“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኦነግ ወታደሮች የረሃብ አድማ ጀመሩ ፤ ” የጎልደለባቸው ነገር የለም ለጉብኝት ክፍት ነው”

ከሰላማዊውን ትግል ጎን ለጎን የትጥቅ ትግል ጀምሮ የነበረውና በርካታ ህጽናትን ለጦርነት መልምሎ ያሰማራው ኦነግ ሸኔ፣ በአደራዳሪዎች ስምምነት ትጥቅ ፈቶ ወደ ማሰልጠኛ መግባቱ የሚታወስ ነው። ከተከፋፈለው ኦነግ ውስጥ በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ሸኔ አሁንም የሰላም ድርድሩን ባለመቀበል ጫካ ያሉ ወታደሮች አሉት። ቢቢሲ የአማርናው ክፍል በተደጋጋሚ የሚያነጋግረው መሮ ይህንኑ እጅ ሰጥቼ ወደ ካምፕ አልገባም ያለውን ክንፍ እንደሚመራውም የሚታወቅ ነው።

ሌሎቹ ከኦነግ ሸኔ የወጡት አመራሮች የየራሳቸውን ኦነግ ክንፍ እየመሩ በሰላማዊ ትግል እየተንቀሳቀሱ ባለበት፣ ፍትሃዊ ምርጫ በሚጠበቅበት ውቅት ዳውድ ኢብሳ መሐል አገር ተቀምጠው ግማሽ ጎናቸው ጫካ መሆኑ እጅግ አስገራሚና አስደናቂ የነበረ ጉዳይ ቢሆንም፣ መንግስት ክልሉ ባደረገለት የእርዳታ ጥሪ አማካይነት መከላከያ በምስጋባት አካባቢውን ከተቆጣጠረ በሁዋላ ሽምግልና መቀበላቸውን ሰለ ሂደቱ የሚያውቁ ይናገራሉ።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

አባ ገዳዎች፣ አደ ስንቄዎች፣ አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ፖለቲከኞች ጣልቃ ገብተው አንድ ሺህ ፫፻ የሚጠጉ ታጣቂ የሸኔ ወታደሮች ወደ ካምፕ ገብተው ነበር። ዛሬ ቢቢሲ ስም ሳይተቅስ በደፈናው ትጥቅ የፈቱት የሸኔ ሃይሎች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። አቶ በቀለ የተባለውን ለማጣራት የጉብኝት ፈቃድ ከመንግስት እየጠበቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ  “መንግስት የገባውን ቃል በአንድ ጀንበር መፈጸም አይችልም። ቢሆንም እንደ አንድ ሰልጣኝ ወታደር የጎደለባቸው ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። ኦነግ ሸኔ በይፋ አንድም ነገር ሳይናገር በጓሮ በተባራሪ የሚወራው ዜና ዓላማው ሌላ ነው፤ ሁሉንም ጉዳይ ህዝብ እንዲፈርደው የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው። በርግጥም ቻካ እያሉ እንደሚያደርጉት በየቀኑ ሰንጋ፣ ሙክት፣ እንደሌለ እናውቃለን” ብለዋል። ከታች የቢቢሲ ዘገባ ያንብቡ

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

በአባ ገዳዎች ማግባባት ትጥቅ ፈትተው ወደተዘጋጀላቸው መጠለያ የገቡና አንድ ሺህ የሚሆኑ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ወታደሮች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ገለፁ።

በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙት እነዚህ የቀድሞ የኦነግ ወታደሮች በካምፑ ለአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ መጋለጣቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አንድ የቀድሞ የኦነግ ወታደር “የተያዝንበት ሁኔታ በጣም አስከፊ ነው። ብዙ ጓደኞቻችን በምግብ እጥረትና በንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት ችግር ታመዋል” ሲል ሁኔታውን ለቢቢሲ ገልጿል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ከዚህም በተጨማሪ በቀጣይ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ይመለሱ ዘንድ ይሰጣችኋል የተባለው ስልጠናም ሆነ ሌሎች የተገቡላቸው ቃሎች አለመፈፀማቸውን ገልፀዋል።

የኦነግ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ ኦነግን እና መንግስትን ሲያሸማግል የነበረው ኮሚቴ አባል የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው አቶ በቀለ ገርባ ወታደሮቹ ችግሮች እንዳሉባቸው የሰሙ ቢሆንም በካምፑ ያሉበትን ሁኔታ ለመመልከት የክልሉን መንግሥት ፍቃድ እየጠበቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን የክልሉ ሃላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0