“Our true nationality is mankind.”H.G.

የተፈረካከሰው ኦነግ እየተሰፋ ነው፤ ለማ መገርሳ ለጠቅላይ ይጫወታሉ፤ የሸኔ – ኦነግ ዳውድ ኢብሳ የሉበትም!!

ለአራትና ከዛም በላይ ተሰነጣጥሮ፣ ነገር ግን ኦነግ የሚለውን የትግል ዓርማ ባለመጣል እዚህ የደረሱት ድርጅቶች ቁመናቸውን እያስተካከሉ ነው። የሰሞኑ ዜና ይፋ ከመሆኑ በፊት በኦሮሚያ የሚታየው የሃይል አሰላለፍና ትግል “እስከ ሰኔ መስመሩ ይለያል” በሚል ባለፈው ሳምንት መዘገባችን አይዘነጋም።

ይህንኑ ተከትሎ ዛሬ ይፋ እንደህነው በገላሳ ዲልቦና በአባ ነገ ውህደት መፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ተፈራርመዋል። ቀደም ሲል አብረው የነበሩት አመራሮች ተለያይተው ቢቆዩም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥሪ አገር ቤት ከገቡ በሁዋላ ለመስማማት ችለዋል።

ለአራት ከተከፈለው ኦነግ የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በመወከል /ኦነግ ዩኒት/ አቶ ገላሳ ዲልቦ እና  የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባርን / ኦነግ ትራንዚሽን/ በመወከል ደግሞ አባነጋ ጃራ ወደ ውህደት በሚያመራቸውን ሰነድ ላይ የስምምነት ፊርም አኑረዋል። ከስነስርዓቱ በሁዋላ ለህዝቡ ሰላም እና አንድነት በጋራ ሲባል ዳግም መዋሃደችውን አመልክተዋል።

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የሚመራው ኦዴፓ  በአባ ነጋ ከሚመራው የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባርን / ኦነግ ትራንዚሽን/ ጋር ወደ ውህደት የሚወስደውን ስምምነት ከስምንት ወር በፊት መፈራረሙ አይዘነጋም። ይህንን የሚያስታውሱና ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አካላት፣ የገላሳ ዲልቦና የአባ ነጋ ስምምነት ሲጠናቀቅ፣ ኦዴፓ ውህደት ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው።

ወደ አገር ቤት ከመግባታቸው በፊት ተበጣጥሰው የነበሩት የኦነግ አመራሮች ወደ አንድ ለመምጣት አስፈላጊውን ድርድርና ስምምነት ከጨረሱ በሁዋላ የፊርማ ማጽደቁ ስራ እንዳይሰራና ተግባራዊ እንዳይሆን አቶ ዳውድ ኢብሳ መሰናክል መሆናቸው አይዘነጋም።

ውጤት ሊያመጣ ከማይችለው የኤርትራ ምሽጋቸው ወደ አዲስ አበባ የገቡት ዳውድ ኢብሳ ለዚህ ጥምረትና ውይይት አልተጋበዙም። ገላሳ ዲልቦ ላይ አሲረው ኦነግ ሸኔን የመሰረቱት ዳውድ ኢብሳ በዚህ አዲሱ ስምምነት አለመጋበዛቸው ብቻ ሳይሆን ከውስጥም ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያካሂዱ ግፊት በዝቶባቸዋል።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

በምርጫ ቦርድ ለመዝገብም ሆነ የድርጅቱን ህጋዊነት ለማጽናት ጠቅላላ ጉቤኤ ማካሄድ ግድ በመሆኑ አቶ ዳውድ ኢብሳ ወደ ጡረታ ሊያመሩ እንደሚችሉ ከግምት በላይ እየተነገረ ነው።

ዳውድ ኢብሳ ጡረታ!! ቄሮ “በቃ” እያለ ነው! ኤርትራ መሽገው የነበሩትና በቅርቡ ወደ አገር ቤት የገቡት የኦነግ አንድ ክንፍ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከድርጅት መሪነታቸው እንዲለቁ ቄሮ ንቅናቄ መጀመሩ ተሰማ። የዛጎል መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ዳውድ ኢብሳ ዙሪያቸው ባልጠሩ የተለያዩ ጉዳዮች የተተበተበ መሆኑም እንዳሰቡት ድርጅቱን እየመሩ ለመቆየት ይቸገራሉ።

በባህላዊው የኦሮሞ ገዳ ደንብ መሰረት አቶ ዳውድ ስምንቱን ዓመት ካጠናቀቁ ቆይቷል። በእድሜያቸውም ቢሆን ሰፊ ህዝብ የሚወክል አንድ ተፎካካሪ ድርጅትን በብቃት ለመምራት በሚያስችለው ደረጃ ላይ አይደሉም። በሚደግፏቸው የወለጋና አካባቢው ቄሮዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄ የሚነሳባቸው አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሁለቱ ማለትም አባ ነገኣ /ጀነራል ሃይሉ ጎንፋና በዙም ድምጻቸው ከማይሰማው ገላሳ ዲልቦ ኦነግ ጋር ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ትክክለኛው የኦነግ ባለቤት ለመሆንም እንደሚቸገሩ ነው።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

እሳቸው የሚመሩት ኦነግ የስራ አስፈጻሚ አመራሮች ከአንድ የትውልድ ቀዬና አካባቢ መሆኑም ሌላ ችግር መሆኑንን የሚያነሱት የዜናው ምንጮች፣ አቶ ዳውድ በሀረርጌ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በምስራቅ ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ ተቀባይነታቸው መመናመኑን ይናጋራሉ። “ተቀባይነት ከሌላቸው በአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ እንዴት ቁጥሩ ከፈተኛ የሆነ ህዝብ ተገኘ ” በሚል ለቀረበላቸው  ጥያቄ ሲመልሱ ” እሱ አዲስ አበባ ላይ ካለው ፖለቲካ የሚነሳ እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ጉዳዩን ትልቅ ያደረገው አቶ ለማ መገርሳና ወርቅነህ ገበየሁ አስመራ ሄደው መደርደራቸው ነው። በሚል በውቅቱ መዘገባቸን ይታወሳል።

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0