“Our true nationality is mankind.”H.G.

ዶክተር አምባቸው መኮነንን ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ልዩ ልዩ ሽመቶችን በመስጠትና ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ ዶክተር አምባቸው መኮነንን ርዕሰ መስተዳድር እና አቶ ምግባሩ ከበደን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አድርጎ ነው የሾመው፡፡

ከልዩ ልዩ ሹመቶች በተጨማሪ የተለያዩ አዋጆችንም አጽድቋል፡፡

አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው ደግሞ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ዶክተር አምባቸው መኮነን ለርዕሰ መስተዳድርነት በዕጩነት ሲቀርቡ በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ የቀረበ የሥራ ልምዳቸውና ግለታሪካቸው፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 29/2011 ዓ.ም (አብመድ)

ዶክተር አምባቸው መኮነን ሲሳይ

ብሔር፡- አማራ

ዕድሜ፡- 48

የትምህርት ዝግጅት

ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ

ሁለተኛ ድግሪ፡- ኤም ኤ በፐብሊክ ፖሊሲ እና ኢኮኖሚክስ በደቡብ ኮሪያ ከሚገኘው ኬ ዲ አይ ስኩል ኦፍ ፐብሊክ ፖሊሲ ኤንድ ማኔጅመንት

ኤም ኤስ ሲ በዓለም አቀፍ ፋይናስ እና ኢኮኖሚ ልማት በእንግሊዝ ሀገር ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኬንት

ሦስተኛ ድግሪ (ፒ ኤች ዲ) በኢኮኖሚክስ ሙያ እንግሊዝ ሀገር በሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኬንት አጠናቀዋል፡፡

ዶክተር አንባቸው መኮነን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ የሕዝብ እና የመንግሥት ሥራዎች ከወረዳ እስከ ፌደራል በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል፡፡ አገልግሎት ከሰጡባቸው ዋና ዋና መስኮች ውስጥም፡-

1. በአማራ ክልል የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር በመሆን ከወረዳ እስከ ክልል ባሉ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚሠሩ አመራሮችን እና ባለሙያዎችን በተለያዩ የሙያ መስኮች እንዲሰለጥኑ እና አቅም እንዲፈጥሩ የማድረግ ተልዕኮን በመወጣት አመርቂ ውጤት አሳይተዋል፡፡

2. የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃለፊ በመሆን በደረጃው የሚገኙት የድርጅቱ ጽሕፈት ቤቶች በዘማናዊ አሠራሮች እንዲደገፉ በማድረግ እና ሥራዎችን በመከታተል ችግሮች እንዲለዩ እና ለአመራሩ ቀርበው እንዲፈቱ የበኩላቸውን ድርሻ አበርክተዋል፡፡

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝቷል

3. ለአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር በመሆን በሠሩባቸው ሁለት ዓመታትም ድኅነትን ለመቀነስ እና ጥሪት ለመፍጠር በተቀረጹ የተፈጥሮ ሀብት ልማት፣ የግብርና ልማት፣ የመጠጥ ውኃ እና የመስኖ ውሃ ልማት ፕሮጀክቶች፣ በወጣቶች ዙሪያ በሥራ ዕድል ፈጠራ እና በኤች አይ ቪ (ኤዲስ) መካከል ላይ አተኩረው በተከናወኑት ውጤታማ አፈጻጸሞች ላይ የመሪነት ሥራ ተውጥተዋል፡፡

4. በተለያዩ ጊዜያትም የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃለፊ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደረጃ የኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆነ የክልሉ የኢንቭስትመንት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ልማት ሥራዎች እንዲስፋፉ በማድረግ በመሪነት ተሳትፈዋል፡፡ በዚሁ ወቅትም የኢንቭሰትመንት መሬት እና የኢንዱስትሪ መንደሮች ተዘጋጅተው ለአልሚዎች እንዲተላለፉ እና ወደ ሥራ እንዲገቡ እንዲሁም በክልሉ በሜትሮፖሊታን እሰከ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ባሉ ከተሞች የቤት መሥሪያ ቦታ በሰፊው ተዘጋጅቶ በርካታ ዜጎች ለተደራጁባቸው ማኅበራት እንዲተላለፉ እና ቤቶቹም እንዲገነቡ በማድረግ እና የመሬት ሀብትን ከሕገ-ወጥ ወረራ በመጠበቅ ወደ ሥራ ሳይገቡ ለረጅም ዓመታት ታጥረው የተቀመጡ የኢንቨስትመንት መሬቶችን ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ እና ለሌላ አልሚ እንዲተላለፉ በማድረግ፣ የከተማ ነባር ይዞታዎችን በማጣራት ውሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ እና በሌሎችም የሥራ መስኮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ተወጥተዋል፡፡

5. ከመስከረም 25/2008ዓ.ም እስከ ጥቅምት 21/2009 ዓ.ም በኢፌደሪ መንግስት የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በዚህም ወቅት መሥሪያ ቤቱን እንደ አዲስ ከማቋቋምና ከማደራጀት ሥራዎች ጎን ለጎን የአገራችንን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ቆልፈው በያዙት ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ላይ ከሚመለከታቸው የኢንዱስትሪው ተዋንያኖች ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ደረጃ በደረጃ ሊፈቱ የሚችሉባቸውን የአቅም ግንባታ አማራጮች በተደራጀ አግባብ በማቅረብ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ሬጉሌሽን ሥራው በጠራ መረጃ ላይ እንዲመሠረት፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደገፍና የውስና ተግባር እንዲገታ ለማድረግ ውጤታማ ሥራ ሠርተዋል፡፡

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

6. ከጥቅምት 22/2009 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2010 ዓም ድረስ በኢፌዴሪ መንግሥት የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በሥርዓት እንዲመራ አመርቂ አመራር በመስጠት እንዲሁም ከተሞቻችን በፕላን የሚመሩ ለኑሮ እና ለስራ የሚመቹ፣ ንጹህ፣ ውብ እና አረንጓዴ የምርት እና የግብይት እንዲሁም የጉብኝት ማዕከላት ሆነው የዙሪያቸውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት የማድራት ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ በከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና፣ በከተማ ፕላን ዝግጅት እና ትግበራ፣ በከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት፣ በቤቶች ልማት፣ በመሠረተ ልማት አቅርቦት በከተሞች ገቢ ማሻሻያ እና ፈንድ ‹ሞቢላይዜሽን› በከተሞች ጽዳት እና ውበት እንዲሁም በሌሎች የሕዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ መሠረታዊ የከተማ ልማት ሥራዎች ላይ በማተኮር አመራር ሰጥተዋል፡፡

7. ከግንቦት 2010 ዓ.ም እስከ ሕዳር 2011 ዓ.ም ድረስ በኢፌዴሪ መንግሥት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

8. ከሕዳር 2011ዓ.ም እስካሁን ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሠረተ ልማት አማካሪ ሚኒስትር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

9. በፖለቲካው መስክም ከ1982 ዓ.ም ጀምሮ የያኔው ብአዴን እና የአሁኑ አዴፓ አባል ሆነው በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች የሠሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ዶክተር አምባቸው በአካዳሚክ ዘርፍ የምርምር ሥራዎችን በሕትመት ጆርናሎች፤ 1 የምርምር ሥራ በኤሌክትሮኒክ ጆርናልና 2. ሥራዎቻቸውን በፕሮሲዲንግስ ላይ ያሳተሙ ሲሆን የማስተርስ ትምህርታቸውን የተከታተሉበት በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ‹ኬ ዲ አይ ስኩል ኦፍ ፐፕሊክ ፖሊሲ ኤንድ ማኔጅመንት› በመባል የሚታወቀው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የቀድሞ ተማሪዎች ኅብረትም በትምህርታቸው እና በሥራቸው ባስመዘገቧቸው ውጤቶች እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የ2016 የዓመቱ ተሸላሚ አድርጎ ሸልሟቸዋል፡፡

በክልላችን ብሎም በሀገራችን የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ ጥልቀት እንዲኖረውና ዘላቂነቱም እንዲረጋገጥ የትግል መድረኩ ለሚጠይቀው ደረጃ የሚመጥን አዲስ ጉልበትና ተነሳሽነት ያለው አመራር ያስፈልጋል፡፡ ዶክተር አምባቸው መኮንን አዳዲስ የለውጥ ሐሳቦችን በማመንጨትና በማስተግበር፣ በዚህ ወቅት ክልሉ እያጋጠመው ያለውን ፈተና ሁሉ በመታል በጽናት ማለፍ የሚችል አመራር በመገንባት የአማራ ሕዝብ ችግሮች እንዲፈቱ የመታገል ድፍረትና ዝግጁነት ያላቸው የለውጥ አመራር እንደሆኑ ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡ ወቅቱ አዲስ ጉልበትና ተነሳሽነት ያላቸውን ኃይሎች የምናሰባስብበት እንጅ ያልንን ኃይል የምናባክንበት አይደለም፡፡ ዶክተር አምባቸው ያላቸውን እምቅ አቅም ለሕዝብ ጥቅማ ማዋል የሚችሉበት ትክክለኛ ጊዜ አሁን ነው፡፡

ስለሆነም ያላቸውን የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ውጤት እንዲሁም ለውጡን ለማስቀጠል ያላቸውን የፀና አቋም መሠረት መሠረት በማድረግ በተሻሻለው የክልሉ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 59/1 መሠረት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እንዲሠሩ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) በዕጩነት ያቀረባቸው ሲሆን የተከበረው ምክር ቤት ሹመቱን እንዲያጸድቅልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

Source AMMA

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0