“Our true nationality is mankind.”H.G.

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ!

 

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 03/2011 ዓ/ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በፓርቲው መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ የነበረው የተሃድሶ እንቅስቃሴ የደረሰበት ደረጃና አጠቃላይ የክልሉ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ በልማት ፣የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር መሻሻል፣ እንዲሁም የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል ፡፡ከዚህም በተጨማሪ በአገራችን እየታየ ያለው ሁለንተናዊ ችግር ከአከባቢ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የሚሻሻልበት ሁኔታ በመለየት ለአገራችንና ለክልላችን ያለው ትርጉም በመረዳት ተጨማሪ የቀጣይ አቅጣጫዎች ለይተዋል፡፡

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በትግራይ በአንድ በኩል ባለፈው ዓመት የጀመርነው ስር ነቀል የተሃድሶ እንቅስቃሴ በ2011ዓ.ም አጠናክሮ ለመቀጠል ተይዞ የነበረ እቅድ በዝርዝር ገምግመዋል ፡፡ መሰረታዊ ተልእኮችን የሆነው ልማትን እውን ማድረግና መልካም አስተዳደር ሰላምን ለማረጋገጥ በቀጣይ ለማጠናከር እንቅስቃሴ ሲያደረግ ቆይተዋል፡፡አሁንም ከዋናው ዓላማችን ሳንወጣ በክልላችን የተያዙ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመለየት የህዝባችንን ደህንነት በሚያረጋግጥ መልክ ተቃኝተው እንዲፈፀሙ ሰፊ ጥረት ሲደረግ ቆይተዋል፡፡ በተለይ በህዝባችን ያልተቆጠበ ጥረትና ከፍተኛ ንቃት የክልላችን ሰላም አስተማማኝ አድርገን ቆይተናል፡፡ የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲጠናከር ለማድረግ በሁሉም ደረጃ ያለ አመራር ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ርብረብ እንዲያደርግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ወስኗል፡፡በተለይ በመልካም አስተዳደር መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ያግዛል ተብሎ የተወሰነው የቀበሌ አስተዳደር መሰረታዊ ማስተካከያ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ወስነዋል ፡፡
በሌላ በኩል ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ለማንበርከክ ከሁሉም አቅጣጫ ሲያጋጥም የነበረው ሴራና ትንኮሳ ቀላል አልነበረም፡፡ይሁን እንጂ ቀና መንገድና ፍትሃዊ ትግል ፤በዋናነት በተከተልነው ሳይንሳዊ የትግል አግባብ ደግሞ በህዝባችን ጠንካራ የተደራጀ ትግል የጠላቶቻችን ፍላጎትና ህልም እንዳልተሳካላቸው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በዝርዝር የገመገመ ሲሆን እስከ አሁን የተገኘ ውጤት ለወደፊት ለማስፋትና ለማጠናከር የሚያስችል አቅጣጫ አስቀመጧል ፡፡

ህዝባችን ተጠራቅሞ የነበረ ችግር እንዲፈታ፤ግዜ የለም በሚል መንፈስ ፈጣን ለውጥ እንዲመጣ ፣ሓላፊነት በተሞላበት መንገድ እያደረክ ያለው እንቅስቃሴ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ይገነዘባል፡፡እንዲህ ዓይነት ጫና ማድረግህም ተገቢ እና መደረግ ያለበት ነው፡፡በተለይ የወጣቱ የስራ እደል በመፍጠር ፣በገጠርም ሆነ በከተማ የመሬት አስተዳደርና ካሳ የሚታዩ ችገሮች በፍጥነት እንዲፈቱ ቀልጣፋ ጥረትና ርበረብ ሊደረግ ይገባልክ፡፡በዚህ ምክንያትም በሁሉ አከባቢዎች ያሉ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ዝርዝር አሰራር ይዘን እንድንቀሳቀስ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የላቀ ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቶ መፍትሄ አስቀምጧል፡፡

ቢሆንም በቅርብ ጊዜ የህዝቡን ልማት ፣ ጥያቄና ትግል ሌላ ትርጉም በማስያዝ ለዘመናት የዘለቀውና በአሁኑ ወቅት ተጠናክሮ የቀጠለውን አንድነት እድል አገኘን ብለው ለማደፍረስ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡የትግራይን ህዝብና ደርጅቱ ህወሓትን ፊት ለፊት ገጥመው ማንበርከክ ያልቻሉ ሃይሎች ሌላ አዋጭ ይሆናል ያሉትን ይዘው ክፍተት ለመፍጠር እየትንቀሳቀሱ ነው፡፡በትግራይ ውስጥም ተላላኪ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት የለም ባይባልም በአጭር ጊዜ ይህንን ይዞ በትግራይ ህዝብ ላይ ዝለል ሲባል የሚዘል ሃይል ለማግኘት ይቻላል የሚል ግምት በትግራይ ህዝብ ቀርቶ የሚያሰማሩ ሃይሎችም የሚገምቱት አልነበረም፡፡ የተለየ ሃሳብ ይዘህ ወደ ህዝብ መቅረብና መታገል አስፈላጊና መሆን የሚገበው ቢሆንም የትግራይን ህዝብ ደህነነት ወደ ገበያ ማስገባት ግን ታሪካዊ ክህደት ነው፡፡ በስመ ፖለቲካ ወደ ንግድ የተሰማሩ እንክርዳዶች በትግራይ ህዝብ ዋጋ የግል ፍላጎታቸው ለማርካት ሲሉ የህዝባችን አንድነትና ፅናት ሊበርዙ ጥረት እያደረጉ ነው። ከደቡብ ይሁን ከሰሜን የተላኩ ባንዳዎች ይህን እኩይ ተግባራቸው ለመፈፀም ተደልለው እየተንቀሳቀሱ ነው።

Related stories   ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር ፌዴራል ፖሊስ ተግባሩን ያጠናክራል

ህዝባችን ይህ አፍራሽ ተግባር፣ እንደተለመደው አንድነትህን በማጠናከርና ለደህንነትህንና ለህልውናህ ቅድምያ ሰጥተህ በፅናትና በቆራጥነት ልትታገላቸው ይገባል። የነዚህ ሓይሎች ተግባርና ፍላጎት ሌላ መልክና ሽፋን ይዞው ሲመጡም፣ እንደየመልካቸው በጥናት ልትታገላቸው ይገባል። ለማይቀረው ድል አንድነትህ አጠናክር፣ በድርጅትህና መስመርህ ጎን ተሰልፈህ ለሁሉም ጉዳዮች በንቃትና በተጠንቀቅ እንደሚትከታተለው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አይጠራጠርም። በእኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ወገኖች ደግማችሁ ደጋግማችሁ እንድታስቡ፣ ከሁሉም በፊት ለህዝባችን ደህንነት ቅድሚያ ሊትሰጡ ይገባል። ጨለማ ተገን በማድረግ እናደርገዋለን ብሎ ማሰብ ግን ከንቱ ነው። የሚጠይቀው ወጋም ከባድ ነው። የሚሰማና የሚያይ መንግስትና ህዝብ ያለው ክልል ነው። ስለዚህ ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በድጋሜ ምክሩን ይለግሳል።
የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በጥልቀት ከተመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ያለዉ የአገራችን ችግር፣ አገራችን ወደማያባራ አደጋ የሚያስገቡ ችግሮች በመጠንም በስፋትም እጅግ በሚያሰጋ ሁኔታ የጨመረበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ባለፉት 27 አመታት አገራችን በመሰረቱ የተረጋጋ ሰላም በማረጋገጥ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ፈጣን፣ ተከታታይ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ እድገት ተመዝግበዋል። የአገራችን ክብርና ልኣላዊነት አስጠብቀን፣ በአገራችን ህዝቦች ጽኑ ፍላጎት የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መገንባት ጀምረን እንደነበርን፤ እስካሁን የተመዘገቡ ፈርጀ ብዙ ድሎች ምስጥር ምን እንደሆነና እንዳልሆነ ማእከላይ ኮሚቴ በጥልቀት ገምግሟል።
ከቅርብ አመታት በተለይ የኢህአዴግ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ከተኮላሸበት በኋላ፤ በአገራችን ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት የሰላም እጦት መስፋፋቱ፣ መረጋጋት እየጠፋ ሁከትና ግርግሮች በስፋት እየጨመረ መምጣቱ፣ ህግና ስርአት ማስከበር ለምን እንዳልተቻለ፣ የሕገ መንግስቱንና የፌዴራል ስርአቱ ፀር የሆኑ ፅንፈኞች የፖለቲካ ሀይሎች አስተሳሰብ የበላይነት አግኝቶ እንደፈለጉት የሚፈነጩበት ሁኔታ ለምን እንደተፈጠረ፣የአገር ክብርና ልአላዉነት እንዲሁም የፖሊሲ ነፃነትን አስከብሮ የቆየውን ፅኑ እምነትና ስርአት ለምን በፍጥነት እየተሸረሸረ እንዳለ፣የተጀመረዉን የልማትና የፀረ ድህነት ትግል ወደ ኋላ ተቀልብሶ ቁልቁል መውረድ ለምን እንዳጋጠመ፣ዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ፌዴራላዊ ስርአታችን አደጋ ውስጥ የወደቀበት ምክንያት በዝርዝር ፈትሾና የዚህ መሰረታዊ ምክንያቶችና ተጠያቂ ማን እንደሆነ ሀላፊነት በተሞላውና በከፍተኛ ህዝባዊና ሀገራዊ መንፈስ ገምግሟል።

ይህ ሁኔታ እንዲፈጠርና እዚህ ደረጃ ያደረሰው ዋና ምክንያት፣መስመሩንና ስርዓቱ እንዲመራ ሀላፊነት የተሸከመው አመራር፣ ኢህአዴግ ከሚታወቅበት እና ከሚለይበት መሰረታዊ እምነቶች እያፈነገጠ፣ የአገሪቱ እውነታ ወደ ጎን በመተው ቅጥ ባጣ ደባል አመለካከት እየተበረዘ፣ አጥር ሌለው የሕገ መንግስት ጥሰት እየፈፀመ፣ ለአገራችን ህዝቦች ሙሉ ዋስትና የሰጠውን የፌዴራል ስርአት አደጋ ውስጥ የሚያስገባ አስተሳሰብና ተግባር የበላይነት እየያዘ በመምጣቱ ነው። ኢህአዴግ በ2010 ዓ/ም ባካሄደው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ ያስቀመጣቸው መሰረታዊ የግምገማ ነጥቦችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በጥብቅ ድስፕሊንና የተጠያቅነት መንፈስ ተግባራዊ ባለመደረጉና ወደ ትክክለኛዉን ባህሪውንና መስመሩ ለመመለስ ስለተቸገረ ነው ይህን ሁሉ ችግር እያጋጠመ ያለው።
ሀገር የሚበትን ተግባር ሲፈፀም፣ የህዝቦች ስቃይና መከራ እንዲበራከት ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ሀይሎች እድል እንዲያገኙ ያደረገው የኢህአዴግና የአመራሩ ችግር ነው። በመሆኑ እስካሁን ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ መኖር አለበት፣ ከዚህ ችግር የመውጫ መንገድ ደግሞ አንድና አንድ ብቻ ነው። ይኸውም ኢህአዴግ ወደ ትክክለኛውን እምነቱና ባህሪው እንዲመለስ ማድረግ ነው። ሕገ መንግስቱንና ፌዴራላዊ ስርአታችን በጥብቅ ድስፕልንና ሳይሸራረፍ ተግባራዊ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው የአገሪቱ ዋስትና ፅኑ መሰረት የሚኖረውና የሚረጋገጠው።

