“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ከስልጣናቸው ተነሱ

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮን ላለፉት ስድስት ወራት ሲመሩ የቆዩት ብርጋዴር ጄኔራል ከማል ገልቹ ከስልጣናው እንዲነሱ መደረጋቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

 

 

”ሰኞ ዕለት የተላከልኝ ደብዳቤ ከሥራ እንደተሰናበትኩ ይገልጻል” ሲሉ ብ/ጄኔራል ከማል ይናገራሉ። ”አይታወቅም፤ የተገለጸ ነገር የለም” በማለት ከሥራ የተሰናበቱበትን ምክንያት እንደማያውቁ ብ/ጄኔራል ከማል ጨምረው ተናግረዋል።

የሥራ ስንብት ደብዳቤው ከመድረሱ በፊት ውይይቶች እና ግምገማዎች እንደነበሩ የሚያስታውሱት ብ/ጄኔራል ከማል በስንብት ደብዳቤው ላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ ፊርማ እንዳረፈበት ያስረዳሉ።

Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድ

ብርጋዴር ጄኔራል ከማል የክልሉ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ሊደርስ እንደሚችል ቀድመው ይገምቱ እንደነበር ተናግረዋል።
ለዚህ ግምታቸውም ሁለት ምክንያቶች እንዳሏቸው የሚገልጹት ብ/ጀ ከማል “በአስተዳደሩ ውስጥ የፓርቲ እና የመንግሥት ሥራ የሚሰሩበት መንገድ በእኔ ፓርቲም ሆነ በግል እምነቴ ተቀባይነት የለውም። በመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ ላይ ፓርቲ ጣልቃ መግባት አለበት ብለን አናምንም” ሲሉ አንደኛውን ምክንያታቸውን አስቀምጠዋል።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

አክለውም ሁለተኛውን ምክንያት ሲጠቅሱ ” መለስ ብዬ ሳስበው የፖለቲካ ተቀባይነት ለማግኘት ሲባል እኔ ወደ ስልጣን እንድመጣ የተደረገው ውሳኔ አመራሩን ጥያቄ ውስጥ የጣለው ይመስለኛል” ሲሉ ይናገራሉ።

ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ከ13 ዓመታት በኋላ የጠቅላይ ሚንስትሩን የሰላም ጥሪ ተከትለው ከኤርትራ ባለፈው ዓመት ወደ ሃገር መግባታቸው ይታወሳል። ከዚያም ጥቅምት ወር ላይ ነበር የክልሉ የአስተዳደርና የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ብ/ጄኔራሉ ክልሉን ያሚያስተዳድረው የኦሮሞ ዲሞክራቲ ፓርቲ (ኦዲፓ) አባል አለመሆናቸው እና እራሳቸው የሚመሩት ፓርቲ መኖሩ ሹመታቸው በርካቶችን አስገርሞ ነበር።

ብ/ጄኔራሉ በሥራ ቆይታቸው በቢሮው የሰው ኃይል ስምሪት እና ቁጥጥር

Source – BBC

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0