የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአድዋ ድልን የሚዘክር ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ።

የከተማ አስተዳደሩ የዓድዋ ድል እና አጠቃላይ የጦርነቱን ሁናቴ የሚገልፅ ማእከሉን በቅርቡ ከሚድሮክ ተመላሽ በተደረገው እና የሃገራች ከተሞች ርቀት መነሻ ቦታ ወይም 0 ኪሎ ሜትር በሆነው በጥንታዊ መጠርያው ሲኒማ አድዋ በመባል በሚታወቀው ቦታ ላይ ለመገንባት የምክረ ሃሳብ አዘጋጅቷል።

 

በምክረ ሃሳቡ ላይ የታሪክ ምሁራን፣ የኪነ ህንፃ ባለሞያዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመነሻ ሃሳቡ ላይ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።

Related stories   “ወያኔ እየሠራው ባለው ግፍና በደል ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ እየተቆለለባት ነው!”ሲሉ ሰምቼ…

ይህ ሊገነባ የታሰበው ማዕከል ከሚኖረው ማህበረ ባህላዊ ፋይዳ በተጨማሪ በውስጡ በጊዜው የነበሩ አልባሳት፣ ጥቅም ላይ የዋሉ የጦር መሳርያዎች፣ ከቅስቀሳው ጀምሮ እስከ ጦር አውዱ የተዘገቡ ማናቸውም ጉዳዮች የሚሰነዱበት እና ለዕይታ የሚበቁበት ስፍራ ይሆናል ተብሏል።

በጋሻ መልክ የሚነገባው ማዕከል ተገንብቶ ሲያልቅ “ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!” የሚል የአዲስ አበባ ከተማ ‘ዜሮ ኪሎ ሜትር’ ምልክት እንደሚጠቀምም ታውቋል።

Related stories   Ethiopia: Lies, Damn Lies, Axum and the West – by Jeff Pearce

ማዕከሉ ግንባታው ሲጠናቀቅ በውስጡ ቤተ መፅሃፍት፣ ቤተ ስዕል፣ የህፃናት ማቆያ፣ የክዋነ ጥበባትና የሲኒማ አዳራሽ፣ የስፖርት ማዘውተርያዎች፣ ሱቆች፣ ካፌዎች እና የምግብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደሚኖሩትም ተገልጿል።

የማዕከሉ የውጪ ይዞታም ለመዝናኛ የተመቸ ለቱሪስት መስዕብነት የሚያገለግል ሲሆን፥ አረንጓዴ እና ነፋሻማ የሆነ አከባቢን በመፍጠሩ ሂደትም ጉልህ ሚና የሚጫወት ይሆናል ተብሏል።

የማዕከሉ ግንባታ የአገራችን ህዝቦች ከልዩነት ይልቅ በአንድነት አገራቸውን እንዲገነቡ ታላቅ ምሳሌ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Related stories   Sisi warns Ethiopia against continuing to fill Nile Dam during visit to Sudan

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በምክረ ሀሳቡ ላይ እንደተናገሩት፥ የማእከሉ ግንባታ በአንድ ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው።

ማእከሉን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅም አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

ማዕከሉ የመላው ኢትዮጵያዊያን በመሆኑ ለመነሻ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ህብረተሰቡ በቀጣይነት ሃሳብ እንዲሰጥበት የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል።

FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *