“Our true nationality is mankind.”H.G.

«ኬኛና የኛ አካሄድ ያጠፋናል»

የነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነገር. . . አካፋውን አካፋ፤ ዶማውን ዶማ ላለማለት ላም ባልዋለችበት ኩበት ለቀማ. . .

እነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ መጋቢ ሀዲስ አለማየሁ እሸቱ፣ መምህር ሰርፀ ፍሬስብሀት እና ሌሎች ተንታኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አስተማሪዎች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ከሰሞኑ አዲስ አበባ ውስጥ በተዘጋጀ አንድ መድረክ አገራችን እያጋጠማት ያለውን ችግር አስመልክቶ ንግግርና ምክር ሰጥተው ነበር። ሁሉም ተናጋሪዎች የሰጡት ምክረ ሀሳብ እንከን የሚወጣለት አይደለም፤ የሁሉም ተናጋሪዎች ምክረ ሀሳብ አካፋውን አካፋ፣ ዶማውን ዶማ የማለት ድፍረት ከማጣቱ በስተቀር።

ሁሉም ተናጋሪዎች አካፋውን አካፋ ላለማለት «ኬኛና የኛ አካሄድ ያጠፋናል» የሚል ትርክት መርጠዋል። በመሠረቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ኬኛና የኛ የሚል ቡድንተኛነት የለም! ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ቡድንተኛነቶች ኬኛ የሚል ጽንፈኛና የጋራ የሚል አቃፊ ካምፖች ብቻ ናቸው። ኬኛ የሚሉን ምድሩንም ሰማዩንም የኛ የሚሉን የኦሮሞ ብሔርተኞች ሲሆን፤ የጋራ የምንለው ደግሞ ምድሩም ሰማዩም የሁላችን ኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት ነው የምንለው አብዛኛዎቻችን ነን።

በየመረኩ ኢትዮጵያ አገራችን እያጋጠማት ያለውን ችግር መንስዔ አስመልክቶ ሲናገሩ የምንሰማቸው እነ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ፣ መጋቢ ሀዲስ አለማየሁ እሸቱ፣ መምህር ሰርፀ ፍሬስብሀትን ጨምሮ ሌሎች ፖለቲከኞቻችን፣ የሃይማኖት አስተማሪዎቻችን፣ ጋዜጠኞቻችን፣ አክቲቪስቶቻችን፣ ወዘተ. . እያደረጉት ያለው «የጋራ» የምንለው አብዛኛዎቻችንን ምድሩንም ሰማዩንም «ኬኛ» የሚሉት ተቃራኒ አድርገው በመፍጠር «የኛ» የሚል የሌለ ጫፍ ፈጥረው «የጋራ» የምንለውን ባልዋለበት በማዋል፤ የኬኛዎቹ ሌላ ጽንፍ አድርጎ የማቅረብ ዘመቻ እጅግ አሳፋሪ ነው። ሊቆም ይገባዋል! ሰማዩንም ምድሩንም ኬኛ የሚሉትን የኢትዮጵያ ችግር መስንዔዎች ደፍራችሁ መናገር ባትችሉ የሌለ ጽንፍ ወይንም dichotomy ፈጥራችሁ «የጋራ» የምንለውን አብዛኛዎቻችን «የኛ» እንዳልን አድርጋችሁ misrepresent ልታደርጉን ግን ከቶ አትችሉም!

በዓሉ ግርማ «ድፍረት የሌላት ብዕር ወረቀት ባታበላሽ ይመረጣል ከአድር ባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ይናገራልና» ሲል እንደተናገረው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር የሆኑትን ኬኛዎቹን ለይቶ መተቸት ሲሳነን ኬኛዎችን ላለማስቀየም የሌለ «የኛ» የሚል ጽንፍ በመፍጠር ለእኩልነትና ለጋራ አብሮነት እየታገሉ ያሉትን ለማሸማቀቅ ሰማዩንም ምድሩንም ኬኛ ከሚሉ ወሮበሎች ጋር በማወዳደር አዳሪ ለመሆን ከመናገር ዝም ብትሉ ዝምታችሁ ብዙ ይናገራል! ስለዚህ አካፋውን አካፋ የማለት ድፍረቱ ከሌላችሁ ዝም በሉ። ጸጋዬ ገብረ መድኅን «አብረን ዝም እንበል» ያለው አካፋውን አካፋ ማለትን ሳይደፍሩ ለእኩለትና የጋራ አገር የሚታገሉትን ለማሸማቀቅ ሲሉ የውሸት dichotomy መፍጠር ን እንደ መናኘ ስራ የሚቆጥሩ ሰዎች ነውና ትክክለኛው ኅሊናችሁ አንደበታችሁን አብረን ዝም እንበል ሊለው ይገባል!

ባጭሩ እባካሁት «ኬኛ» የሚሉትን የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪዎች ንጹህ ለማድረግ «የኛ» የሚል የሌለ ትርክት ፈጥሯችሁ «የጋራ» የሚለውን አቃፊና አካታች የሀሳብ መስመራችንን በአድርባይነት ጥላሸት አትቀቡት። ከቻላችሁ በኦሮምኛ «ኬኛ» የሚል እንጂ በአማርኛ «የኛ» የሚል ችግር ፈጣሪ ሌላ ጽንፍ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሌላ ማስተካከያ ስሩ። ድፍረቱ ካላችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ምድሩንም ሰማዩንም «ኬኛ» የሚሉ አግላይ ጽንፈኞችና ምድሩም ሰማዩም የጋራ የሚሉ አካታችና አቃፊ እሳቤዎች ብቻ መሆናቸውን፤ ሕዝባችን ከነዚህ የትኛውን መምረጥ እንዳለበት አስተምሩ። አዲስ አበባን «ኬኛ» ሲባል ሰታችኋል። ኅሊና ካላችሁ ጌጀራና ሚስማር የተጠቀጠቀበት አጣና ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ አደረግን እያሉ «ፊንፊኔ ኬኛ» የሚሉ ታከለ ኡማ ከክፍለ ሀገር አምጥቶ መታወቂያ ያደላቸው ባለሜንጫዎችና እና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ወጥተው አዲስ አበባን የጋራችን ናት የሚሉ ሰላማዊ ዜጎችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ እንዲለይ አስተምሩ።

የአገር ጉዳይ የሚያሳስባችሁ ከሆነ ምድሩም ሰማዩም የጋራ የሚለውንና አብሮ መኖርና የጋራ አገር እሳቤን የግል ያደረገውን የአዲስ አበባ ወጣት ሰብስባችሁ ስለ አብሮ መኖርና የጋራ አገር ግንባታ በማስተማር ጊዜ ከምታባክኑ የኢትዮጵያ ችግሮች ምንጭ የሆኑትን ምድሩንም ሰማዩንም «ኬኛ» የሚሉትን አግላይና ጽንፈኛ ወጣቶች ሰብስባችሁ ስለ አብሮ መኖርና የጋራ አገር ግንባታ አስተምሩ። የአዲስ አበባም ሆነ የኢትዮጵያ ችግር በአብሮ መኖርና የጋራ አገር እሳቤ ያደጉት፤ አቃፊና አካታች እሳቤ የያዙት የአዲስ አበባ ልጆች ሳይሆኑ ከክፍለ ሀገር እየመጡ መታወቂያ ታድሏቸው ፊንፊኔ ኬኛ እያሉ ኦሮሞ ያልሆነው አዲስ አበባ ውስጥ እጣን እንኳ የሚያጨሰው እኛ ከፈቀድን ብቻ ነው የሚሉ ቄሮዎች መሆናቸውን በአካል፣ በፎቶና በተንቀሳቃሽ ምስል ያያችሁት እውነት ንገሩ! ይህ በማድረግ በጎ አስተማጽዖዎች ማድረግ ካልቻላችሁ ላም ባልዋለችበት ኩበት አትልቀሙ! ዝም አይነቅዝም!

Achamyelehe Tamiru fb

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0