(የኦነግ መግለጫ- መጋቢት 27 2011 ዓ.ም)

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድንበር ማስፋፋት እና ላልታወቃ ስዉር ዓላማ ቁጥራቸዉ ከመቶ በሚልቁ የክልሉ ልዩ ኀይል እና ከመንግስት ጦር የተቀነሱ ወታደሮችን ከከሚሴ የኦሮሞ ልዩ ዞን አስተዳደር ዕዉቅና ዉጪ በዳዌ ሐረዋ ወረዳ እና ርቄበምትባል ቦታ አሰማርተዉ በሰላማዊ ህዝብ ላይ በቄዬዉ ተኩስ ከፍተዉባቻዉ በሰዉ ህይወት እና በንብረት ላይ ዉድመትበማድረስ በህይወት የመኖርን መብት ነፍጓቸዋል፡፡

እነዚህ ኀይሎች በዝግጅት ላይ በነበሩበትም ሆነ ጥቃቱን በከፈቱበት ጊዜ ይዞ ስንቀሳቀሱ የነበሩት የኢትዮጵያን እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትን ባንድራ ሳይሆን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ዓርማ መሆኑ ደግሞ የአሁኑን ንክኪ ይበልጡኑ ያባባሰ መሆኑን ተረድተናል፡፡

Related stories   የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአስተዳደር እና ደህንነት ምክትል ኀላፊ የሆኑት ኮለኔል አለበል አማራ ትላንት ለቢቢሲ እንደተናገሩት እነዚህ እራሳቸዉን የአማራ ክልል ልዩ ኀይል ብለዉ የሰየሙት የጥፋት ኀይሎች የወሰዱትን እርምጃ ህጋዊ ለማስመሰልጣቱን ወደ ኦነግ በመቀሰር ሰላማዊ ትግልን በመጀመር ላይ ያለዉን ድርጅት ለመወንጀል ሞክሯል፡፡ የዚህ ዘመቻ መነሻ ለሀገርየማይታዘዙ ስርዓተ አልበኞችን በተለያያ ደረጃ በማሰማራት የልዩ ዞኑን ሰላም በማደፍረስ በህደትም በህግ የተደራጀዉን የኦሮሞ ልዩዞን ከምሴን በማፍረስ በኀይል ወደ ሌላ ዞን ለመቀላቀል በአድስ መልኩ የተጀመራ የተስፋፍነት አባዜ ነዉ ብለን እናምናላን፡፡

Related stories   የትግራይ ረሃብ ድሮም ተደብቆ የኖረ ወይስ አዲስ በሁለት ወር የተፈጠረ? ገለልተኛ ፈራጅ ያጣው አወዛጋቢው አጀንዳ! – ሪፖርት

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ልዩ ኀይል በቄዬዉ በሰላም ይኖር በነበረዉ ህዝብ ላይ የወሰደዉ እርምጃ ህግ እና ስርዓትን የጣሰ መሆኑን ያምናል፡፡ ለደረሰዉም ጥፋት ተጠያቂዉ ይህ ኀይል እና የሚመራቻዉ መንግስት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለመደዉ ዉሸት ኦነግን እየወነጀለ የህዝብን ሰላም ከማደፍረስ እራሱንእንድቆጥብ እንጠይቃለን፡፡

በመጨረሻም፤ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተፈጠረዉን ችግር በእርጋታ እንድፈታ እየጠቆሚን፤ የፌድራል መግስትም ይህጉዳይ በሌላ አቅጣጫ እንዳይሄድ ቁጥጥሩን ያደርግ ዘንድ አናሳስባለን፡፡

Related stories   ምርጫ ቦርድ ኢዜማን ጨምሮ ስድስት ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ቀይሩ አለ፤ ኢዜማ በመላው አገሪቱ ብቻውን እንደሚወዳደር አስታወቀ

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

መጋቢት 27 2011 ዓ.ም

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *