ብውሸት መዝለቅ ከባድ ነው!! መለስ ከሚማርበት ትምህርት ቤት፣ ካደገበት ቀዬ፣ ከተሰደደበት ጫካ፣ በጠብ መንጃና በኢትዮጵያ ጠላቶች ድጋፍ መሪ ሆኖ ከኖረበት ቤት ውስጥ፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያልዋሸውና ያልጭበረበረው ጉዳይ የለም። ዛሬ ህወሃት ለገጠመው “የሰለጠነ” ሰደት የዳረገው ይኸው የእሱ ክፋትና ተንኮል እንዲሁም ውሸት ክምር ለመሆኑ የሚከራከር የለም።

የሚማር ነበስ ካለው ይማረውና ይህ ክፉ የኢትዮጵያ ጠላት ” የሚጠላውን ህዝብና አገር እንዴት ሊመራ ቻለ” በሚለው ጉዳይ በርካቶች ላይ ጣት መቀሰር ቢቻልም ዛሬ ያ ዘመን አልፏልና አይሆንም። ይሁን ከተባለ መለስን ከብራስልስ መቀስቀስ ይሆናልና ማስተዋል የሚጠይቀው እዚህ ላይ ነው። መለስን ቀስቅሶ ወደ ቀድሞ ቦታው ለመመለስ አብይ አህመድ ላይ የተጀመረው ዘመቻ አንዱ ማሳያ ነው።

መለስ ነብሰ ገዳይ፣ አረመኔ፣ ከሃጂ፣ አገር ቸርቻሪ፣ ለትግል ጓዶቹ የማይተኛ፣ ይጠቅመኛል ካለ ማናቸውንም ዓይነት በማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ላይ ከመፈጸም ወደ ሁዋላ የማይል፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለማክሰም ሌት ከቀን የባከነ፣ ለዚሁ ተግባሩ በግብር ከፋዩ በጀት የሚንቀሳቀሰውን የአገሪቱን ብሄራዊ ሚዲያ ሳይቀር ለጥላቻና ለበቀል መቀስቀሻ ያዋላ፣ ህዝብ እንዲባላ ምስል ያስቆመ፣ አማራን ለይቶ ጠላት በማድረግ በተላላኪዎቹ ግፍን ያራባ፣ ለውሸታምነቱ ተወዳዳሪ የሌለው፣ አገርን ከህዝባቸው ጋር አስጠብቀው ያቆዩትን ጀግኖች የሚጠላ፣ ህጻናት፣ አረጋዊያንና እናቶች በጠራራ ጸሃይ በአልሞ ተኳሾች እንዲደፉ የሚያዝ፣ እጁ፣ ልቡ፣ አዕምሮው፣ ዱካው ሁሉ በደም የጨቀየ የሴጣን ሽንት እርጉም ነበር።

አብረውት የታገሉት እንደመሰከሩት መለስ ላይ የሚጮኸው የንጹሃን ነብስ እጅግ ብዙ ነው። ክህደቱን የታገሉትን በሙሉ የበላ፣ የሚከራከሩትን ሁሉ ያነከት፣ ፓርቲውን በብቸኝነት ያለ ተከራካሪና ተሟጋች ሲዘውር ኖሮ እዳና ድንቁርናን አሸክሞ ድንገት የተስፈተለከ እንግዴ ነው። ይህ ክፉ የዘራው መርዝና አሜካላ አድጎ ፍሬው ሲያፈራ ወደ አመራር የመጡት ዶክተር አብይ ዛሬ ፈተና የሆነባቸው የዚሁ የእርጉም መኸር ነው። ይህንን በሚገባ መረዳት ግድ ነው። መለስ የሚባለው እርጉም አገሪቱን የሰራት እሱ ወይም የሱ ጥንስሶች ሲገፉ አገሪቱ እንደዚህ ነፍራ እንድትበታተን ነው። ይህ እውነት በማኒፌስቶና በሰንድ የተደገፈ፣ ከእንቅልፋቸው በነቁ አበሮቹ ገሃድ የወጣ ሃቅ ነው።

እናም አሁን ላይ የሚታየው ችግር ይህ ለውጥ የወለደው ሳይሆን፣ ለውጡ ሊቀለብሰው የሚገባ ስር የሰደደ የመለስ አሜካላ ነው። ይህንን የመለስ አሜካላ ከህዝብ በመለየት በብልጠትና በማስተዋል ለመቀልበስ ከመትጋት ይልቅ በዚህ አሜካላ የተጠመቀ አምቡላ እንደተጋተ ውይፈን ማበድ የሚጠበቅ አይደለም። ማንም ሆነ ማን አገር ከሌለ ዳራ ቢስ ነው። እዛ አንድጄ እዚህ ቁጭ ብዬ እሞቃለሁ የሚል ከንቱ አስተሳሰብ የትም አያደርስም። ህዝብ እንደ ህዝብ ጠላት ሆኖ አያውቅም። ህዝብና ህዝብ ተጣልተው አያውቁም። አማራና ትግሬን የሚያጣላ ምንም ጉዳይ የለም። ኦሮሞና አማራውንም የሚያቧቅስ ምንም ምክንያት የለም።

በመለስ ደፍድፎ የጠመቅውን የክፋት አምቡላ በፈረሰው አናት ቅሉ እየተጋቱ እዚያና እዚህ ዘራፍ የሚሉ ጠባቦች፣ ዘረኞች፣ አክራሪዎች፣ ዓላማቸው በውል የማይታወቅ የስልጣን ጥመኞችን ህዝብ እና ሰፊው አድፋጭ የህብረተሰብ ክፍል ዞር በሉ ሊል ይገባል። ችግሮችን በር ዘግቶ በውይይት ከመፍታት ይልቅ በየሚዲያው በማስታወክና ሰላማዊ ዜጎች ላይ በመትፋት አገርን ማፈራረስ ነገ ለጸጸት እንኳን አያበቃም። የተተፋውን ሁሉ በማሰራጨት የዩቲዩብና የሳይበር ገበያ ማሻቀጥ ቀን ሲያልፍ የጸጸት መጽናኛ አይሆንም። መልካም ነገርን መቀያየርና መማማር እየተቻለ ለሳንቲም ለቀማ የሴራ ፖለቲካን ምስኪን ታዳጊዎች፣ እናቶችና አባቶች ላይ መድፋት በየትኛውም ዘመን ይቅርታ አያሰጥም።

አሁን ያለንበት ጊዜ እጅግ አደገኛ ነው። ሁሉም ተጨንቋል። የዛኑ ያህል አዋቂ ነን ባዮች ከኪሏቸው በላይ እየዘባረቁ አየሩን አብቀውታል። ሚዲያው በጃቸው የሆኑትም ሆኑ ሌሎች ትችታቸውና ተቃውሟቸው ገደብ አልፏል። በ፱፯ ዓ ም ” ፓርላማ ትገቡ እንደው ዋ!” ተብሎ ያ ድንቅ ምርጫ ድምሩ በዜሮ እንደተባዛ ሁሉ አሁንም ከዚያን ዘመን ፉከራ ትምህርት የተወሰደ አይመስልም። ይልቁኑም ጀግንነት ሆኗል።

በኦሮሚያ ሰፊ ድጋፍ አለው የሚባለው ጃዋር መሐመድም ሰለ ” ገሎና” እና ” ሴኮማንዶ” በቂ እውቀት እያለው ለመስከን አለመሞከሩ ግራ የሚጋባ ነው። ችግሩ እሱ ጋር የሚቀር ባለመሆን ጉዳይን ለመጠቆም አሰብኩ እንጂ፣ የኦሮሚያ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጉዳይ በራሱ አሁን ካለው ውጥረት በላይ ሌላ ውጥረት እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። እናም ሰከን ማለትና ሁሉንም በወጉ እያስኬዱ ሰላማዊውን ህዝብ ከጭንቀት ማላቀቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ይሆናል።

” ገሎና” እና ” ሴኮማንዶ” ቀጣዩ የኦሮሞ ህዝብ ትክርተ ናቸው። ሚዲያ ባይኖራቸውም ስር ሰደዋል። ገሎና የመካከለኛውን ኦሮሚያ ወይም የቦረና ግንድ ልጆችን ወደ አንድ ህብረት የሚያመጣ፣ ከፍ የሚያደርግ፣ ወደ ጎን የተዘረጋ አደረጃጀት ነው። አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ሃረርጌና ቦረና ወይም የባሬንቱን ግንድ አንድ የሚያደርግ አደረጃጀት ነው። በወለጋ በኩል ያሉት የሜጫ ግንዶች ያልተቀናጁ በርካታ ወኪሎች አሉዋቸው። እናም ገሎና ሸዋን ጨምሮ ድፍን መካከለኛ ኦሮሚያን እንደ ድር አድርቷታል።

እውነታው ይህ ነው። ጩኸትን መጮህ ይቻላል። ጩኸት ሁሉ ግን ሃይል አይደለም። የማይጮኹ ሃያላን አሉ። የማይጮሁ መናገር ሲጀመሩ እንደ ቆርቆሮ የሚጮሁ ይተነፍሳሉ። እናም ውሸታም መሆናቸውን ህዝብ ይለያቸዋል። ህዝብ ከመነዳት ራሱን ካልጠበቀ ውሸትን ከእውነት መለየት አይችልም። መለስ ውሸታም እንደነበር ገና ወደ ስልጣን ሳይመጣ ያወቁ ነበሩ። ዓመታት ቆጥረው በራሳቸው ምክንያት ቀጣፊነቱ ያልገባቸው ነበሩ። ዛሬም እንደዚያ ነው። የሰውን ልጅ እየማገዱና እያስማገዱ የህዝብ ወኪል ነን የሚሉ ጉዳያቸው ብዙም ሳይርቅ እርቃኑንን ይወጣል።

” ገሎና” እና ” ሴኮማንዶ” የኦሮሚያ ስውር አደረጃጀቶች አስመልክቼ በዚሁ ገጽ እመለስበታለሁ። ባልና ሚስት ተፋቱ ከሚለው የበቀለ ገርባ አዲሱ የእውቀት ደረጃ ምጥቀት ይጠብቃችሁ!! ዘመኑ አስፈሪ ነው። ክፉውን አያሳየን። ክፉው እንዲመጣ ሲጭሩ አድረው የሚውሉ ልብ ይስጣችሁ። ክፉው በደጅ ነውና እናስተውል!!

ጸሃፊ – አሻራ ለማ ተጂ ከተማ

 

ዝግጅት ክፍሉ – ይህ ጽሁፍ የጸሃፊውን እምነትና አስተሳሰብ ብቻ የሚያንጸባርቅ ነው

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *