“Our true nationality is mankind.”H.G.

ትግራይ ተገንጥላለች – በ”ሴራ ትርምስ” የፌደራል መንግስት ቀስፈውታል

“አጉል ሃሳብ በአዲሱ ትውልድ ላይ ሲጫን ከድግግሞሽ ብዛት እምነት ይሆናል። ያ እምነት አጉል ከመሆኑ አንጻር በጭንቀትም ይሁን በስጋት ይንጣል። በስጋትና በጭንቀት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ደግሞ መዘዝ አላቸው። ካመዘዞቹ አንዱና ዋናው አፍን መክፈትና መቀደድ ነው። መቃዠትና ማስቃዠት ያስከትላል። እናም በዚህ ቅዠት መሰረት ትግራይ ተገንጥላለች። ህዝብ ግን አልተጠየቀም። ህዝብ እንዲለምደው ነው ቅዠቱና ልፍለፋው። እንደ እኔ እምነት ” ትግራይ ያለ ህዝብ ፈቃድ ደሴት ሆናለች”  በመሃል አገር ያለው የሴራ ፖለቲካ ውጤት የሆነው መተራመስ አግዙእቸው እንጂ እስካሁን ከቅዠታቸው እንዲነቁ ወይም በደንብ እንዲቃዡ ይሆን ነበር”

… የናዚም ሆነ የፋሽስት አክራሪ የጎሳ ብሄርተኝነት ተከታዮችን ከሰውነት ተራ በመውጣት የግለሰብ ማንነታቸውን አጥፍቶ እንደ እንሰሳት መንጋ የአንድን የጎሳ ድርጅት መሪዎች በጭፍን እንዲከተሉ ያደርጋል። እነዚህ በመሪዎቻቸው ሀሳብና ትዕዛዝ በጭፍን የሚመሩ ህሊና ቢስ የተደረጉ በጎሳ ብሄርተኝነት ስሜት የሰከሩ የአንድ ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ጀሌዎች መሪዎቻቸው አድርጉ ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ ካለ አንዳች ማወላወልና ማንገራገር ይፈፅማሉ። በዚህ አይነት ህሊናቸውን ያጡ ጀሌዎች በበዙበትና ስልጣን በተቆናጠጡበት ሃገር ውስጥ ሊከሰት የሚችለው አደጋ የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት ሊቀጥፍ ይችላል፤ ሀገርን ያፈርሳል፤ ህዝብን ይበትናል። ትላንት የናዚ ጀርመኖች ፍልስፍና ገዥና ዋና አስተሳሰብ (dominant ideology) በነበረበት ግዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዳዊያን፣ እስላሞች፣ ጂፕሲዎች ወዘተ በገፍ እየተነዱ ሲፈጁ አብዛኛው የጀርመን ህዝብ ድርጊቱን ሳይቃወም እንዲያውም ሲደግፍ ታይቶ ነበር። በዛን ጊዜ በርካታ ጀርመናዊ በናዚ ጭፍን የጀርመን የበላይነት ፍልስፍና (Deutschland ueber alles) ወይም ጀርመን ከሁሉ በላይ በሚለው የአርያን የዘር የበላይነት በሚያንፀባርቅ አስተሳሰብ አይምሮው ተመርዞ ነበር። በዚህ ምክንያት የጀርመን ህዝብ በጎውና መጥፎውን የሚለይበትን ህሊናውን አሽቀንጥሮ በመጣል የራሱን ማንነት አሳልፎ ለናዚ መሪዎች በገፀ-በረከትነት ሰጠ።

ዛሬ በኢትዮጲያችን ተመሣሣይ ሁኔታ እየታየ ነው ብዬ እሞግታለሁ። የወያኔ ድርጅት ትግል ሲጀመር የዚህን ድርጅት እኩይ አላማ በመቃዎም የተገረፉ፣ የተገደሉ፣ የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉና ለነዚህም ከፍተኛ አክብሮት እንዳለኝ ልገልፅ እፈልጋለሁ። ለሀገራቸው ያደረጉትንም ውለታ አልረሳም። ይሁን እንጂ ለ17 አመታት በጦርነት እንዲሁም ላለፉት 38 አመታት ወይም 39 አመታት በፀረ-ኢትዮጵያ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ በተለይም ቀለም ቆጠረ የሚባለው ክፍል በዛሬው ወቅት የመርዘኛው የትግራይ ብሄርተኝነት ሰለባ በመሆን የዚህ ያለው ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ የወያኔ አገዛዝ ደጋፊና አቃፊ ከሆነ ውሎ አድሯል። ይላሉ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ

ኢትዮጵያ ስትበተን እኛ ቆመን እንቀራለን። ኢትዮጵያ ኮንትራት ናት። አንቀጽ ፫፱ ተመስርቶ ጋብቻ ፈጽመናል። በዚሁም ጋብቻ መሰረት እንኖራለን። የማይጠቅመን ከሆነ እንፋታለን የሚለውን አስተያየት የሰጡት የዚሁ ከላይ የተጠቀሰው የወያኔ አስተሳሰብ ተሸካሚ ከሆኑት መካከል አንዱ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ስትራቴጂ መምህር ናቸው የተባሉት አቶ መሃሪ ዮሃንስ ናቸው። ኢትዮጵያ እንደምትፈራርስ እርግጠኛ ሆነው ለአውራ አምባ  በሰጡት መግለጫ ” ሳይንቲፊካሊ ኢትዮጵያ መቀጠል ወደማትችልበት ደረጃ ደርሳለች፤ ስለዚህ በረጅም ግብና ርቀት አስበን ኢትዮጵያን የመኖርና ያለመኖር ህልውንችን አድርገን አናይም” ሲሉም ኢትዮጵያን እንደ ወላለቀች አገር ሲስሉ ታይተዋል።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

ታክቲካል የሆነ ግንኙነት ከኢትዮጵያ ጋር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ስትፈርስ ትግራይ ትቀጥላለች። መፍረስ የማይቀር ስለሆነ በሰለጠነ መንገድ በሰላምና በዕምነት መፋታት፣ ይህ እስከሚሆን ፌደራሊዝሙን የመቆያ ጋብቻ አድርገው እንደሚያዩት አቶ መሃሪ ደጋግመው ነግረውናል።  ቲክኒካል ሲሉ የገለጹት ግንኙነት ደግሞ  ትግራይን ማልማት፣ የትግራይን ሃይል መገንባት ነው። ከዚህ እሳቤ ውጪ ህወሃት ሊንቀሳቀስ ቢሞክር ” ቀፍድደን እንይዘዋለን” ሲሉ አስጠንቀቀዋል።

አማራጭ የሌለውና ለድርድር የማይቀርበው ግን በግልጽ የማይጠሩት ግን “ደርግ” / አማራውን ነው/ ሲሉ የሚጠሩትት ሃይል አራት ኪሎ የሚገባ ከሆነ አዲስ አበባ ድረስ በመምጣት ማባረር ነው። ይህ የሚሆነው ተመልሶ አራት ኪሎ ለመግባት ሳይሆን ደርግን ለመበተን ነው። አቶ መሃሪ በተደጋጋሚ በአዲስ አበባ ጉዳይ እንደማያገባቸው፣ ሊጨነቁ እንደማይገባ፣ ከኢትዮጵያ ጋር ስትራቴጂካል ግንኙነት እንጂ የፍቺው ጉዳይ እንደማይቀር እየተናገሩ መልሰው በምርጫ ለእነሱ የሚጠቅማቸውን ሃይል መምረጥ እንዳለባቸው ለወዳጆቻቸው የትግራይ ተወላጆች መክረዋል። ይህ እርስ በርሱ የሚቋሰል አስተሳሰብ ምን የወለደው እንደሆነ ባይታወቅም በኦሮሞ ላይ እምነት እንዳላቸው፣ ለኦሮሞ እንደሚታገሉ፣ እንደሚያግዙ፣ ይህም ከፍትህ አንጻር እንደሆነ ይሞግታሉ።

የትግራይ ተወላጆች ትግራይ ላይ ብቻ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የመከሩት አቶ መሃሪ የገበያ ቦታ እንደሚያስፈልጋቸው ግን አልሸሸጉም። በዚህም አስተሳሰባቸው ትግራይን በኢንደስትሪ አሳድጎ ሌሎች ክልሎችን የገበያ መዳረሻ ለማድረግ አቶ መለስ ወጥነውት ሲንቀሳቀሱ የነበረውን ህልም ፍንትው አድርገው አሳይተዋል። የዚሁ የገለማ የዝርፊያ አስተሳሰብና ስትራቴጂ ተጠቂ መሆናቸውን በይፋ አሳይተዋል። የሰውየው ግልልጽነት ከጭንቀት ይምጣ አማራጭ ከማጠት በውል ባይታወቅም፣ ኢትዮጵያን ከማንቋሸሽ አልፈው ለትግራይ ” ህልም ” እስካልጠቀመች የማታስፈልግ ኢምፓየር እነድሆነች እየተወራጩ ተናግረዋል።

ከትናንት በስቲያ ጉባኤውን ያጠናቀቀው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ሲጀመር ጀመሮ ፌደራሊዝምና ህገ መንግስቱ ሲል የሚወተውተው ከላይ ከተቀመጠው ” ኢትዮጵያ ኮንትራት ናት” ሲሉ አቶ መሃሪ በድፍረት ከሰጡት ማብራሪያ ጋር የሚሳሳም፣ ገዢ የሆነ የስትራቴጂው ምሶሶ መሆኑንን የሚያረጋግጥ ነው።

ኢህአዴግ ፈርሶ አጋር የሚባሉትን ድርጅቶች በማካተት አገራዊ /ብሄራዊ ፓርቲ የመሆኑንን ውሳኔ እንደሚነቀፉ ያስቀመጡት ምክንያትም በአጭሩ ” የኮንትራት ውላቸው” እነሱ ባልፈለጉት መንገድ እንዳይበጠስ ከመጓጓትና ከመስጋት የተነሳ ነው።

በቅረቡ በሃገሪቱ አንድ ፓርቲ  ለመመስረት የቀረበውን ሃሳብ  በተመለከተ ውህደቱ ከመፈጸሙ በፊት  ሊያዋህዱ የሚችሉ ተግባራት መከናወን እንዳለባቸው እምነት እንዳለው የገለጸው ማዕከላዊ ኮሚቴው፥ ሁሉም እህት ድርጅቶችና  መላው አባላቱ ሰፊ ዴሞክራሲዊ  ውይይት ማካሄድ እንዳለባቸውም ያሳሰበው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት፣ ይህ እስካልሆነ ድረስ ውህደቱ እንደማይታሰብ ይፋ አድርጓል። የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ለህገ መንግስቱና ፌደራል ስርዓቱ ጽኑ እምነት በመያዝ  “ታገሉልኝ” ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

ህወሃት ስትራቴጂውን ለማስፈጸምና ” የትግራይን ሕልም” እውን ለማድረግ የሚከተለው ስልት መከፋፈል እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚነገር ነው። ዛሬም ለውጡ ከመጣ በሁዋላ የሚታየው ይህ ነው። የአማራ ክልል የጸጥታ ሃላፊ ኮሎኔል አለ በል ለቪኦኤ ሲናገሩ ” እኛ ካልገዛን” በሚል ከግጭት ጀርባ እጃቸው እንዳለ በተዘዋዋሪ ተናግረዋል። በዚሁ መነሻ የትግል ጥሪ የተላለፈላቸው የብሄር ብሄረሰብ ድርጅቶች ተከፋፍለው ከጎኑ እንዲቆሙለት ነው።

በቅማንት ዘመናዊ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያ ታጥቆ ሲያሸብር የነበረውን ሃይል ህወሃት እንዳደራጀውና እንዳስታጠቀ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሶማሌ ክልል፣ እንዲሁም ባልተበጣጠሰው የሃያ ሰባት ዓመት መዋቅሩ አማካይነት ለውጡን በጀት መድቦ እየሸረሸረ ለመሆኑ የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች ” የሴራ ፖለቲካ” ሲሉ ለህዝብ በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው።

ትግራይ ሕልም አላት። በሕልሟ ልክ አገራዊ ተቋማት ያስፈልጋታል። ኢትዮጵያ ይህንን ማድረግ ካልቻለች፣ ወይም እነሱ የሚነዷት ባቡር ካልሆነች በዚሁ የሴራ ፖለቲካ እንደሚገፉበት ጥርጥር የለም። ገና ገና ምቼ ተነካና!!

ከህወሃት ጉባኤ ከተሰማው መግለጫ ውጭ ምንም አልጠብቅም ነበር። የሚያሳዝነው ህወሃት ከኢህአዴግ ህብረትና ከፌደራል ስርዓቱ ካፈነገጠ ቆይቶ ሳለ፣ አልገዛምና አልታዘዝለትም ያለውን መንግስት ሲተች፣ በጀት ሲጠይቅ፣ ሌሎች እንደሱ እንዲያፈነግጡ ለማስተባበር በገሃድና በህቡዕ ሲሰራ ዝም መባሉ ነው።

አቶ መሃሪ እንዳሉት “ህወሃት እንደ ሰራቂ ውሽማ” ወደ መቀሌ ሸሽቶ ህግና ህገመንግስት እንደማይመለከተው በተግባር እያሳየ ” ህገመንግስት ይከበር” እያለ የሚጮኸው ያደረ ህልሙን ለማሳካት ጊዜ መግዣ እንጂ የትኛውንም የብሄረሰብ ክፍል ለመጠቀም አይደልም። እዚህ አልይ አዲሱ የሶማሌ ክልል መሪ ሙስጣፋ ያሉት በቂ ምስክር ነው። ” ብርድ ብርድ ያላቸው” ነበር ያሉት። “እኛ ወንጀለኛ አልሸሸግንም፣ የመከላከያ ሰራዊት አላገትንም” ሲሉም አክለዋል።

ህወሃት አደብ እንዳይገዛ የሚረዱት የሴራ ፖለቲካቸው ተሸካሚ የሆኑ ሃይሎች ናቸው። በመሃል አገርና በመላው አገሪቱ ሰላም ከሰፈነ የፌደራል መንግስቱ እነሱን የማንበርከክ ስልታዊ አካሄድ እንደሚሄድ ህወሃት ጠንቅቆ የሚያውቀውን ያህል ሌሎቻችን አልተረዳነውምና የሚከፈለውን ዋጋ አበዛው። ጊዜም ወሰደ። በዚህ መሃል አገር እየመራ ያለው ሃይል ላይ የብቃት ችግር እንዳለበት የስብከት ዘመቻ ለማጧጧፍ አመቺ ሁኔታ ተፈጠረ። ያገኘውን ሁሉ የሚያመነዥገው የመረጃ ረሃብተኛ ለዚህ ሴራ ሰለባ ሆኖ ወገኑን በላ፣ እየበላ ነው፤ ወደፊትም ….

ከለውጡ በፊት ኦህዴድን እንደገና በማደራጀት ጊዜ ለመግዛት የሞከረው ህወሃት እውስጥ ባሉ የለውጥ ሃይሎች ግድግዳ ተሰርቶበት ከነበረበት የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት ተከሰከሰ። ባላሰበውና ባልጠበቀው መልኩ ብአዴንና ኦህዴድ ደቡብን በከፊል ይዘው አንገዋለሉት። ከስልጣን የተፈነቀለበት ውጥን የሚያስበረግገው ህወሃት እሱ በለውጥ ሃይሎች ጊዜ ተከልክሎ ስልጣኑን እንዳጣ ሁሉ፣ አሁን ላለው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ጊዜ ነፈገ። ለሃያ ሰባት ዓመት የዘረጋውን ድር እየተጠቀመ መርዙን በረብጣ ብር እያሸገ በተነ።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

በዚህም እሳቤው አሰቀድሞ ሲከራከርበት የነበረውን የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተበት ነው። በመጨረሻዎቹ ሰዓታት የህወሃት ጀነራሎችና ሃላፊዎች አሜሪካንን ” እኛ ከወረድን አገሪቱ ትፈራርሳለች፣ ምስራቅ አፍሪቃ ትናጣለች፣ ማሻሻያ አድርገን እንድንቀጥል እርዱን” በማለት ቢማለዱም ” እንደ እናንተ ያታለለን የለም” በሚል ሰሚ አጥተው ተባረዋል።

ይህ ” እኛ ከሌለን” የሚለው እሳቤ ከወደቁም በሁዋላ ቢሆን ከፍተኛ ገንዘብ እያፈሰሱ የሚያራምዱት አቋማቸው ነው። ህዝብ እንዲፈናቀል፣ እርስ በርስ እንዲጋጭ፣ እንዲጋደል በጀት መድበው እየሰሩና በቂ መረጃ እየቀረበባቸው ባለበት በአሁኑ ወቅት ” በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እያጋጠመ ባለው ሞት፣  መፈናቀልና እንግልት የተሰማንን ሃዘን እየገለጽን በቀጣይ በህዝብ ላይ ተመሳሳይ ተግባር እንዳይፈፀም የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመቸውም በላይ በፅናት ይታገላል” ማለቱ ያስገርማል።

” ኢህአዴግ አንድ ነገር ያውቃል፣ እኛም ይገባናል፣ የትግራይ ምስኪኑ ህዝብ ግን አልተረዳም” የሚሉ አሉ። እኔም እስማማለሁ፣ ይህም በመርህ ደረጃ ህወሃት ከድርጅቱ መባረሩን ነው። በቀጣዩ ጉባኤ ኢህአዴግ ይፈርሳል። ይህ እንዲሆን ከውጭና ከውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ አለ። ድርጅቱ ከፈረሰና አገራዊ ፓርቲ ከሆነ ህወሃት ብቻውን የተገንጣይና የነጻ አውጪ ስም ይዞ ይቀራል። ይህ ሲሆን ለአብላጮች ተገዝቶ መኖር፣ አለያም በወጉ ህዝቡን አሳምኖ መለየት ምርጫው ይሆናል። አለያም በአብላጮች ድምጽ ህጉ ይቀየርና …..

በወጉ እንዲለይ ሲደረግ ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር የጎረቤት አገር አይነት ግንኙነት ይመሰርታል። ለሚፈልገው ጥቅም ሁሉ በውጭ ምንዛሬ ይከፍላል። በምስራቅ አፍሪቃ የሚተገበረው አዲስ አሃሳብ፣ የሱዳን መንግስት መውደቅ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ስትራቴጂክ ግንኙነትና የባለጸጋዎቹ ፍላጎት ተዳምሮ … “ታላቋ ትግራይን ያያቹህ ፣ በለህልሟን ትግራይ ያያቹህ፣ ታላቅ ነበርን ታላቅ እንሆናለን… ” የሚለውን ዜማ እንሰማለን። ይህ እንደሚሆን ስለሚረዱ ገና ያተራምሱናል። አለመተራመስ የቀሪው ኢትዮጵያዊያን ምርጫ ነው። በሰላም መኖርና ወደ ልማት መዞር!! ምክንያቱም እንደ እኔ እንደ እኔ ትግራይ ከህዝብ ፍላጎት ውጪ ተገንጥላለች።

“አጉል ሃሳብ በአዲሱ ትውልድ ላይ ሲጫን ከድግግሞሽ ብዛት እምነት ይሆናል። ያ እምነት አጉል ከመሆኑ አንጻር በጭንቀትም ይሁን በስጋት ይንጣል። በስጋትና በጭንቀት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ደግሞ መዘዝ አላቸው። ካመዘዞቹ አንዱና ዋናው አፍን መክፈትና መቀደድ ነው። መቃዠትና ማስቃዠት ያስከትላል። እናም በዚህ ቅዠት መሰረት ትግራይ ተገንጥላለች። ህዝብ ግን አልተጠየቀም። ህዝብ እንዲለምደው ነው ቅዠቱና ልፍለፋው። እንደ እኔ እምነት ” ትግራይ ያለ ህዝብ ፈቃድ ደሴት ሆናለች”  በመሃል አገር ያለው የሴራ ፖለቲካ ውጤት የሆነው መተራመስ አግዟቸው እንጂ እስካሁን ከቅዠታቸው እንዲነቁ ወይም በደንብ እንዲቃዡ ይሆን ነበር። ዳሩ ምን ያደርጋል ትግራይ ተገንጥላለች፣ የ “ሴራ ትርምስ” የፌደራል መንግስትን ቀስፈውታል ” ህዝብ አቋም ይዞ የሚያተራምሱትን ወግዱ አለማለቱ ጊዜ ሰጠ!!

ዝግጅት ክፍሉ

ይህ ጽሁፍ የአቅራቢ ሃሳብ ብቻ ነው

 

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0