የጀርመኑ አንጋፍ የእግር ኳስ ክለብ ባየር ሙኒክ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ አካዳሚ እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡ ይህንን በማስመልክትም የፊታችን ረቡዕ በአዲስ አበባ ስታድየም የእግር ኳስ ጨዋታዎች እንደሚካሄዱ ክለቡ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።

በዚህም ስምንት የታዳጊ እግር ኳስ ቡድኖች እርስ በእርስ የዋንጫ አሸናፊ ለመሆን ይጫወታሉ ተብሏል፡፡ ክለቡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ሀላፊዎች እና የክለቡ የክብር እንግዳዎች በተገኙበት ያስመርቃል ተብሏል፡፡

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክለቡ የቀድሞ ተጫዋች ጆቫኒ ኤልበር ክለቡ በጀርመን ቡንደስሊጋ ያገኘውን ዋንጫ በመያዝ እንደሚሳተፍ ተነግሯል፡፡ ሆኖም ይህ የእግር ኳስ ትምህርት ቤት የት አካባቢ እንደሚገነባ የተባለ ነገር የለም።

FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *