” እናቴ ክርስቲያን ናት፣ ሚስቴ ፕሮቴስታንት ናት አባቴ ሙስሊም ነው። ሰው ወደደኝ አልወደደኝ ችግር የለውም። እኔ ለአገሪቱ ምን እንደሰራሁ ወደፊት ይታወቃል። …. የእኔን አክቲቪስት …. ስልጣን ብፈልግ እጄ ላይ ነው። ዴሞክራሲ ለመገንባት ሚኒስትር መሆን የለበኝም። መታሰር አልፈልግም። ሚኒስትርነትም ይደብረኛል። ነጻ ሆኜ መስራት ነው የምፈልገው… ይህን የማደርገው ቢበዛ ሁለት ዓመት ነው። ከዛ በሁዋላ ኢንስቲቲዩት ከፍቼ ማስተማር ነው የምፈልገው …”  ጃዋር 

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው ጃዋር መሐመድና ለጊዜው ስማቸውን መጥቀስ አግባብ ያልሆነ ሶስት ግለሰቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ ክስ ሊመሰረትባቸው ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ስለመሆኑ ተሰማ። አካሄዱ መላውን የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ቀውስ ላይ የሚጥል በመሆኑ ታላላቅ አገራትን አሳስቧል።

የዲፕሎማቲክ ምንጮቻቸውን በመጥቀስ ለዛጎል መረጃ የሰጡ እንዳሉት የዓለም ታላላቅ አገራት ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለውን ሁሉ በቅርበት እየተከታተሉ ሰለሚገኙ ለጊዜው አራት የሚሆኑ ሰዎችን ሕዝብን በሕዝብ በማነሳሳትና እልቂት እንዲፈጸም ቀደም ጀመሮ ሲካሂዱት የነበረው ቅስቀሳ በመረጃነት ተሰብስቧል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ለሚፈልጉት አካልና የህብረተሰብ ክፍል በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ መታገል አግባብ እንደሆነ የሚታመን መሆኑን፣ የአገሪቱም ህግ ሆነ የዓለም አቀፍ ህግ ይህንኑ እንደሚያረጋግጥ ያመለከቱት የዜናው ምንጭ፣ ” በተለያዩ ጊዜያት ህይወታቸው ያለፈ፣ የተፈናቀሉ፣ የተሰደዱ…. የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ይህ እንዲከናወን በግልጽና በስውር የሚተላለፉ ትዕዛዞች በመረጃነት ተሰብስበዋል” ሲሉ አስታውቀዋል።

ክሱ መቼ እንደሚጀመርና እንዴት እንደሚተገበር ተጠይቀው ማብራሪያ ያልሰጡት ምንጭ ” ጉዳዩ ትልቅ ነው። ከዚህ በላይ ማለት አይቻልም” ማለታቸውን አመልክቷል።

በተያያዘ ዜና የኢጋድ አገሮችም ስጋታቸውን በመግለጽ መረጃ በመቀያየር ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። የአፍሪካ ህብረትም ጉዳዩን እያጤነውና በኢትዮጵያ ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት የሚደረገውን ሩጫ ከማውገዝም አልፎ ፖለቲካዊ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ግምት እንዳላቸው ምንጩ ተናግረዋል። አዲስ አበባን ታላቅ ያሰኟት የዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ነገሮች በዚህ ከቀጠሉ የራሳቸውን ውሳኔ ሊወስኑ እንደሚችሉ፣ ይህም ታላቂቱን አገር መልሶ ሊያኮስሳት እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ከጃዋር በተጨማሪ ሶስቱ ሰዎች እነማን እንደሆኑ በስም ያልጠቀሱት የዜናው ባለቤት፣ አንድ የሚዲያ ባለሙያ እንደሚገኝበት ግን ጠቁመዋል። ጃዋር እንዲከሰስ ፒቴሽን ሲሰባሰብ የቆየ ቢሆንም የአሁኑ ክስ ከዛ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ታውቋል።

በተደጋጋሚ ጊዜ ስለመከሰስ ሲነሳ የሚያጣጥለው ጃዋርን ለማግኘትና አስተያየቱን ለማከል አልቻልንም። ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት ህግና ስርዓት አክብሮ እንደሚሰራ፣ የሚያስፈራው አንዳችም ነገር እንደሌለ በድፍረት መልስ መስጠቱ የሚታወስ ነው። የአሜሪካ ዜግነት ያለው ጃዋር አገሪቱን የመምራት ሃሳብ እንዳለውም ከአንዳንድ ወገኖች እየተሰማ ነው። ዜናውን አስመልክቶ ጃዋር ማንኛውንም የመቃወሚያ አስተያየት የምናትም መሆናችንን እናስታውቃለን።

ይህንን ዜና አስመልክቶ አስተያየት የጠየቅናቸው ባለሙያ ” ጃዋር ከኦዴፓ ጋር አብሮ የሚሰራ ከሆነ ሁሉንም ጉዳይ በዝግ መቸረስ መልመድ ይገባዋል። ሁሉንም ጉዳይ አደባባይ እያወጣ ከተማና አገር እንዲናጥ ማድረጉ በራሱ ህገወጥ ነው። ቆንጨራና ዱላ በማስያዝ አንዱ ሌላውን እንዲያስፈራራ ማደራጀትና ማዘዝ፣ ይህንኑ ቆንጨራና የስለት መሳሪያ በሚዲያ እያሰራጩ ሌሎችን ማሸማቀቅ በህግ ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ጃዋር በርካታ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚያስወነጅሉ ጉዳዮችን ያከናወነ ቢሆንም፣ የሚገርመው ይህንን ሁሉ እያከናወነ ከመንግስት ጋር እሰራለሁ ማለቱ ነው” ብለዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በማርች ስምንት የሴቶች ቀን ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቀጥታም በይሆን ይህንን ስጋት አውስተዋል። ” ልንሰበስበው ወደማንችለው ችግር እንገባለን” ሲሉ።

የሚናገሩበትን ማይክራፎን በጣታቸው መታ መታ አደርገው ” አሁን የስማችሁት ድምጽ ከባድ ድምጽ ሆኖ ሳይሆን፣ ጸጥ በማለታችሁ ነው የሰማችሁት” ያሉት ዶክተር አብይ የአብዛኞች ዝምታ ጥቂቶች እንዲደመጡ ማድረጉን፣ ይህ አካሄድ አደገኛ በመሆኑ ዝምታን በማቆም አገራቸንን እንታደግ ሲሉ ተሰምተዋል። በመጨረሻም ” ኢትዮጵያ አትፈርስም” ሲሉ ንግግራቸውን ቸርሰዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *