ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ብሄራዊ ስሜታቸው፣ አገርን አንድ አድርገው ለመምራት መነሳታቸው፣ ኢትዮጵያዊነትን መስበካቸው፣ ከአንድነት ሃይሎች ጋር አብረው መስራታቸው፣ ኢትዮጵያ አትከስምም በሚል መርሃ መነሳታቸው በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ጽንፈኛ ድርጅቶች አልወደዱላቸውም። እንደውም ገና ሳይደራጁና ሳይቆሙ ግፋ ቢል በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ፈንግሎ ለመጣል የተጀመረው ሩጫ መዳረሻው በድፍን ኦሮሚያ አመጽ መጥራትና ከልጣን እንዲወርዱ መጠየቅ ነው። ከዛም አክራሪው ሃይል ኦሮሚያን ይረከባል። ይህ እቅድ ጃዋር ተዘግጅቼበታለሁ በሚል ከሚናገረው አንዱ ነው። ሌላው አዲስ አበባን ዙሪያዋን ዘግቶ በማስራብና በቆሻሻ በማጀል መንግስትን ማስወገድ ይሆናል።

———————————————————————————————————–

ጃዋር መሐመድ ” አንገት በሜንጫ እንቆርጣለን” ሲል ለይቶ ሌላውን ብሄር ሳይሆን ዛሬ የሚምለበትንም የኦሮሞ ክርስቲያን ህዝብ ጭምር ነው። ጃዋር በኢትዮጵያ የስልምና እምነት ተከታዮችን ጆሮና ቀልብ አጣ እንጂ አሳቡ ያ ነበር። ለዚሁም ተግባሩ ለዛሬ መነሻ የሆነውን ድጋፍና እርዳታ ከአላማ ወዳጆቹ አግኝቷል።  ለዚህም የቀድሞውም ሆነ የአሁኑ ኢህአዴግ በቂ መረጃ አላቸው። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ይፋ መሆኑ አይቀርም።

በስድስት ወር ጊዜ ወስጥ አፈናጥረን እንጥለዋለን

ሲነጋና ሲመሽ ውል አስሮ የማይናገረው ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በአገር ቤት ህግ ክስ የሚጠብቀው ጃዋር ዛሬ አገር ቤት ገብቶ አገር የሚያተራምሰውና ህዝብ ከሕዝብ ጋር እንዲጋጭ መመሪያ የሚያራባው በትግሉ ወቅት ኦህዴድ ፈቅዶለት በዘረጋው መረብ ተማምኖ እንጂ ሌላ የረባ ጥንካሬ ኖሮት አይደለም። የቀድሞውን የአንድ ለአምስት ጥርነፋ  ከቀበሌ ጀምሮ በመበጣጠስ ህወሃት የሚመራውን የድህንነት ተቋም መረጃ እንዲመክንበት ሲደረግ ኦህዴድ ባይፈቅድ ኖሮ የሚታሰበም አልነበረም። ራሱ ጃዋር በተደጋጋሚ ከኦህዴድ ጋር አብሮ እንደሚሰራ ሲገልጽ በተዘዋዋሪ ይህንን ማመኑ ነው።

መረጃ ከመስጠት ጀምሮ፣ እሱ እንዲያሰራጫቸው የሚፈለጉ መረጃዎች ሲበተኑ በማሰራጨት ኦህዴድ ያጀገነው ጃዋር ዶክተር አብይ ላይ ነጥሎ ዘመቻ የጀመረው ገና ወደ ስልጣን የመምጣታቸው ጉዳይ ሲሰማ ነው። ” የዶክተር አብይን ጠቅላይ ሚኒስትርነት አንፈልግም፣ አንቀበልም” በማለት በገሃድ ሲቃወም የተደመጠው ጃዋር፣ አብይ አህመድ ከተመርጡ በሁዋላም ቢሆን እግር እገራቸውን እየተከተለ ሊያሳጣቸው ሲሯሯጥ ማየት የተለመደ ነው።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

ዶክተር አብይ ገና ወደ ሃላፊነቱ እንደመጡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተቀባይነት በማግኘታቸው የተላዘበ የመሰለው ጃዋር፣ መርዙን ግን አልተፋውም ነበር። የቅርብ ሰዎቹ እንዳጫወቱኝ ጃዋር በየቀኑ የአብይን ስም እየጠራ ይዝታል። ዛቻው ደግሞ ” አሽቀነጥረዋለሁ” በሚል ነው። ለለማ መገርሳ ክብር እንዳለው በተደጋጋሚ የሚናገረው ጃዋር፣ ዶከተር አብይ አገር የመምራት ብቃት እነደሌላቸውም መተቸት የለት ተዕለት ተግባሩ ነው።

” ከግራኝ መሐመድ በሁዋላ የመጀመሪያው ተጸኖ ፈጣሪ ነኝ ” እያለ ራሱን የሚገልጸው ጃዋር ለይቶ ዶክተር አብይን መጥመዱ ከምን መነሻ እንደሆነ አድፍጬ ስከታተል ነበር። ባለኝ የሃላፊነት መድረክ በማውቃቸው የቅርብ ሰዎቹ አማካይነት ከሶስት ሳምንት በፊት የሚከተለውን አረጋግጫለሁ።