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

ሆኖም አሁንም እየተፈጠረ ላለው ችግር ይበልጥ የሚያባብስ፣ የአገራችን ህልውናና ክብር የሚነኩ ተግባራት ከማሰብና ከመተግበር አልቀረም። ኢህአዴግ ጀምሮት የነበረውና ተኮላሽቶ የቀረው በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴ ወደ ትክክለኛውን መስመር እንዲመለስ ከማድረግ ይልቅ፣ በቅርብ ጊዝያት አማራጭ የመፍትሔ አቅጣጫ ተብሎ እየቀረበ ያለዉ ጉዳይ፣ ኢህአዴግ በማዋህድ አንደ ሀገራዊ ፓርቲ ማድረግ የሚል ነው። በመሰረቱ የፓርቲ ውህደት ጥያቄ በተለያዩ ጊዝያት ስነሳ የነበረና በጥናት እንዲመለስ አቅጣጫ ተቀምጦ እንደነበር ግልፅ ነው። ይህ አቅጣጫ የተቀመጠው ደግሞ ኢህአዴግ ጤናማ በነበረበት ወቅት፣ በመሰታዊ የድርጅቱ እምነቶችና መስመር ላይ ፅኑ እምነት በነበረበት እና ምንም መሸራረፎች ባልነበረበት ወቅት ነው። ይሁን’ንጂ የደፈረሰና ጉራማይለ አመለካከትና እምነት የያዘ ኢህአዴግ፣ አይደለም ለውህደት ከዚህ ከቀደም ለነበረው አደረጃጀቱም የሚሆን የአስተሳሰብና ተግባር አንድነት የሌለው ኢህአዴግ ነው ያለው። በሁሉም መሰረታዊ ጥያቄዎች የፕሮግራም፣ ስትራቴጂ፣ መለያ እምነቶች በእህት ድርጅቶች መካከል አንድ የሚያደርግ አመለካከትና እምነት በሌለበት፣ ሁሉም ወደተለያየ አቅጣጫዎች በሚላጋበት ውህድ አንድ ፓርቲ ሊታሰብ የሚችል አይደለም።

አንድ የሚያደርግ የጋራ አመለካከት በሌለበት ወቅት አንድ ድርጅት እንደ ድርጅት ህልወና ሊኖረው አይችልም። አንድ የሚያደርግ አመለካከት በማይኖርበት ጊዜ ድርጅታዊ መበታተን እንጂ ውህደት ሊመጣ አይችልም። ስለዚህ ከውህደት በፊት፣ ለመወሀሃድ የሚያዋህደንን ነገሮች ልናስቀምጥ ይገባል። ቅድም ቀዳድም ፅኑና ግልፅ መለያ መስመር አጥንተን ልንይዝ ይገባል። ኢህአዴግ እንዲበተን ከሚያደርጉ የተዛቡ አመለካከቶች የሚለይ ዶብ፣ አጥር፣ በግልፅ አስቀምጦ ግልፅና ፅኑ ስርአት አስቀምጦ ብቻ ነው ስለ ውህደት መነጋገር የምቻለዉ። የፓርቲዎች ውህደት በፍፁም ዴሞክራሲያዊ ሂደት ማለፍ ይኖርበታል።በሁሉም እህት ድርጅቶችና መላ አባላት ዴሞክራሲያዊ ውይይቶች ሳይካሄዱ የሚፈፀም መሆን የለበትም። ስለዚህ አሁን ባለው ሁኔታ ኢህአዴግ ስለውህደትና አንድ ፓርቲ መሆን ሊታሰብ የሚችል አይደለም። ከዚህ አግባብ ውጭ የሚኖር አማራጭ ለተፈጠረው ችግር የሚያባብስ እንጂ መሰረታዊ መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል በፅኑ እናምናለን።
እቺ ትላንት ለህዝቦች ሰላምና መብት መከበር በሰራችው ስራ በዓለም ተምሳሌት የነበረች አገር አሁን ለራስዋ መሆን ተስኗት ከውጭ ሌላ የሚያረጋጋት ሃይል የሚጋበዝበት ሁኔታ እየታዘብን ነው። ህዝቦች ታግለውና መስዋእትነት ከፍለው ያመጡት የፌዴራል ስርዓታችን የሚያፈረስና አሃዳዊ ስርዓት ለመመለስ በጠራራ ፀሓይ ሲሰበክና እሱ ነው ለኢትዮጵያ አማራጭ ሲባል እየተገነዘብን ነው፡፡ ህገመንግሰት በአንደኛው ወይ በሌላኛው ምክንያት ሲሸራረፍና ሲጣስ ማየት የዕለት ተዕለት ተግባር ሆነዋል፡፡ሌላ ቀርቶ በቀጣይ ዓመት መካሄድ የሚገባው ሃገራዊ ምርጫ ህገመንግስታዊ ባልሆነ መንገድ መከሄድ አለበት የለበትም እየተባለ ነው፡፡ድርጅታችን እንደ ተለመደው ዓላማውንና መስመሩን ለህዝብ አቅርቦ ልክ እንደ ድሮ በህዝብ የተማላ ይሁንታና ድጋፍ ለመምራት የሚጥር ቢሆንም ምርጫ በተያዘለት ግዜ ማከሄድ ግን ከዚህ በላይ ነው፡፡ይህ አንድ መሰረታዊ የህዝቦች ልአላዊ ስልጣን የሚረጋገጥበት ፣ሕገ መንግስታችን በፅናት ለመተግበር ያለን ቁርጠኝነት የምናረጋግጥበት ሂደት ነው፡፡ሕገመንግስት ሲመችህ የሚተገበር፣ ሳይመች ሲቀር የሚጣስ አይደለም፡፡በመሆኑም ሕገመንግስታዊ ስርአቱ በማንኛዉም ሁኔታ መከበር አለበት፡፡ ሕገመንግስታችን ባስቀመጠው የምርጫ ስርዓት መሰረት በተያዘለት የግዜ መርሀ ግብር ሊካሄድና ‘ከእኛ እናሸንፋለን አናሸንፍም’ የህዝብና ህገመንግሰት ክብርና ልዓላውነት መቅደምና መከበር እንዳለበትና በተያዘለት ስርዓት በጥብቅ ተግባራዊ እንዲሆን ህወሓት በፅናት ይታገላል ፡፡
ብሩህ ተስፋና እድገት ጀምሮ የነበረ ሃገር ዘንድሮ ህዝቦች በሰላም እጦት እንዲሰቃዩ፣እንዲፈናቀሉ፣በጠራራ ፀሓይ ህይወታቸውና ንብረታቸው እንዲያጡ፣አሁን ነገ ምን ይፈጠር ይሆን ብለው በስጋት ተሸማቅቀው እንዲያድሩ ፣በማንነታቸው እንዲሸማቀቁ ፣ተመልሰው የሚበላና የሚጠጣ አጥተው እንዲማቅቁ ፣መጠለያ አጥተው በበረድና ፀሓይ ላይ እንዲጣሉ ከማየት በላይ የሚያስደነገጥና የሚያሳፍር ተግባር ምን ሊኖር ይችላል? በዚህ አጋጠሚ ለደረሰው ሞት፣መፈናቀልና መንገላታት የተሰማን ሐዘን እየገለፅን ተመሳሳይ ተግባር በሆነ ህዝብ ላይ እንዳይፈፀም ህወሓት ከማንም ግዜ በላይ በፅናት ይታገላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ በሃገራችን ሲታይ ለሁሉ ሃገር ወዳድ ወገናችን ሊያሳስበውና ሃላፊነት እንዲሰማው የሚያደርግ ቢሆንም የሄን እንዳይፈጠር መስዋእትነት ለከፈለው ህዝብና ደርጀት ግን ይበልጥ ያሰስበዋል፡፡በመሆኑም መላ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፣ዴሞክራስያውያን ሓይሎች፣በህገመንግስታችንናን የፌዴራል ሰርዓታችን ፅኑ አቋም ይዛቹ የምትታገሉ ሓይሎች ፣ሃገራችን አሁን ከገባችበት መከራና ችግር ለማስወጣት ተባብረን በጋራ እንድንሰራ ህወሓት ጥሪውን ያቀርባል፡፡ህወሓት እንደ ድሮው የሃገራችን ህዝቦች ወደ ቀድመው ሰላማቸው እንዲመለሱ ህገመንግስታዊና ፌዴራላዊ ሰርዓታችን በጥብቅ እንዲተገበር ከማንኛውም ጊዜ በላይ በፅናት እንደሚታገል ህወሓት በድጋሜ ያረጋግጣል፡፡
አሁን ያለው የኢትዮ ኤርትራ ሰላም በተለይ በኤርትራ ህዝብና በትግራይ ህዝብ የተጀመረው ወንድማዊ እንቅስቃሴና እስከ አሁን የደረሰበት አውንታዊ እድገት በመገምገም ለወደፊቱ ዘላቂና ዋስትና ያለው እንዲሆን ያለው ዝግጁነት የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ በድጋሜ ያረጋግጣል፡፡

Related stories   አውሮፓ ህብረት - ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ

የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ!
ሚያዝያ 04/2011 ዓ/ም
መቐለ፣

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0