የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሚኒስትሮችን ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፦

አቶ ገዱ አንድአርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አቶ ለማ መገርሳ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር

ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቅራቢነት የቀረበለትን የሚኒስትሮች ሹመትን ነው ተቀብሎ ያፀደቀው።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በእጩዎቹ ሹመት ዙሪያም የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፥ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ጫላ ለሚ ምላሽና ማብራሪ ሰጥተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት፥ ሚኒስትሮች ሲቀየሩ ምክንያቱ አብሮ ቢገለፅ፣ አቶ ለማ መገርሳ እና አቶ ገዱ አንድአርጋቸው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ነበሩ፤ ከክልል ለምን ተነስተው ወደዚህ መጡ የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

አቶ ጫላ ለሚ በሰጡት ምላሽ፥ በሚኒስትሮች ሹመቱ ላይ ከዚህ ቀደም ከነበረው የተቀነሰ እንደሌለ በመግለፅ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ለሌላ ስራ በመልቀቃቸው በምትካቸት መሾሙን አስታውቀዋል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

የመከላከያ ሚኒስትር ስራ የነበሩት ኢንጂነር አይሻም በሙያቸው እንዲመደቡ ተደርጎ በምትካቸው አቶ ለማ መመደባቸውንም ገልፀዋል።

ሁለቱ እጩዎች ከክልል ርዕሰ መስተዳድርነት የተነሱትም በክልል ላይ ችግር ስላለባቸው ሳይሆን፥ በአሁን ወቅት ሀገሪቱ ያለችበት ለውጥ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዙ በመሆናቸውና የፌዴራል መንግስቱን የበለጠ ለማጠናከር ታስቦ እንደሆነ አንስተዋል።

ምክር ቤቱ በቀረበለት የሚኒስትሮች ሹመት ላይ ከተወያየ በኋላ በአንድ ተቃውሞ፣ በአምስት ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *