አሁን አሁን እየተለመደ የመጣው ጉዳይ ” ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል” የሚል ቀልድ መስማት ነው። እኒህ ለሰው ልጆች ህይወት ቅንጣት ደንታ የማይሰማቸው ሰላምዊ ሕዝብ አብሮ እንዳይኖር አጀንዳ እያራቡለት ካጋደሉት በሁዋላ ” አዝነናል፣ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን” እያሉ ይሳለቃሉ። አፈር እየገፋ የሚኖር ምስኪን ሕዝብ ደጅ እሳት አዳፍነው ቤንዚን ከረጩ በህዋላ መግለጫ በማዥጎድጎድ የአዞ እንባ ያነባሉ።

ኦነግ ሸኔ በጫካና በከተማ ተከፍሎ በመትነንና በመክሰም መካከል እየተንፈራገጠ ባለበት ወቅት የእሱ ምትክ ለመሆን የሚታትሩ ከሌላ ጫፍ ተፈልፍለው ለመሞት እየጋለቡ ነው። የሚያሳዝነው ይህ ግልቢያቸው አክሳሪ መሆኑን በገሃድ የሚያዩ ወገኖች ሊደግፏቸውና የመልዓክ ክንፍ ሊተክሉላቸው ሲራወጡ መታየቱ ነው። አሁን በገቢር እንደሚታየው የኦነግ ቅርጽ ያለውና በከፍተኛ በጀት ለጥፋት አክርሮ እየበረረ ያለው ሃይል ሳይፈጠር ወደ መትነን መቃረቡ ነው።

ለጊዜው ይፋ አይሁን እንጂ መከላከያ ሰራዊት እያሳደደ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ወረበሎች የጉዳዩን ምንጭ እየዘከዘኩት ስለሆነ በቅርብ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ነው። ለዛጎል መረጃ የሰጡ እንዳሉት አደራጅቶ፣ አስታጥቆና ክፉ ሃሳብ ጠቅጥቆ ሰላማዊ ህዝብ ላይ አውሬዎችን ያሰማሩት ክፍሎች ይፋ ሲሆኑ የሚሰጡት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

በሰሜን ሸዋ የተለያዩ ቦታዎች፣ በተለይም በከሚሴ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ ከየአቅጣጫው የሚሰሙት መረጃዎች ግራ የሚያጋቡ ቢሆኑም መንግስት ዘⷝቶም ቢሆን በቁጥትር ስር አድርጎታል። በነፍጥ የታገዘና የተደራጀ ጥቃት መፈጸሙ ለምንና ምን ተፈልጎ እንደሆነ ሃላፊነት ወስዶ ማብራራት የቻለ ሃይል የለም። በድርጊቱ የተወነጀለው ኦነግ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን ኮንኖ ማጣራት እንዲካሄድ አስቀድሞ ጠይቋል።

“ጉዳቱ እና ጥቃቱ በተደራጀ መልኩ ስለነበር በቀጠናው የእምነት ተቋማት ጭምር እስከ ማቃጠል የተደረሰበት ሁኔታ አለ” ሲሉ የሰሜን ሸዋ ዞን የአስተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢያ ለጀርመን ድምጽ አስታውቀዋል። የአብን ከፍተኛ ሃላፊ የሆኑት አቶ ክርስቲያን ” አናለቅስም። ሰማእታት ናቸው” ሲሉ በክልሉ ሚዲያ ተደምጠዋል። ንጹሃኑ ለየትኛው ዓላማ ሰማዕት እንደሂኑ ግን አላብራሩም።

Related stories   ሱዳን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደምታነሳ አስጠነቀቀች፤ "ብሄራዊ የጀግንነት ጥሪ ያፈልጋል"

ግጭቱ ወይም ጥቃቱ ከመከናወኑ በፊት ቬሮኒካ መላኩ በሚል የፌስ ቡክ አምደኛ የሚታወቁት ይህንን ብለው ነበር።

“አማራነት ወይም ሞት” ፋኖ የማይቀርበት ቀን እሁድ መጋቢት 29 ኬሚሴ ላይ ፕሮግራም ተይዟል!!

~እኛን አማራ የሚባል አያስተዳድረንም !!
~ኬሚሴ ከተማ ተብሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን አስተዳደር በ29 በሚኖረው የአማራ ወጣቶች ማህበር አንድ የአማራ ክልል ባለስልጣን ድርሽ አይልም፣ኬሚሴንም አይረግጥም!!~ከመጡም የአስክሬን ሳጥናቸውን ይዘው ይምጡ!! ይህን ቃል በቃል ለኬሚሴ

አማራ ወጣቶች ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ የመለሱላቸው ነው ።እኔም ኬሚሴ ከተማ ካሉ የመረጃ ምንጮቼ ደውዬ እንዳረጋገጥኩት የጀዋር መልዕክተኞች ከአርሲ እንደመጡና በከተማዋ ውስጥም የኦነግ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጭምር እንዳላቸው አረጋግጠውልኛል።!!እስኪ እናያለና እዛው በሜዳችን እንገናኛለን ሙያ በልብ ነው!!!ተካረምናት፣ክልላችን መሬታችን ላይማ ከአርሲ በመጣ የኦነግ አሸባሪ አይፈነጭባትም።ለ አስር ሺህ ኦሮሞ አንድ ፋኖ በቂያችሁ ነው እንተዋወቃለን።አንድ ጥይት ሳንተኩስ በአይሱዙ ጭነን እንልካችዋለን።

ዋናው ነገር ግን የአማራ ወጣቶች ማህበር በኬሚሴ እሁድ መጋቢት 29 ይመሰረታል ማለት ይመሰረታል ነው ሰምተሀል ይ መ ሰ ረ ታ ል!!

እናንተ ስታፈናቅሉን እኛ ዝም ያልነው እኮ ትልክና አስተዋይ መሆናችን እንጅ አቅም አተን አይደለም።የአማራ ፋኖ አይደለም ከኬሚሴ ከኢትዮጲያ የማስወጣት አቅም አለን ወዳጄ፣
መጋቢት 29 ማለትም የፊታችን እሁድ ሁሉም የአማራ ልጆች እንዳይቀር እዛው ሁሉንም እናየዋለን።ጀግንነታችሁን እዛው እንዲታሳዩን፣ነገር ግን አንድም የኦሮሞ ተወላጅ እንዳይቀር አደራ እንደ ደብረ ዘይቱ በአንድ የፋኖ ተኩስ ፈርጥጣችሁ አርሲ እንዳትገቡ።እንደዚ አፍህን እንድትከፍት ያደረገህ የእኛው አዴፓ ነው እንጂ ጀዋር ወይም ኦነግ አይደለም።ኬሚሴን እኮ እንድትኖሩበት ፈቀድንላችሁ እንጅ መሬቱን አልሰጠናችሁም።ይህንንም ደግሞ የመንፈግም መብቱ የኛ ነው።ቤታችን ውስጥ ሆነህማ አትፀዳዳብንም ጥንባታም ጋላ ሁላ።

Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

አማራነት ወይም ሞት!! እጣ ፈንታችንን በእዳችን እንፅፋለን

ቬሮኒካ መላኩ ነኝ ፤

መጋቢት 24/2011 ከቤተ አምኃራ

ሰብአዊ ቀውሱን ተከትሎ አብን ይህንን መግለጫ አውጥቷል

መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አብን ይጠይቃል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የፌዴራልና ክልል መንግሥታት የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት በአግባቡ ማስጠበቅ ባለመቻላቸው ከሰሞኑ ራሳቸውን የኦነግ አባላት መሆናቸውን የሚናገሩና የኦነግን ዓርማ የያዙ የቡድን ጦር መሣሪያዎችን የታጠቁ የጥፋት ኃይሎች በምድረገኝ/ከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች በፈፀሙት ወረራ በወገኖቻችን ላይ ግድያን ጨምሮ በርካታ ማኅበረስነልቦናዊ ጫና ፈጥረዋል። የተደራጁ ወራሪ ቡድኑ ቤተእምነት ሳይቀር አቃጥሏል። ሰላማዊ የሕዝባችን የዕለት ተዕለት ኑሮም በተፈፀመው ድንገተኛ ወረራና የተደራጀ ዘረፋ ተናግቷል። የሆነው ሁሉ ታስቦበትና ታቅዶበት የተደረገ ወረራ ስለመሆኑ አብን ከፍተኛ ጥርጣሬ አለው። እስካሁን የተገኙ መረጃዎችም ይኸንኑ ጥርጣሬያችንን የሚያጠናክሩ ሆነው አግኝተናቸዋል። የክልሉ መንግሥት በወገኖቻችን ላይ በጥፋት ኃይሎች እየተፈፀመ ያለውን ግድያ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ በአስቸኳይ ሊያስቆመው ይገባል። የፌዴራል መንግሥትም ከወገንተኝነት ወጥቶ ወራሪዎችን ሊቆጣጠር ይገባዋል።

«ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል» እንዲሉ አማራ ጠል ወራሪ ኃይሎች በሕዝባችን ላይ ያደረሱት በደል አንሶ የአብንን ስም ለአደባባይ ቅሌታቸው መሸፈኛ ለማድረግ ሲሯሯጡ አስተውለናል። በከሚሴ ዞን የገጠር ቀበሌዎች «አብን በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ጭፍጨፋ ሊያካሂድ ነው» የሚል የአሉባልታ መርዛቸውን በመርጨትም ነዋሪዎችን እየቀሰቀሱ መሆናቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶናል። አብን ላይ መሰል የስም ማጠልሸት ተግባራት የሚያከናውኑ አካላት ለፈፀሙት የጭፍጨፋ ወንጀል የጎሳና ኃይማኖት መደበቂያ ዋሻ እየማሱ መሆኑን ብንረዳም ቅሉ፤ በእነዚህ ግለሰቦች የተሳሳተ መረጃ መነሻነት አካባቢው ወደ ተራዘመ የብጥብጥ ማዕከልነት እንዳይቀየር፤ መንግሥት አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ እርምጃ እንዲወስድ ከወዲሁ እናሳስባለን። አብን ሕዝባችንን በቋንቋና ኃይማኖት የሚከፋፍሉ አካላትን እያወገዘ ለወገናችን እንድነት በጽናት መቆሙንም ያረጋግጣል።

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

ንቅናቄያችን በምድረገኝ/ከሚሴና አጣዬ አካባቢዎች በደረሰው የወገኖቻችን ሕይወት መጥፋት የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን እየገለፀ፤ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ጥፋቶችን በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርቡ በአጽንዖት ይጠይቃል።

እጣፈንታችንን በራሳችን እጆች እንጽፋለን!

መጋቢት 30/2011 ዓ·ም
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ
አዲስ አበባ፥ሸዋ፣ ኢትዮጵያ

ሁሉም ወገኖች የየራሳቸውን ቢሉም አሁን ባለው ሁኔታ አማራ ክልል በተደጋጋሚ ቦታ እየለየ የሚደርስበትን ጉዳት መሸከም የሚችልበት አቅም፣ የፌደራል መንግስትም ህግ አያስከብርም እየተባለ የሚወቀስበት ጊዜ ሊያከትም እንደሚችል የዛጎል ምንጮች ይናገራሉ። ይህንን እውን ለማድረግ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊታወጅና አጥፊዎችን ለህግ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ ይጠቁማሉ። ይህንኑ ውሳኔ በህዝብ እውቅና እንዲሰጠው ሰፋፊ ህዝባዊ ውይይቶችና የወቅታዊ ሁኔታዎችን ማስገንዘቢያ መድረኮች እንደሚዘጋጁም ታውቋል።

ኦዲፒ የታችኛው መዋቅሩ በኦነግ ጀሌዎች፣ የአዴፓ መዋቅርም በአብን የተሰረሰረ በመሆኑ ማጥራቱም ተጠናክሮ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ለውጡ ይፋ ከሆነ ጀምሮ በከፍተኛ በጀት አገሪቱን ከዳር እስከዳር ለማፈራረስ ሲሰሩ የነበሩ አካላት ክፍተቱን ተጠቅመው ስልታን ለመጨበጥ ያላደረጉት ጥረት የለም። ያላደረሱት የጉዳት አይነት የለም። ህዝብ አይሆንም በማለቱ ቦታ እየቀያየሩ አገሪቱን ለማፈራረስ ለሚተጉ ከሃጂና አኩራፊ ሃይሎች አሁንም ህዝብ እንቢታን በመመለስ፣ ልሂቃን ማስተዋልን በምምረጥና ዝምታን በመስበር፣ ወጣቱ ግብተኛነትን በመጠየፍ ሰክኖ ሊራመድ እንደሚገባ ጉዳዩ የገባቸው እየወተወቱ ነው።

የአማራ ክልል ማምሻውን እንዳስታወቀው አሁን ተኩስ እንደቆመና ነገሮች ወደ መላክም ገጽታቸው እየተመለሱ ሲሆን የአምልኮ አጸዶችን በማቃጠል ለተፈጸመው ወንጀል ሙስሊሙና ክርስቲያኑ በህብረት መልሶ የማቋቋምና አደጋውን የመከላከል ስራ በህብረት እየተሰራ መሆኑንን አመልክቷል።

በተመሳሳይ አስር ሰው ሳይሞት ጉዳዩ ከሩዋንዳ እልቂት የሚብስ እንደሆነ በማህበራዊ ገጽ በመዘገብ በሌሎች ክልሎች የበቀል እርምጃ እንዲወሰድ የሚወተውቱ ” አክቲቪስቶችና”  የነሱን ሃሳብ አከፋፍዮች ጽሁፍ እያሰራጭም ነው።

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *