“Our true nationality is mankind.”H.G.

የሰሜን ብሄራዊ ፓርክን ሰደድ እሳት በሄሊኮፕተር መታደግ ተጀመረ፤ እሳቱ መጥፋቱ አዘናግቷል

ቀደም ሲል እሳቱ በሰው ሃይል በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ በመሆኑ ሄሊኮፕተር ለማስመጣት ተጀምሮ የነበረውን እንቅስቃሴ እንዲቆም ቢደረግም ዛሬ በሰሜን ብሄራዊ ፓርክ የተነሳውን የእሳት አደጋ በሄሊኮፕተር በመታገዝ የማጥፋት ስራ መጀመሩ ታላቅ ተስፋ መሆኑ ተገለጸ።

ከኬንያ ለዚሁ ተግባር የገባችው ሄሊኮፕተር ታሪካዊ የኢትዮጵያ ቅርስ የሆነውን የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ የመታደግ ስራዋን ከመጀመሯ አስቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ” ለሁሉም ንገሩ ፓርኩ እየወደመ ነው” ሲል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ሰጥተው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከእስራዔል አቻቸው ጋር ባደረጉት ንግግር የእስራኤል አስራ ሁለት የዘርፉ ባለሙያዎች ጎንደር ገብተው እሳቱ ወደተነሳበት አካባቢ አቅንተዋል። እስራኤል በዘላቂነት ስልተናና እገዛ የምታደርግበት መንገድ እንደሚመቻችም ታውቋል። ለጊዜው ይፋ አይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜያት ውስጥ ተመሳሳይ አደጋ ቢከሰት ፈጥኖ ለማጥፋት የሚያስችላትን የሰው ሃይልና መሳሪያ ባለቤት እንድትሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከወዳጅ አገራት ጋር እየመከሩ መሆኑን በጀርመን የሚኖሩ ዲፕሎማት ለዛጎል ተናግረዋል። ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።

የአማራ ክልል ደንና ዱር እንሰሳት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክትር ባላይነህ አየለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮፖሬት እንደገለጹት ሄሊኮፕተሯ ደባርቅ አካባቢ ውሃ የመያዝና የመርጨት ሙከራዋን ካደረግች በኋላ ነው በሰሜን ብሄራዊ ፓርክ እሳት በማጥፋት ስራ የተሰማራችው፡፡

በፓርኩ አካባቢ ያሉ የውሃ አማራጮች ለመጠቀም ከፓርኩ ሰራተኞች ጋር ግንኙነት ከተደረገ በኋላ ሂሊኮፕተሯ ወደ እሳት አደጋ ቦታው መሰማራቷን ነው ዶክተር በላይነህ የተናገሩት፡፡

ለዚሁ ተግባር ከኬንያ ዛሬ ጠዋት የገባችው ይህችው ሄሊኮፕተር ከ1ሺህ እስከ 1ሺህ 200 ሊትር ውሃ የመያዝ አቅም አላት ተብሏል፡፡

12 አባላት ያሉት እስራኤል የሰደድ እሳት አደጋ ሙያተኞች ቡድን ዛሬ ጠዋት ጎንደር የገባ ሲሆን ÷ ወደ ስፍራው ለማቅናት በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ እስራኤል የኢትዮጵያ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው የባለሙያዎች ቡድኑን የላከቸው።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ባለፈው አርብ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከእስራኤል አቻቸቸው ብኒያሚን ንታኒያ ጋር በእስራኤል ድጋፍ ዙሪያ በስልክ መወያየታቸውንም ነው ያመለከቱት።

12 አባላት ያሉት ይህ የባለሙያዎች ቡድን ከእስራኤል የእሳት አደጋ ብርጌድ የተውጣጣ ሲሆን፥ በሰደድ እሳት ከፍተኛ እውቀት እና ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች መሆናቸውን ምክትል አምባሳደሩ አስታውቀዋል።

ቡድኑ የሰደድ እሳቱ ወዳለበት ስፍራ በማቅናት እሳቱን የመቆጣጠር ጥረትን ያግዛሉ ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሄሊኮፕተሮችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ትናንት ማምሻውን መግለፁ ይታወሳል።

————————————————————————————————————————-

በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ ዛሬ ረፋድ ለአብመድ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያና የእስራኤል መንግሥታት ትብብር የባለሙያዎቹ ቡድኑ ተልኳል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሆ በጉዳዩ ዙሪያ ባለፈው ዓርብ በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ ነው የባለሙያዎቹ ቡድን የተላከው፡፡

የባለሙያዎች ቡድኑ ከእስራኤል የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል አገልግሎት የተውጣጣ 10 አባላት ያሉት ሆኖ አንደኛው የቡድኑ ሐኪም ቀሪዎቹ ግን የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ቡድኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሆ ትዕዛዝ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንቅስቃሴውን እንደሚያስተባብሩት መግለጫው ያሳያል፡፡

ቡድኑ ጎንደር ሲገባ የተቀበሉት የአማራ ክልል የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ የክልሉ መንግሥት ለባለሙያዎች ቡድኑ የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጅቶ መጠበቁን ገልጸዋል፡፡

የባለሙያዎች ቡድኑ የእሳት ቃጠሎውን ሁኔታና አጠቃላይ መልክአ ምድሩን የተመለከቱ ሀቆችን በመመልከት ተጨማሪ ድጋፍ በምን መልኩ እንደሚደረግ የሚያሳውቅ ነው፡፡

የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴርም የባለሙያዎች ቡድን የእሳቱን ሁኔታ ተመልክቶ የሚሰጠውን ምክር ሐሳብ በፍጥነት ለመተግበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ከ1ሺህ 200 እስከ 1ሺህ 300 ሊትር ውኃ መሸከምና መርጨት የሚችል የኬንያ የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተርም ጎንደር መግባቱን ዶክተር በላይነህ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ሄሊኮፕተሩ ውኃ የሚቀዳበት ቦታም መለዬቱም ታውቋል፡፡ ሄሊኮፕተሯ ከደቂቃዎች በፊት ወደ ፓርኩ አቅንታለች፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ – ከጎንደር

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 06/2011ዓ.ም (አብመድ)

Image may contain: 1 person, smiling, beard

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0