“Our true nationality is mankind.”H.G.

ወርቅነህ ገበየሁ  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሶስተኛ ሰው ሆነው ተሾሙ፤ ሹመቱ ትርጉም አለው!!

Related image

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በተባበሩት መንግስታት ሶስተኛ የሃላፊነት እርከን በሆነው የረዳት ዋና ጸሐፊነት የስራ መደብ መሾማቸው ተገለጸ። የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቶሬዝ ዶ/ር ወርቅነህን ገበየሁን በተጠቀሰው ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ መሾማቸውን ይፋ ያደረጉት በትናንትናው ዕለት ነው።

ከ፳፩፱ ጀመሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ዶክተር ወርቅነህ  ይህንን ሹመት ያገኙት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት በአዲስ መልኩ እያደረገች በመሆኗ ነው።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳስታወቀው ተመድ ይህንን የወሰነው ኢትዮጵያ በአፍሪቃ ቀንድ ለምታበረክተውና እያከናወነች ላለው ተግባር እውቅና ለመስጠት ነው።

በተመድ ውስጥ ሶስተኛ ከፍተኛ የስልታን እርከን የሆነው ይህ ሹመት በርካቶችን ያስገረመ ቢሆንም ጉዳዩ በአፍሪቃ ቀንድ ከተያዘው አዲሱ እቅድ አንጻር የሚጠበቅ መሆኑንም ያመለከቱ አሉ። ሃላፊነቱ  አካባቢያዊና አህጉራዊ ሃላፊነት እንዳለባት የሚያመለክት ከመሆኑም በላይ አዲስ የተጀመረው የምስራቅ አፍሪቃ አገራት የትሥሥርና ቀጠናውን የማዋቀር አጀንዳ ቀጣይ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንን ያሳያል።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

ሰፊ ሃላፊነት የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአገር ውስጥ የጽንፈኛ እንቅስቃሴና የሴራ ፖለቲካ እንቅፋት ቢሆንባቸውም በቀጠናው የወሰዱትን ሃላፊነት ስልጣን ከያዙበት ማግስት ጀምሮ በስካት እያከናወኑ እንደሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት እየመሰከሩክላቸው ነው። ዶከተር ወርቅነህ ገበየሁም በጅቡቲና በኤርትራ መካከል ለረዥም ጊዜ የሚያወዛግበውን የይዞታና የድንበር ችግር በሰላማዊ መንገድ  ለመቋጨት የሚቻልበትን አግባብ በማመቻቸት የተጫወቱት ሚና ትልቅ አድናቆት የተቸረው ነው።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ዋና ቢሮውን ናይሮቢ ያደረገውና ከአምስት ሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያስተዳድረው የተመድ ዋና ጽ/ቤትን እንዲመሩ የተሾሙት ዶከተር ወርቅነህ ሹመታቸው  በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለሚመራው የምስራቅ አፍሪካ አዲሱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቁርኝት ታላቅ ድጋፍ ለመስጠት እንዲቻል ታስቦ መሆኑ ስለሹመቱ አስተያየት የሰጡ አመልክተዋል።

የምስራቅ አፍሪቃ ጂኦፖለቲካ እጅግ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ከመሆኑ አንጻር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሶማሌ ክልል አማጺ ሆኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ወደ አገር ቤት እንዲገባ ማድረጋቸው፣ በሶማሌ ክልል የነበረውን የወሮ በላ አስተዳደር ማስወገዳቸው እንዲሁም የሶማሌ ክልል ከጅቡቲ እንዲሁም ከሶማሌ ጋር በደምና በጎሳ የተነካካ ከመሆኑ አንጻር ዙሪያ ገባውን ካሉ አገራት ጋር የጸጥታ ስምምነት ላይ ለመድረስ መቻላቸው እጅግ የተሳካ ድል የማስመዝገብ ያህል ተቆጥሮላቸዋል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ሰሞኑን ደግሞ ከደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራና ሶማሌ ጋር የተደረሰው የድህንነትና የኢኮኖሚ ጉድኝት ስምምነት፣ ኬንያንና ሶማሌያን ማግባባታቸው፣ አሜሪካ ሙሉ ቀልቧን ሰጥታ፣ አምባሳደር ያማማቶን ሶማሌ መድባ እየከወነች ያለውን አዲሱን የምስራቅ አፍሪቃ ፖሊስ ጉዞ ስኬት የሚያሳይ እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህም በላይ ዶክተር ወርቅነህ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ሰፊ ተሞክሮና ልምድ ስላላቸው ሹመት ትርጉሙ ከፍተኛ ነው።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0