“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኦሮማራን ጥምረት ማፍረስ የመጨረሻ ድንቁርና ነው!

ስለ ኦሮማራ አስፈላጊነት እና ፋይዳ ያልተባለ ነገር የለም ማለት ይቻላል። ግማሾቹ ተጨባጭ መሰረት የሌለው ጥምረት እንደሆነ ሲናገሩ የተቀሩት ሌሎች ብሔሮችን አግላይ እንደሆነ ይገልፃሉ። አንዳንዶች ኦሮማራ ህወሓትን ለማስወገድ ብቻ ያለመ ወቅታዊ ጥምረት ነው ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ጥምረቱ ኦህዴድ/ኦዴፓን በህወሓት ቦታ ለመተካት ተግባራዊ የተደረገ የአጭር ግዜ ስልት እንደሆነ ይገልፃሉ። ይሁን እንጂ ሁሉም ወገኖች የማይክዱት ሁለት መሰረታዊ ሃቆች አሉ። አንደኛ፡- የኦሮማራ ጥምረት ለተወሰኑ ወራትም ቢሆን በኦሮሞና አማራ ልሂቃን መካከል የነበረውን የእርስ-በእርስ መዘላለፍ እና መጠላለፍ በመግታት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መንገድ እንዲነጋገሩና እንዲተባበሩ አስችሏል። ሁለተኛ፡- በዚህ አጋጣሚ የኦዴፓና አዴፓ አመራሮች፣ እንዲሁም በኦሮሞና አማራ ልሂቃን መካከል የተፈጠረው ጥምረትና አንድነት የህወሓትን የጭቆና ቀንበር ማስወገድ ችለዋል።

ህወሓት አዲስ አበባን ለቅቆ መቀሌ ከገባ በኋላ፤ ላለፉት 27 አመታት “ፖለቲካ እሳት ነው!” እያለ ጓዳ ውስጥ ሲርመጠመጥ፣ የህወሓት/ኢህአዴግ አባልና ደጋፊ ሆኖ ሲያሽቃብጥና ሲልመጠመጥ የነበረ ሁሉ የፖለቲካ ድርጅት አመራርና አባል ሆነ። አሜሪካና አውሮፓ ሆነው ሙሾ ሲያወርዱ የነበሩ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በእውን የሌለ የቢሆን-ዓለም ተረታቸውን ይዘው መጡ። አስመራ ተቀምጦ እርሻ ሲያሳርስ የነበረ ነፃ አውጪ ተብሎ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። ቀድሞ በፍርሃት ቆፈን ተለጉሞ የነበረ ሁሉ የፖለቲካ አዋቂና ተንታኝ ነኝ አለ። በአጠቃላይ በጭንቁ ወቅት በየስርቻው ተደብቀው የነበሩ የድል አጥቢያ ጀግኖች ከያሉበት ተጠራርተው በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ አድራጊ-ፈጣሪ ሆኑ።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

የድል አጥቢያ ጀግኖች የመጀመሪያ ሰለባ የሆነው የኦሮማራ ጥምረት ነው። ላለፉት 27 አመታት በቂምና ጥላቻ የተገነባን ግንብ ያፈረሰ፣ በኦሮሞና አማራ መካከል የሰፈነውን ያለመተማመን እና ጥርጣሬ በመቅረፍ እርስ በእርስ መተማመን እና መተባበር ያስቻለን ጥምረት ለማፍረስ መረባረብ ጀመሩ። በእርግጥ ለረጅም አመታት ቂምና ጥላቻ ሲሰበኩ የኖሩ ህዝቦችን ዳግም መለየትና መለያየት ቀላል ነው። ችግሩ በአፈረሱት ምትክ ምንም ይዘው አለመቅረባቸው ነው። ከቀድሞ የተሻለ አማራጭ ሳይኖርህ የነበረውን ማፍረስ የመጨረሻ ድንቁርና ነው።

Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ

የኦሮማራን ጥምረት በጋራ በማጣጣልና በማውገዝ ለማፍረስ ያደረጉት ጥረት የድል አጥቢያ ጀግኖች ድንቁርና ማሳያ ነው። ይህን የትብብርና አንድነት መድረክ ከማፍረስ በስተቀር የተሻለ አማራጭ የፖለቲካ መንገድ ለመቀየስ ቅንጣት ያህል ጥረት ሲያደርጉ አይስተዋልም። የኦሮማራ መንገድ ዛሬ ላይ አድርሶናል። ዛሬ እሱን ለማፍረስ የምትረባረቡት ነገ በየትኛው መንገድ ወደዬት ልትሄዱ ነው? ድንቁርና ግብዝ ያደርጋል! ግብዝ ሰው እንኳን በተግባር የሚያደርገውን በቃላት የሚናገረውንም ጠንቅቆ አያውቅም። ትላንት መብታችሁን ለመጠየቅ ቅንጣት ያህል ድፍረት ያልነበራችሁ ዛሬ ላይ የመብት አስከባሪ፣ የህዝብ ተቆርቋሪ መሆን አትችሉም። እኔ የማዝነው እናንተን ተከትለው በራሳቸው ላይ ዕልቂት ለሚደግሱትን ሚስኪኖች ነው።

Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ
Seyoum Teshome

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0