በቅርቡ በአንድ ንግግራቸው ዶከተር አብይ ” ይህን መንግስት በሶስት ወር አሽቀንጥረን እንጥለዋለን” ተብሎ እቅድ መያዙን መግለጻቸው እንዳለ ሆኖ፣ የእነ ጃዋር እቅድ ግን ስድስት ወር ነው። ጃዋር ፍጹም ከማይቀበሉት የኦነግ ሰዎች ጋር እቅዱን ሊያሳካ ስለማይቻለውና የቆየ ጸብ ከኦነግ አመራሮች ጋር ስላለው የኦነግ ወታደሮች እጃቸውን ሰጥተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ በማያገባው ጉዳይ ገብቶ ሲጣደፍ የከረመውም ለዚህ ተግባሩ መንገድ ላመቻቸት ነው።

ኤርትራ ከትመው የነበሩትን የኦነግ አመራሮች ጥምብር ኩሳቸውን እያወጣ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ለመለየት ከፍተኛ የሚዲያ ዘመቻ በማደረጉ፣ አመራሮቹን ሲዘልፍና ክብራቸውን በሚነካ መልኩ ሲያዋርዳቸው ሰለኖረ እነሱን ተጠግቶ ድብቅ አላማውን ማስፈጸም አይችልም፣ በመሆኑም  እነሱን ከፖለቲካው ገበያ ለማጥፋት ይረዳው ዘንደ ሳይጠራ አባ ገዳዎች ጀርባ አቶ በቀለ ገርባን አስከትሎ ደፋ ቀና አለ።

የኦነግ ጉዳይ ሲባረድ ጃዋር ምክንያት ሲፈልግ ነበርና የኮንዶሚኒየም እደላውን ተንተርሶ ድፍን ኦሮሚያን ለምሳመጽ እድል አገኘ። ለማ መገርሳን ለይቶ በማድነቅ ባስነሳው በቆንጨራና በዱላ የታጀበ አመጽ አመካኝቶ ዶክተር አብይ የሚመሩትን ፓርቲ ናጠው።የኦሮሚያ ክልል አቋሙን ይፋ አድርጎ ድርድር እንዲደረግ ከጠየቀ በሁዋላም አመጹንና ቆንጨራውን ገፋበት። ጉዳዩ የኮንዶሚኒየም ሳይሆን ነጥሎ አብይ አህመድን ለማጥፋት ያቀደውን ሴራ እንዴት እነሚሳካ ሙከራ የተደረገበት መሆኑ ነው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ይህ ሁሉ የሚሆነው እንዴት ነው ? ለምድን ነው ? 

ከሶስት ሳምንት በፊት ጃዋር ለወዳጆቹ ሚስጢሩን በመጠኑም ቢሆን በተባራሪ እንዲወራ አስቦ ፍንጭ ቢጤ እየሰጠ ነው። ከአንደበቱ የሰሙ እንደሚሉት ጃዋር በቅርቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል። አሁን በወሬ ድወረጃ እንዲሰራጭ ያደረገው በሁዋላ ላይ ዱብ እዳ እንዳይሆን አስቦ ሲሆን፣ ይህ ካልተሳካ ኦሮሚያን ይመራል። ቄሮ ምርጫውን ይታዘባል ሲል የተደመጠውም ይህንኑ አመላካች ነው።

የገንዘብና የሚዲያ ችግር የሌለበት ጃዋር ምርጫውን በዱላና በቆንጨራ እጁ ውስጥ እንደሚያስገባ ያምናል። ለዚህም ማስረጃው ምርጫው አንድም ቀነ ሊራዘመ አይገባም፣ የሽግግር መንግስት መቋቋም የለበትም፣ አሁን ያለው የሽግግር መንግስት ነው፣ ይህ መንግስት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማንዴት የለውም፣ ህዝብ ስላልመረጠው ታማኝነት የለውም፣…. የሚሉ ጉዳዮችን በተደጋጋሚ የሚያነሳውም ከዚህ ህልሙ በመነጨ ነው።

በለውጡ ማግስት የጠበቀውን ያላገኘው ጃዋር፣ በዚሁ ምክንያት በዶክተር አብይ ላይ ጥላቻ ማሳደሩ እኔን ጨመሮ በርካቶች እናውቃለን። እንደውም ጀርባው በውሉ ስለሚታወቅ ብዙም ቀልብ ያላገኘው ጃዋር ዶክተር አብይ እስካልተወገዱ ድረስ ስፍራ እንደማይኖረው ሙሉ በሙሉ በማመኑ ሁለት እቅዶችን ይዟል።

እቅድ አንድ – ቄሮን ፓርቲ ማድረግ

ኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎችን አቀናጅቶ ግዙፍ ፓርቲ ከሆነ በድምጽ መንግስት የመሆን አቅም ስላለው ከወዲሁ አመጹን መግፋቱ የጃዋርና የስውር አጀንዳው አራማጆች ፍላጎት ነው። የስልጣን ፋላጎት እንደሌለው ዘወትር የሚናገረው ጃዋር በሸዋ ውስጥ ብዙ ተቀባይነት ስለሌለውና የጀነራል ሃይሉ ጎንፋና የፕሮፌሰር መረራ  ድርጅቶች ሰፊ ተቀባይነት ስላላቸው አሁን አዲስ አበባ ዙሪያ የሚሯሯጠው ድጋፍ ለማግኘትና ሸዋ ላይ አሻራውን ለመጣል ነው።

በቅርብ ዘመዱ ስም የተመዘገበው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክን በወጉ በመጠቀም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚሮጠው ጃዋር ከዓለም ጌቶች እይታም ሩቅ እንዳልሆነ በርካቶች እሱን ጨምሮ የሚያውቁት ሃቅ ነው። ይህ ጉዳይ ወደፊት የምመለስበት ይሆናል። ወደ ዋናው ነገሬ ስመለስ አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ ዶክተር መረራ ጉዲና፣ ገላሳ ዲልቦ፣ ሊንጮ ለታ እና ሌሎች አንጋፋዎቹ ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካው ሜዳ መወገድ አለባቸው የሚል እቅድ የያዘው ጃዋር ቄሮን ወደ ፓርቲ ለመቀየር እየሰራ መሆኑንን የምናውቅ እናውቃለን።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

በተመሳሳይ የመካከለኛ ኦሮሚያ ተወላጆችን ወደ አንድ መድረክ የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ ምንም እንኳን ሚዲያ አልባ ቢሆኑም በውስጥ ለውስጥ የዘረጉት አደረጃጀት ለጃዋር እቅድ እንቅፋት ሆኖበታል። ከማክረርና ጎሳ ከመቁጠር የራቀ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ እንቅስቃሴ እግሩ ሁሉም ስፍራ በመኖሩ ጃዋር ሊቋቋመው እንደማይችል እሙን ነው። ስለዚህ በጊዜ ሂደት ሳይሆን በግርግር አብይ አህመድን ለማስወገድ የሚደረገው ዘመቻ ፣ ቄሮን ወደ ፓርቲ አደረጃጀት ቀይሮ የሚገኘውን ድል ጃዋር የሚጠብቀውን ያህል ስለማይሆን ነው። ምርጫው አይራዘምም የሚባለው ትርክት መነሻም ይኸው ነው። ለውጡን አጣድፎና አርገብግቦ መብላት!!

እቅድ ሁለት – አክቲቪስትነትና የሚዲያ መሪነትን አጣምሮ የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ በመሆን ማድፈጥ

ጃዋር ከላይ ያለውን ባጭሩ የተቆነጸለ ሂሳብ ስለሚረዳ ከሚዲያ የታማጆር ሹምነት ቆርጦ መልቀቅ አይችልም። ለይቶለት ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ ሚዲያውን ለሌላ ሰው አሳልፎ ለመስጠት የማይወስነውም በዚሁ ስሌት ነው። በርካቶች እንደሚስማሙበት የዶከተር አብይ ፓርቲ ከሌሎች ተሰሚነት አላቸው ከሚባሉ ፓርቲዎች ጋር ውህደት ለመፍጠር እየሰራ በመሆኑ ጠንክሮ ሳይወጣ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ኦዴፓን መብላት የሚቻለው ሚዲያውን በመያዝ ይሆናል።

በዚህ መሰረት ከጀርባ ያለውን ሃይል በማሰማራትና በውል በማይታወቅ ጉዳይ በማሳመጽ የዶከተር አብይን ቅቡልነት ለማሳነስ ጃዋር ኦዴፓ ውስጥ የከተተውን እጁን እየተጠቀመበት ነው። የሚፈልገውን መልዕክት በማሰራጭት፣ የሚቃወሙትን በማሸማቀቅ፣ ኦዴፓን እየናጠው ያለው ጃዋር ኦዴፓን ከሌሎች ፓርዎችና በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ እንዲጠላ አጥብቆ እየሰራ ነው።

በጅምላ ንቅናቄ ኦዴፓን እጅ ለመጠምዘዝ የሚታክተው ጃዋር፣ በዚህ አካሄድ የኦዴፓን ክንድ ለማዛልና ፓርቲውን ሙሉ በሙሉ ከህዝብ ለይቶ ለመቆጣጠር የሚዲያና የአክቲቪስት ኤታማዦር ሹምነቱን ነክሶ ለመያዝ ይገደዳል። አሁን እየሆነ ያለውም ይህ ነው። የመካከለኛ ሸዋ አደረጃጀትን በሚቀጥለው ለውይይትና ለመረጃ ያህል በመጠኑ ፈንጠቅ አደርጋለሁ

 

ዝግጅት ክፍሉ –  ይህ ጽሁፍ የጸሃፊ አመልከካት እንጂ የዝግጅት ክፍሉን አይወክልም!!

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *