ዛጎል ዜና – “ወይፈንን መጋፈጥ የሚቻለው ፊት ለፊት ቀንዱን በመያዝ እንጂ ጭራውን በመጎትተ አይደለም። ጭራውን በመያዝ ወፈንን ለምታገል መሞከር ነጮቹ እንደሚሉ ማምታት ነው” ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ጌታቸው አረዳ ተናገሩ። ከለውጡ በሁዋላ እጅግ የሚደነቁ ስራዎች ቢሰሩም አሁን ያለውን ችግር ግን ለመቅረፍ አያስችሉም አሉ። ሰኞ በሚጀመረው የድርጅቱ ጉባኤ ከሁሉም በላይ አገሪቱ ያለችበትን አደገና ሁኔታ አምኖ መቀበል ዋና ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አስታወቁ። “ለጥቅም ሲባል ከማጭበርበር የሚችል ካላ ልንሰጥ ይገባል” ብለዋል።

ከድርጅታቸው ጉባኤ መጠናቅቀ በሁዋላ ከወይን ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ጌታቸው ይህንን የተናገሩት አዴፓ በክልሉ ውስጥ ለተፈጠሩት ቀውሶች ህወሃት ላይ በማመካኘት እጁን ስለመቀሰሩ ተጠይቀው ሲመልሱ ነው። ምላሽ የተሰጠው በአማራ ክልል ለተከሰቱትና እየተከሰቱ ካሉት ግጭቶች ጀርባ የህወሃት እጅ እንዳለበት የአዴፓ አመራሮችና ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በተደጋጋሚ ለሚያቀርቡት ክስ ነው።

“ኢህአዴግ ጋር የነበሩ ኳሊቲዎች ችግሮችን ፊት ለፊት ነው መሚጋፈጥ ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው አዴፓ በክልሉ ለሚፈጠሩት ችግሮች በሙሉ ሃላፊነቱን መውሰድ የሚገባው ራሱ እንጂ ሌላ አካል አለመሆኑንን ተናግረዋል። የትግል ጓዶቻቸውን ስም መጥራት እንደማይፈልጉ በመግለጽና በፊትለፊት እንደሚናገሩዋቸው ያወሱት አቶ ጌታቸው፣ “አዴፓ ህወሓትን ተጠያቂ ማድረግ አይችልም፡፡አማራ ክልል ለተፈጠረው ችግር በዋናነት ሳይሆን መቶ ከመቶ ተጠያቂው ነው ” ብለዋል።

የሕዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ሃላፊነት በመውስደ መንግስት እንደሚኮን፣ ይህን ማድረግ ሳይቻል ሲያቃጥል በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጄ አይነት የመንግስትነት ይዘት እንደሌለ፣ ማናቸውንም ጉዳዮች እንደ ወይፈኑ ምሳሌ ፊት ለፊት ቀንዱን ይዞ መዋጋት ግድ መሆኑንን በመግለጽ  “እንደዚህ ዓይነት ሰዎች” በማለት የአዴፓን አመራሮች ተችተዋል። ” እነ እገሌ ናቸው” በሚል ምንም ስሌትና ማስረጃ ሳያቀርቡ ህወሃት ላይ ወቀሳ መሰንዘራቸውን ኮንነዋል። ይሁን እንጂ የአዴፓ አመራሮች በምን በመን ጉዳዮች ህወሃትን እንደወቀሱና ጣታቸውን እንደቀሰሩ አላብራሩም። ጠያቂውም በትኖ አልጠየቀም።

” ቢያንስ ቢያንስ” አሉ አቶ ጌታቸው ” ቢያንስ በሚባለው ደረጃ አንድ ድርጅት እኮ ነን” ካሉ በሁዋላ ” እነዚህ ሰዎች” ሲሉ የጠሩዋቸውን የአዴፓ አመራሮች ራሳቸውን ወደ እስረኛነት የሚወስድ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው እየገቡ ያሉት። እስረኝነቱ በምን መልኩ እንደሆነ አላብራሩም።

የፊታችን ሰኞ ከሚጀመረው የድርጅቱ ጉባኤ ምን እንደሚጠበቅ ለተጠየቁት ” አገሪቱ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች አምኖ መቀበል ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ችግር እንዳለ ማመን አብዛኛው የመፍትሄው ክፍል መሆኑንም ጠቁመዋል።

” እውነት ለመናገር እጅግ በርካታ ሃሪፍ ሃሪፍ ስራዎች ተሰርተዋል” ሲሉ ለውጡን ያሞካሹት አቶ ጊታቸው በተቃራኒው የተሰራው ሃሪፍ ስራ ሁሉ አገር አሁን ካለችበት ችግር እንደማያድን አስምረውበታል።

“የተሰሩት ታላላቅ ስራዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቤታቸው አይመልስም፣የእርስ በእርስ ግጭቶችን አያስቆምም፣የተዳከመውን  የኤክስፖርት እንቅስቃሴ አያስቀጥልም” በማለት ተናግረዋል። “እስከ ሚቀጥለው ምርጫ ድረስ ቢያንስ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተመልሶ ህዝብ ቢያዳምጥ ፣ከነብዙ ችግሩ ከነ ብዙ ጣጣው /ጣጣውን ይድገም አላልኩም ግን የጎደሉትን አማልቶ ለህዝብ ጥያቄዎች የሚመጥን ትኩረት ሰጥቶ፣ ለህዝብ ተስፋ ሊሆን የሚችል ችግርን ተቀብሎ፣ ለመንቀሳቀስ የሚወስንበት መድረክ ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉም ገልጸዋል። 

“ለጥቅማ ጥቅም ሲባል ህዝብን ከማጭበርበ የሚችል ሰው ካላ እንስጥ ነገር ግን እስካሁን አላየሁም” ሲሉም አማራጭ አገር ተረካቢና አስተዳዳሪ ሃይል እንደሌለ ተናግረዋል።

የትግራይን ደህንነትና የህዝብን ሰላም ለማስጠበቅ የተቀመጠው አቅጣጫ አግባብ እንደሆነ በህወሃት ደረጃ መገምገሙና በስኬት መታየቱንም አቶ ጌታቸው አመላክተዋል።

 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *