“Our true nationality is mankind.”H.G.

የፀረ ጥላቻ አዋጅ!

ክፍል_አንድ

አጠቃላይ

1. አጭር ርዕስ

ይህ #አዋጅ “የጥላቻ ንግግርንና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን

ለመከላከል የወጣ አዋጅ ቁጥር__/2011 “ተብሎ ሊጠቀስ

ይችላል፡፡

2. ትርጉም

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካለሆነ በቀር በዚህ

አዋጅ ውስጥ፦

1. “ንግግር” ማለት በቃል፣ በጽሑፍ፣ በምስልና ስዕል፣ በቅርጻ ቅርጽ እና በሌሎች ተመሳሳይ መንገዶች መልእክትን የማስተላለፍ ተግባር ነዉ፡፡

2. “የጥላቻ ንግግር” ማለት የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ፣ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ንግግር ነው።

3. “ሃስተኛ መረጃ” ማለት የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ

ውሸት የሆነና ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ክፍ ያለ ንግግር ነው።

4. “ብሮድካስት ማድረግ” ማለት በሬዲዮ ወይም በቴሌቪዥን ሥርጭት ማድረግ ነዉ፡፡

5. “ማህበራዊ ሚዲያ” ማለት ሰዎች መልዕክት ለመለዋወጥ፤ ትስስር ለማዳበር፤ ሀሳብ ለመጋራት የሚጠቀሙበት በኢንተርኔት አማካኝነት በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ ለሆኑ ሰዎች መረጃ የሚደርስበት መንገድ ነዉ፡፡

6. “ጥቃት” ማለት በግለሰብ፤ ቡድን ወይም ማህበረሰብ ላይ የሚደርስ የህይወት፤ የአካል፤ የስነልቦና ወይም ቁሳዊ ጉዳት ነው።

7. “ሰዉ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ ሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው።

8. ማንኛዉም በወንድ ጾታ የተገለጸ ለሴት ጾታ ያገለግላል፡፡

3. አላማ

የአዋጁ አላማዎች

1.ሰዎች ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብታቸውን ተግባራዊ

ሲያደርጉ ሰብዓዊ ክብርን፣ የሌሎችን ደህንነትና ሰላም አደጋ ላይ ከሚጥል ንግግር እንዲቆጠቡ ማስቻል፤

2. በማህበረሰቡ ውስጥ እኩልነት እንዲሰፍን፣ መከባበር እንዲኖርና መግባባትና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲጎለብት ማድረግ፤

3. ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት አደጋ የሆኑ የጥላቻ አመለካከትና

የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን መስፋፋትን እና ተያያዥ ወንጀሎችን መከላከል እና መቀነስ ናቸው።

ክፍል ሁለት

የተከለከሉ ተግባራት

4.#የጥላቻ_ንግግር

1.ሆነ ብሎ የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን፤ ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ውጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈፀም፤ ወይም

ጥቃት እንዲፈፀም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል፦

ሀ. መልዕክቶችን በመናገር፥

ለ. ፅሁፍ በመጻፍ፥

ሐ. የኪነጥበብ እና እደጥበብ ውጤት በመስራት፥

መ. ፅሁፍ፣ ምስል፣ ስዕል፣ የኪነጥበብ እና፥ እደጥበብ ውጤት፣ የድምፅ ቅጂ፣ ወይም ቪዲዮ በማተም ወይም በማሰራጨት፥

ሠ. መልዕክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት፤ ወይም

ረ. በሌሎች ማናቸውም መገናኛ መንገዶች ለህዝብ መልዕክቱ እንዲደርስ ማድረግ ክልክል ነው።

2. ማንም ሰው በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ ቁጥር 1 ላይ በተገለፀው አግባብ ጥላቻ የሚያስተላልፍ መልእክት ለማህበረሰብ ወይም ለሶስተኛ ወገን እንዲደርስ በማሰብ በህትመት ወይም በፅሁፍ መልክ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

5. የሃሰት መረጃ

የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፣ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልፅ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መረጃን ሆነ ብሎ በማንኛውም መንገድ ማሰራጨትና ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ የተከለከለ ነው።

ክፍል ሶስት

የወንጀል ተጠያቂነት

7. የወንጀል ተጠያቂነት

1. ማንም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4(1) (ሀ-ረ) የተመለከቱትን የተከለከሉ ተግባራት የፈጸመ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ እስከ ሶስት አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም እስከ ብር 10,000 በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡

2. በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4 ንዑስ አንቀፅ 1 የተከለከሉት ተግባራት በመፈጸማቸው የተነሳ በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ወይም የተሞከረ ከሆነ የተከለከሉትን ተግባራት የፈጸመዉ ሰው እንደነገሩ ሁኔታ እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።

3. ማንም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 4(2) ላይ የተመለከተውን የተከለከለ ተግባር የፈጸመ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ ከአንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ከብር 5000 ያልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡

4. ማንም ሰው በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 የተመለከተውን የተከለከለ ተግባር የፈጸመ እንደሆነ እንደነገሩ ሁኔታ እስከ አንድ አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም እስከ ብር 3,000 በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡

5. በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 የተመለከተውን የተከለከለ ተግባር

የፈጸመው ሰው ድርጊቱን የፈጸመው ከአምስት ሺ በላይ ተከታይ ባለው የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ከሆነ ወይም በብሮድካስት አገልግሎት ወይም በየጊዜው በሚወጣ የህትመት ውጤት ከሆነ እስከ ሶስት አመት በሚደርስ በቀላል እስራት ወይም እስከ ብር 10,000 በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡

6. በዚህ አዋጅ አንቀፅ 5 የተከለከለው ተግባር በመፈጸሙ

በግለሰብ ወይም በቡድን ላይ ጥቃት የተፈጸመ ወይም የተሞከረ ከሆነ፣ ሁከት ውይም ግጭት የተከሰተ እንደሆነ የተከለከለውን ተግባር የፈጸመዉ ሰው እንደነገሩ ሁኔታ እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።

Source: #EthioNewsflash

Gemechu& Andualem help?!

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0