“Our true nationality is mankind.”H.G.

ህወሃት – ባንዳ፣ እንክርዳድ፣ ሰይጣን የሚሉ ፍረጃዎችን ለገበያ አቀረበ፤

የህወሃት ወቅታዊ ቁመና ሶስተኛው ደረጃ ላይ መድረሱን ጉዳዩን የሚከታተሉ ይናገራሉ። ለውጡ እንደመጣ ሕዝብ የሚለውንና የሚያቀርበውን መቀበል፣ እርምት እንደሚደረግ መግለጽና ይቅርታ በመጠየቅ ማስተናገድ ነበር። ከመሃል ፖለቲካ የተሽቀነጠረው ህወሃት ጎንበስ ብሎ ትግራይ ከገባ በሁዋላ ስልጣን ለተተኪዎች እስከመስጠትና ዴሞክራሲ በክልሉ ተግራዊ እንደሚደረግ ሲምሉና ሲገዘቱ ነበር።

ከቆይታ በሁዋላ ” ተከበናል፣ ተወረናል፣ አማራና ሻዕቢያ አንድ ላይ ሊወጉን ነው…” የሚሉ ቅስቀሳዎችን ጀመሩ። በዚህም ቅስቀሳ ህዝብ እንዲፈራና አማራጩ ህወሃት ብቻ እንደሆነ እንዲያስብ አደረጉት። በዚህም ቅስቀሳ ህወሃት ህዝብ ውስጥ ገባ።

አሁን ዛሬ ላይ ” ሰይጣኖች፣ ባንዳዎች፣ እንክርዳዶች፣ የፖለቲካ ነጋዴዎች፣ የመሃል ፖለቲካ ተላላኪዎች…” በሚል ፍረጃና ማስፈራራት ጀመረ። የህወሃት ጉቤኤ እንደተጠናቀቀ በትግራይ መገናኛዎች የሚሰራጩ አስተያየቶች እነዚህን አዳዲስ የፍረጃ ቃላቶች የሚያስተናግዱ ሆነው ነበር የሰነበቱት።

ከውስጥ የሚነሳው ችግር አደገና እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚያሳዩ አስተያየቶች ፣ ከውጪ ከሻዕቢ ጭምር የሚቃጣ ማንኛውንም ችግር እንደሚቀለብሱት የሚገልጹም ነበሩ። ስለ ውስጥ ችግር ስጋት ማውራትና መስበክ የተፈለገበት ዋንኛ ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ ህወሃት በመግለጫው በገሃድ ከድርጅቱ እምነትና ሃሃሳብ ውጪ የሆኑትን በሙሉ የትግራይ ህዝብ ፈርጆ እንዲታገላቸው፣ እንዲያጠፋቸውና እንዲያገላቸው ጠይቋል። አያይዞም ባንዳ፣ እንክርዳድ፣ ከሃጂ፣ የፖለቲካ ነጋዴዎች፣ ያላቸውን ” ዋጋ ያስከፍላል” ሲልም አስጠንቅቋቸዋል።

በቴሊቪዥን ደግሞ ” ስይጣኖች” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። እንገዲህ እነዚህ የተፈረጁ አካላት በስም እነማን እንደሆኑ በይፋ ባይዘረዘርም፣ አቶ አብርሃ ደስታ ግን በይፋ ፍረጃውን በማታታል ይልቁኑም ለስለማና ለህዝብ የማይተቅም ” አደገና” ሲሉ ነው የገለጹት።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

ስም ሳይጠቅስ በፖለቲካ ስም ንግድ የሚነግዱ የትግራይን ህዝብ ደህነነት ወደ ገበያ ማስገባት ታሪካዊ ክህደት የሚፈጽሙ ሲል ህወሃት ሲኮንን ማንን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ እንደሚታወቅ ነው አቶ አብረሃ ደስታ ያስታወቁት። ህወሃት በመግለጫው ” ከሃጂ፣ እንክርዳዶች በሚል ማስፈራሪያ አዘል ለተሰራጨው መግለጫ አቶ አብርሃ ደስታ ” በዚህ ጊዜ የማይታሰብ፣ ሕዝብን አስፈራርቶና ረግጦ ለመግዛት የሚደረግ፣ ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ ነው ብዙ ማብራሪያ ሳይሰጡ ያጣጣሉት።

አካሄዱ ለትግራይ፣ ለትግራይ ሕዝብ፣ ለአገርም እንደማይጠቅም የገለጹጥ፡የአረና ሊቀመንበር፣ ህወሃት አፈናውን እንደሚቀጥል ማረጋገጫ መስጠቱን ነው ያርጋገጡት። “የትግራይን ህዝብ በማስፈራራት አፍኖ ለመግዛት ታስቦ የተዘጋጀውን የህወሃት መግለጫ በአገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተወያየንበት ያለውን አጀንዳ ገደል የሚከት” ሲሉ ነው ያወገዙት።

አቶ አብርሃ ለጀርመን ድምጽ እንደገለጹት አባሎቻቸው “ጽዳት ለምን አጸዳቹህ” በሚል የክልሉ የጸጥታ ሃይል ክፉኛ ድብደባ ማካሄዱ፣ ማሰሩና የታሰሩበት ቦታ አለመታወቁ አገሪቱ አሁን ባለችበት ወቅታዊ የለውጥ ሂደት ላይ የማይታሰብና የማይገመት መሆኑንን አመልክተዋል።

ህወሃት በመግለጫው “…. የተሰማሩ እንክርዳዶች በትግራይ ህዝብ ዋጋ የግል ፍላጎታቸው ለማርካት ሲሉ የህዝባችን አንድነትና ፅናት ሊበርዙ ጥረት እያደረጉ ነው። ከደቡብ ይሁን ከሰሜን የተላኩ ባንዳዎች ይህን እኩይ ተግባራቸው ለመፈፀም ተደልለው እየተንቀሳቀሱ ነው

በቅርብ ጊዜ የህዝቡን ልማት ፣ ጥያቄና ትግል ሌላ ትርጉም በማስያዝ ለዘመናት የዘለቀውና በአሁኑ ወቅት ተጠናክሮ የቀጠለውን አንድነት እድል አገኘን ብለው ለማደፍረስ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡የትግራይን ህዝብና ደርጅቱ ህወሓትን ፊት ለፊት ገጥመው ማንበርከክ ያልቻሉ ሃይሎች ሌላ አዋጭ ይሆናል ያሉትን ይዘው ክፍተት ለመፍጠር እየትንቀሳቀሱ ነው፡፡በትግራይ ውስጥም ተላላኪ ለማግኘት የሚደረግ ጥረት የለም ባይባልም በአጭር ጊዜ ይህንን ይዞ በትግራይ ህዝብ ላይ ዝለል ሲባል የሚዘል ሃይል ለማግኘት ይቻላል የሚል ግምት በትግራይ ህዝብ ቀርቶ የሚያሰማሩ ሃይሎችም የሚገምቱት አልነበረም፡፡ የተለየ ሃሳብ ይዘህ ወደ ህዝብ መቅረብና መታገል አስፈላጊና መሆን የሚገበው ቢሆንም የትግራይን ህዝብ ደህነነት ወደ ገበያ ማስገባት ግን ታሪካዊ ክህደት ነው፡፡ በስመ ፖለቲካ ወደ ንግድ የተሰማሩ እንክርዳዶች በትግራይ ህዝብ ዋጋ የግል ፍላጎታቸው ለማርካት ሲሉ የህዝባችን አንድነትና ፅናት ሊበርዙ ጥረት እያደረጉ ነው። ከደቡብ ይሁን ከሰሜን የተላኩ ባንዳዎች ይህን እኩይ ተግባራቸው ለመፈፀም ተደልለው እየተንቀሳቀሱ ነው።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

ህዝባችን ይህ አፍራሽ ተግባር፣ እንደተለመደው አንድነትህን በማጠናከርና ለደህንነትህንና ለህልውናህ ቅድምያ ሰጥተህ በፅናትና በቆራጥነት ልትታገላቸው ይገባል። የነዚህ ሓይሎች ተግባርና ፍላጎት ሌላ መልክና ሽፋን ይዞው ሲመጡም፣ እንደየመልካቸው በጥናት ልትታገላቸው ይገባል። ለማይቀረው ድል አንድነትህ አጠናክር፣ በድርጅትህና መስመርህ ጎን ተሰልፈህ ለሁሉም ጉዳዮች በንቃትና በተጠንቀቅ እንደሚትከታተለው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አይጠራጠርም። በእኩይ ተግባር የተሰማራችሁ ወገኖች ደግማችሁ ደጋግማችሁ እንድታስቡ፣ ከሁሉም በፊት ለህዝባችን ደህንነት ቅድሚያ ሊትሰጡ ይገባል። ጨለማ ተገን በማድረግ እናደርገዋለን ብሎ ማሰብ ግን ከንቱ ነው። የሚጠይቀው ወጋም ከባድ ነው። የሚሰማና የሚያይ መንግስትና ህዝብ ያለው ክልል ነው። ስለዚህ ከእኩይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በድጋሜ ምክሩን ይለግሳል” ይላል መግለጫው

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

ጽዳት ያጸዱ ተወገሩ፣ ታሰሩ – ጀርመን ሬዲዮ

እሁድ ሚያዝያ  6፤ በመቐለ ኩሓ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ ወጣቶችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በፖሊስ መደብደባቸውና መታሰራቸው ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ገለፀ፡፡ እርምጃው የሕግ የበላይነት የጣሰ ብሎታል፡፡ በጉዳዩ ላይ የዓረናው ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ብቸኛው በትግራይ ክልል በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነትና ዲሞክራሲ በትላንትናው ዕለት እሁድ በመቐለ ኩሓ ወጣቶች በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ በነበሩበት ወቅት የመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ጥቃት እንደፈፀሙባቸው ገልፅዋል፡፡ በጥቃቱም የፓርቲው አባል፣ አክቲቪስቶችና ሌሎች ወጣቶች ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል፣ ታስረዋል ብሏል፡፡  በፓርቲ የደረሰው ጥቃት ለማጣራት ቢንቀሳቀስም በፀጥታ ሐይሎች ክልከላ እንደደረሰባቸው ሊቀ መንበሩ አቶ አብረሃ ደስታ ዛሬ በፅሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ዓረና እንዳለው ትላንት በፓሊስ ድብደባ ከተፈፀመባቸው የመቐለ ኩሓ ክፍለከተማ ነዋሪዎች መካከል የዓረና ማእከላይ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ቁጥጥር ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ፅጋቡ ቆባዕ እንደሚገኙበት ተነግሯል፡፡ ይህ ተግባር ሕጋዊነት የጎደለውና በዚህ ወቅት የማይጠበቅ ነው ያለው ፓርቲው ድርጊቱ የሚወገዝ መሆኑ አቶ አብረሃ ደስታ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከመንግስት ወገን መረጃ ለማግኘት የመቐለ ኩሓ ክፍለ ከተማ ፖሊስና የፀጥታ ፅሕፈት ቤት ሐላፊዎች ለማግነት ሞክረን አልተሳካም፡፡ የመቐለ ከተማ ፀጥታና አስተዳደር ፅሕፈት ቤት ሐላፊ በበኩላቸው በጉዳዩ ዙርያ የደረሳቸው አንዳች መረጃ እንደሌለ ነግረውናል፡፡

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0