረው ጠቅላላ ዋጋ ውስጥ ቢያነስ 40 በመቶ መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል።

በዚህ መሰረትም ደንበኞች ለባለ አንድ መኝታ 65 ሺህ 58 ብር፣ ለባለ ሁለት መኝታ 100 ሺህ ብር ለባለ ሶስት መኝታ ደግሞ 154 ሺህ 560 ብር መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል።

በ40/60 የቤቶች ፕሮግራም በዕጣ ለመተላለፍ ከቀረቡ ቤቶች ውስጥም ለመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ልዩ ኮታ መሰጠቱ ነው የተገለፀው።

በዚህ ፕሮግራም የሚተላለፉ ቤቶች ስፋት ባለ አንድ መኝታ 60 ካሬ ሜትር ፣ባለ ሁለት መኝታ 80 ካሬ ሜትርና ባለ ሶስት መኝታ ቤቶች ደግሞ 100 ካሬ ሜትር ስፋት አላቸው።

በመላኩ ገድፍ

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0