“Our true nationality is mankind.”H.G.

ዛጎል አጫጭር ዜናዎች

 “… ምርጫ  መደረግ ያለበት የተሻለ ነገር ለማምጣት ነው” ብርቱካን ሚደቅሳ

Image result for birtukan mideksa

የሥራ ጫናም ሆነ በአገሪቱ ከሚታየው መረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫው የጊዜ ወደፊት መገፋት እንለበት ቢያምን ይህን የማድረግ ሥልጣን አለው ወይ በሚል የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጣን “የለውም” ብለዋል አያይዘውም ሊደረግ የሚችለውን አብራርተዋል።
”ምርጫ ለማድረግ ያህል አናደርግም።ምርጫ በዜጎች ደህንነትና ሕይወት ላይ የተባባሰ ነገር ለማምጣት ብለን አናደርግም። ምርጫ የተሻለን ነገር ለማምጣት ነው መደረግ ያለበት። እስካሁን ከተደረጉ ምርጫዎች በአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ተአማኒነት ያገኘ እንዲሆን አድርገን ለሱ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በኛም ፣ በተሳታፊዎችና በሰላሙ ሁኔታ መሬት ላይም መኖራቸውን አረጋግጠን ነው የምናደርገው። “ ብለዋል
አያይዘውም “የኛ ዝግጅት ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ ፣ የሌሎች ተሳታፊዎች ያሉበት ሁኔታ እንዴት እንደሆነ እና ያለው ደግሞ የሰላም ሁኔታ ምርጫን ለማድረግ የሚያስችል ነው ወይ? የሚለውን ግምገማ አይተን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ማድረግ አንችልም ብለን የምናምን ከሆነ ይህንኑ በዝርዝር አስቀምጠን ለሚመለከተው አካል በጥያቄ እናቀርባለን” ብለዋል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዜግነትና በመራጮች ትምሕርት ረቂቅ መመሪያ ላይ ከሲቪክ ማሕበረሰብ ድርጅቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

Related stories   ‹‹የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ከፍተኛ ጥቅም አለው፤ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር ያጠነክራል››

VOA

Image result for ጁሊያን አሳንጅ

የብሪታንያ ፖሊስ በኤኳዶር ኤምባሲ ሎንደን ውስጥ ተጠልሎ የከረመውን የዊኪሊክስ መሥራች ጁሊያን አሳንጅን ማሠሩ ተቃውሞም ድጋፍም አስከተለ። ምሥጢራዊ መረጃዎችን አደባባይ በማውጣት የሚታወቀው ዊኪሊክስ ባለቤት ላለፉት ሰባት ዓመታት ገደማ ሎንዶን በሚገኘው የኤኳዶር ኤምባሲ ጥገኝነት ጠይቆ ተቀመጦ ነበር። ዊኪሊክስ ኢኳዶር ሕገወጥ በሆነ መንገድ ለአሳንጅ የሰጠችውን ከለላ ድንገት በማቋረጧ ዓለም አቀፍ ሕግን ጥሳለች ሲል ከሷል። የኤኳዶር ፕሬዝደንት ሌኒን ሞሬኖ ግን ክሱን አስተባብለዋል፤«ሚስተር አሳንጅ ምንም እንኳን ተገቢውን ደንብ እንዲያከብር በተለያየ አጋጣሚ ቢጠየቅም፤ በተደጋጋሚ ከሃቫና እና ካራካስ የዲፕሎማሲ ጥገኝነት አሰጣጥ ሥርዓትን የሚቃረን ተደጋጋሚ ጥሰት ፈጽሟል። በተለይም በሌሎች ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ደንብን የሚጻረረውን ደንብ ጥሷል።»አክለውም ለሌላ ሀገራት ተላልፎ እንዳይሰጥ ከብሪታንያ የመተማመኛ ቃል እንደተገባላቸውም አመልክተዋል። የብሪታኒያ ፖሊስ በበኩሉ ዩናይትድ ስቴትስ ተላልፎ እንዲሰጣት በመጠየቋ ዛሬ ረፋዱ ላይ አሳንጅን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለው አስታውቋል። አሳንጅ ስዊድን ውስጥ በወሲብ ጥቃት ክስ ተመስርቶበት ቆይቷል። ደጋፊዎቹ መታሰሩን ፕረስ ነፃነት ላይ የተወሰደ አሉታዊ ርምጃ ነው በሚል ሲያወግዙ፤ ተቃዋሚዎቹ በአንፃሩ ለፍትህ መከበር የተደረገ ነው እያሉ ነው። የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ የአሳንጅ መያዝ ማንም ከሕግ በላይ እንዳልሆነ አመላካች ነው ብለውታል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በበኩላቸው የዴሞክራሲ እጅ ነፃነትን እያነቀ ነው ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። ጁሊያን አሳንጅ በዌስት ሚንስቴር ማጅስትሬት ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

DW

ሁለት ጊዜ የተራዘመዉ 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ

ከአንድም ሁለት ጊዜ የተራዘመውና መች እንደሚከናወን ገና በውል ውሳኔ ያላገኘው 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ምንም እንኳን በጊዜ ገደቡ መከናወን ባይችልም አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲከናወን ይሰራል ሲል ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለዶቼ ቬለ «DW» ተናግሯል፡፡

    
Karte Sodo Ethiopia ENG

ከአንድም ሁለት ጊዜ የተራዘመውና መች እንደሚከናወን ገና በውል ውሳኔ ያላገኘው 4ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ምንም እንኳን በጊዜ ገደቡ መከናወን ባይችልም አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲከናወን ይሰራል ሲል ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለ« DW » ተናግሯል፡፡ ቆጠራው እንዲራዘም ሲወሰን ሰፊ ክርክር ተደርጎና በወቅቱ ቢከናወን በሃገሪቱ ላይ ለሌላ ቀውስ መጋበዝ መሆኑን ሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እንዲሁም ፌዴራል መንግስት አምነውበት መወሰኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ተናግረዋል፡፡ ከምንም በላይ ግን በሃገሪቱ የጸጥታ መጓደል በየቦታው ከቀያቸው የተበተኑ ኢትዮጵያዊያን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለመቻሉ ቆጠራውን ለማራዘም ገፊ ምክንያት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ቆጠራው መራዘሙ ሲሰማ የቆጠራ መሳሪያውን ወደየ ቤታቸው ይዘው ሄደው የነበሩ ወደ አንድ መቶ የሚደርሱ ሰራተኞችም አሁን ንብረቶችን መልሰው ገቢ አድርገዋል ብለዋል ሃላፊው፡፡

Related stories   ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ

DW

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳ የወለጋ ስታዲየምን መረቁ

በነቀምቴ ከተማ የተገነባው የወለጋ ስታዲየም 80ሺ ሰው የማስተናገድ አቅም እንዳለው ሰምተናል፡፡ስታዲየሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፍጹም ቅጣት ምት በመምታት እንደመርቁት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተነግሯል፡፡ለወለጋ ስታዲየም ግንባታ 196 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ የተሰማ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 181.7 ሚሊዮኑ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑን ሰምተናል፡፡ዛሬ ተመርቆ የተከፈተው ስታዲየም በነቀምት ትልቁ አና ዘመናዊው መሆንን ጽ/ቤቱ ተናግሯል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0