ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በርካታ ማከፋፈያዎች ያሉት ሸዋ ዳቦ ከመንግስት ጋር የነበረውን ትስስር በመተው የዋጋ ጭማሪ አድርጓል።

ሸዋ ዳቦ በረጅም ዘመን አገልግሎቱ እና በምርቱ ጥራት ሲወደስ ቢቆይም ከሚያዚያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ ቅሬታን አስነስቷል።

ድርጅቱ ባለ መቶ ግራሙን ዳቦ ከ1 ብር ከ30 ወደ 2 ብር ከ50 ሳንቲም እንዲሁም ባለ 200 ግራሙን ደግሞ ወደ 5 ብር ዋጋቸውን ከፍ አድርጎታል።

ለዚህም በመንግስት በድጎማ የሚቀርበው ስንዴ መቆራረጥን ተከትሎ በግሉ ከገበያ በገዛው ስንዴና ዱቄት አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ መወሰኑን የድርጅቱ የአስተዳደር፣ ምርትና ቴክኒክ ሀላፊ አቶ ግርማ ታደሰ ተናግረዋል።

በስንዴ አቅርቦት ችግር ምክንያት 40 ሚሊየን ብር የወጣበት ዳቦ መጋገሪያ ማሽን ስራ ማቆሙንም አስታውሰዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ባለው ገበያ ስንዴ በኩንታል እስከ 1 ሺህ 700 ብር ሲሸጥ በውጭ ሀገራት ግን ከትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎች ውጭ 550 ብር በሚደርስ ዋጋ ይገኛል።

እናም ሀገሪቱ በየአመቱ በገፍ ስንዴን ከውጭ እያስገባች ለህብረተሰቡ ዳቦ እና ዱቄት መንግስት በሚቆርጠው ዋጋ ለሚያቀርቡ አምራቾች እና አከፋፋዮች በድጎማ ታቀርባለች።

በዚህም ህብረተሰቡም ሆነ አምራቾች ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው የንግድ ሚኒስቴር የሚገልፀው።

ሸዋ ዳቦ ግን የሚቀርብለት የድጎማ ስንዴ በቂ አለመሆኑንና በፍጥነት እንደማይደርስለት በመጥቀስ በድጎማ ስንዴው ምርት እያመረቱ በመንግስት በተቆረጠ ዋጋ ማቅረብ አዋጭ አይደለም በሚል ከንግድ ሚኒስቴር ጋር ውሉን ቀዷል።

የንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ወንድሙ ፍላቴ፥ ሚኒስቴሩ የድርጅቱን ውሳኔ እንደሚያከብር ጠቅሰው ስራው ትርፋማ መሆኑን ራሱ ድርጅቱ ባጠናው ጥናት አረጋግጧል ይላሉ።

ከዋጋ ጭማሪው ጋር በተያያዘም በነፃ ገበያ መርህ ሸዋ ዳቦ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደሚችልና አቅሙ ያለው መግዛት እንደሚችል ጠቁመው፥ ሚኒስቴሩም ጭማሪው በሰፊው ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ችግር እንዳይፈጥር እየሰራ ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ በተለይም በአዲስ አበባ የመንግስትን የዋጋ ድጎማ በመጠቀም በተተመነው ዋጋ ዳቦ እና ዱቄት የሚያመርቱ ተቋማት ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ መድረሱንም ገልጸዋል።

የንግድ ሚኒስቴር በየወሩ ከ600 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ በመላ ሀገሪቱ በድጎማ የሚያሰራጭ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ከ160 ሺህ በላዩ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎች የሚሰራጭ ነው።

አሁን ላይም ይህ አቅርቦት እንዳይቋረጥ እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ከግዥ ስርዓት መጓተት ጋር በተያያዘ አቅርቦቱ በቂ አለመሆኑንም ይገልጻሉ።

በዚህ በጀት አመትም 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ገዝቶ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው ያለው ንግድ ሚኒስቴር፥ ከመንግስት ጋር ትስስር ለፈጠሩ የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎች በድጎማ የሚቀርበው ስንዴ አይቋረጥምም ብሏል።

በቅርብ አመታት ውስጥ ግን የሀገሪቱ የግብርና ምርታማነት በማሳደግ ከውጭ በመንግስት ድጎማ የሚገባውን ስንዴ ለማስቆም አቅጣጫ መቀመጡንም አስታውቋል

ሸዋ ዳቦ ከመንግስት ጋር የነበረውን ትስስር በመተው የዋጋ ጭማሪ አድርጓልአዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 7 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በርካታ ማከፋፈያዎች ያሉት…

Публикувахте от FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) в Понеделник, 15 април 2019 г.

ኤፍ ቢ ሲ)

በፋሲካው ታደሰ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *