አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር በመሆን ተሾሙ። ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት ባካሄደው አራተኛ አስቸኳይ ስብሰባው ነው አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አድርጎ የሾመው። በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት የተሾሙት አቶ ሽመልስ የርእሰ መስተዳድርነት ስራውን የሚሰሩ መሆኑም ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ በዛሬው እለት የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር በመሆን መሾማቸውን ተከትሎ ነው ጨፌው አቶ ሽመልስን በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት የሾመው።

Related stories   Speaking Truth to Power, Samantha: Stop Defending Ethiopia’s “Proud Boys”!

አቶ ሽመልስ ዛሬ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነው እስከሚሾሙ ድረስ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በጉባዔው ላይ ባስተላለፉት መልእክት፥ “የህዝባችን ትግል እውን እስኪሆንና ፍላጎታቸው ከግቡ እስኪደርስ ድረስ ህዝቡ የወከለኝ በመሆኑ በህብረት እና በአንድነት የተጣለብንን የታሪክ አደራ እንወጣለን” ብለዋል።

Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

‘እኔም የሚጠበቅብኝን ጠንክሬ እሰራለሁ’ ሲሉም አቶ ለማ በጉባዔው ላይ ተናግረዋል።

አቶ አዲሱ አረጋ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተደርገው ተሹመዋል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ኦዲፒ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አቶ አዲሱ አረጋ የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል። አቶ አዲሱ አረጋ የኦዲፒ ፅህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩትን ዶክተር አለሙ ስሜን በመተካት ነው የተሾሙት። አቶ አዲሱ አረጋ ከዚህ ቀደም የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነበሩ።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *