“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኦሮሚያ ክልል በእጣ የሚከፋፈለው የኮንዶሚኒየም እደላ እንዲቋረጥ አሳሰበ፤ የአዲስ አበባ አስተዳደር ያለው ነገር የለም

የአዲስ አበባ አስተዳደር በእጣ የሚያከፋፍለውን የኮንዶሚኒየም ቤቶች አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልላው መንግስት እንደሚቃወም ጠቅሶ መግለጫ አወጣ። በክልሉ ውስጥ የሚደረግ ማናቸውን ተግባራት ከኦሮሞ ህዝብ እውቅናና የክልሉ መንግስት ፈቃድ ውጪ ሊከናወን እንደማይገባ አሳስቧል።

የክልሉን የኮሙኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ እንደዘገበው፤ የክልሉ መንግስት አቋሙን ይፋ ያደረገው ዛሬ ነው። መግለጫው ይፋ ከመሆኑ በፊት ጃዋር መሐመድ የአዲስ አበባ ክልልን አስጠንቅቆ ነበር። እጣው ከወጣ በሁዋላም ብትናንትናው እለትና በዛሬው እለት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፎች ሲደረጉ መዋላቸውን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ አመልክቷል።

ጃዋር መሐመድ ከሰልፈኞች ጋር በመሆን ንግግርና መፈክር ሲያሰማ ታይቷል። በመፈክሩም ክልሉን አስጠንቅቋል። የሕዝቡን ጥያቄ ወደ ሁዋላ በማለት ወደ ተግባር የሚገባ ከሆነ ተቅውሞው እንደሚቀጥልም አስጠንቅቆ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ በሰበር ዜና እንዳስታወቀው የኦሮሮሚያ ክልል ድርጊቱን አጥብቆ እንደሚቃወምና ከኦሮሞ ህዝብ እውቀና ውጪ ማናቸውም ተግባራት ሊፈጸሙ እንደማይገባ፣ ይህንን የሚያደርገው የሌሎች ብሄሮችን መብት ለመጋፋት ሳይሆን በክልሉ ውስጥ ሙሉ ሃላፊነት ስላለው ነው።

በዙም ዝርዝር ያለቀረበበት የሰበር ዜና በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ካነሳቸው መካከል አምቦ፣ ጊንጪ፣ አልተካተቱም። ሰሞኑንን ራሳቸውን ይፋ ያደረጉት የቱለማ እንቀስቃሴ በጉዳዩ ላይ የያዘው አቋም እስካሁን ይፋ አልሆነም። ሙሉ ሸዋን ለማዳረስ የተነሳው የቱለማ እንቅስቃሴ አብሮ በመኖር የሚያምን፣ በመዋለድና በዝምድና የሚመካ፣ ግድያና ጸብ የኦሮሞ ባህልና መለያ አለመሆኑን የሚገልጽ እና በቅርቡ እነ ጃዋርን በመቃወም የራሱን ሚዲያ ከፍቶ የኦሮሚያን እምብርት ሸዋን በልዩ ሁኔታ በውስጧ ካሉት ማህበረሰቦች ጋር ለማደረጃት እንደሚሰራ ይፋ ያደረገ እንቅስቃሴ ነው።

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

በአብዛኛው የኦሮሚያ የተቃውሞና የአስተዳደር መረቦች ዋናውን ባለቤት ቱለማን ያላከበረና በወጉ ሃላፊነት ያልሰጠ፣ ከማህበረሰቡ ወግና ባህል ባፈነገጠ መልኩ በርካታ ህጸጾች እንደሚሰሩ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ በስፋት እየዘገበ ነው።

ገንዘብ በቆጠቡና በከተማዋ በጀት የተገነቡትን ቤቶች የኦሮሚያ ክልል እንዴት አድርጎ እንደሚወስድ ወይም እንደሚረከብ ባይታወቅም፣ ሚዛን የጠበቀ አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች ከቀያቸው የተፈናቀሉ የመኖሪያ ቤት ሊሰጣቸው እንደሚገባና የተቀረው በተያዘው እቀድ መሰረት በእጣ ሊከፋፈል እንደሚገባ ይናገራሉ። የአዲስ አበባም አስተዳደር ይህንኑ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰምቶ ነበር።

በመካከሉ እን ጃዋር ባቀናጁት ተቃውሞ ሳቢያ የኦሮሚያ ክልል የቤት ማከፋፈሉ ስራ እንዲቆም ሲያውጅ ሙሉ በሙሉ ሃምሳ ሺህ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለመውሰድ ይሁን በድርድር የተለየ አቋም ለማራመድ በመግከጫው አለተጠቆመም። ዶክተር አብይ የሚመሩት ፓርቲ የሚመራው የኦሮሚያ መንግስት ይህንናቋም መያዙን ተከትሎ የአዲስ አበባ ክልል የያዘው አቋም ይህ እስከተዘገበት ሰዓት ድረስ አልታወቀም። ጃዋር አዲስ አበባ ከ፩፱፱፭ ዓ.ም በፊት ወደነበራት ቅርጽና ይዞታ እንድትመለስና ይህ ከሆነ በሁዋላ ድርድር ሊደረገ እንደሚችል አመልክቷል።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

ፋና ይህንን ዘግቧ

በአዲስ አበባና ኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ መተላለፋቸው ተገቢ አደለም- የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባና በኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለባለ አድለኞች መተላለፋቸው ተገቢ አለመሆኑን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገለፀ።

የክልሉ መንግስት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ባወጣው መግለጫ የኦሮሚያ ክልል ጥያቄ እያነሳባቸው ባሉና የክልሉን ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ሂደት እንዳይተገበርም አቋም መያዙን ነው የገለፀው።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሁሉም አቅጣጫ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ደረጃ በደረጃ እየሰራ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫው አንስቷል።

በዚህም ትላልቅ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ነው መግለጫው የጠቆመው።

የአዲስ አበባ ጉዳይም ይሁን ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች በሙሉ በቅደም ተከተላቸው መልስ እንዲያገኙ በተሃድሶ ከስምምነት ላይ የተደረሰበት መሆኑን በማንሳትም ይህም እየተሰራበት መሆኑን ነው ገልጿል።

በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ ጉዳይ አልባት እስከሚያገኝ የኦሮሚያ ክልልን ጥያቄ እያነሳባቸው ያሉ የክልሉን ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች በእጣ ማስተላለፍ ትክክል እንዳልሆነ የክልሉ መንግስት ያምናልም ነው ያለው።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

በመሆኑም ይህ ውሳኔ ስራ ላይ እንዳይውል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጠንካራ አቋም መያዙን በመግለፅ፥ ይህ አቋም በቀዳሚነት የህዝቡን ተጠቃሚነት በማስጠበቅ የመነጨ እንጂ የሀገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች አብሮ የመኖር እሴት ከመጥላት የመነጨ አለመሆኑ ከግንዛቤ ሊገባ ይገባልም ብሏል።

የክልሉ መንግስት ከአዲስ አበባ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ማንኛውንም አጀንዳዎችን እና ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንደሚመለከተውም ነው በመግለጫው ያስታወቀው።

በአዲስ አበባን እና በዙሪያዋ ተያይዘው የሚከናወኑ ስራዎች ከክልሉ መንግስትና ህዝብ እውቅና ውጪ ለመስራት መታቀዳቸው ህጋዊ ነው ብሎ እንደማያምንም አስታውቋል።

“ትናንት ከህዝብ ጋር የታገልነው የህዝቡን ችግሮች ለመቅረፍ እና ህዝቡን ወደ ተሻለ ብልፅግና ለማሸጋገር ነው ያለው መግለጫው፥ ዛሬም ቢሆን ትናንት ለህዝቡ ቃል የገባናቸውን ድሎች እያስመዘገብን መተናል፤ ይህንንም በማስቀጠል ማንኛውንም የህዝብ ጥያቄ በትግል ለማስመለስ አስፈላጊውን መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን” ብሏል የክልሉ መንግስት።

የኦሮሞ እና የኦሮሚያ መብትና ጥቅምን በማስከበር ወደተሻለ ብልፅግና ለማሸጋገር እንሰራለን በማልትም ለዚህም በህጋዊ መንገድ እንሰራለንም ነው ያለው።

በአዲስ አበባ ጉዳይም ከወሰንና ቤቶች ጉዳይ በዘለለ የከተማዋን የኦሮሞ ባለቤትነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብሏል የክልሉ መንግስት በመግለጫው።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0