የኦዲፒ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ አምቦ ላይ አቶ ተስፋዬ ገ/አብ የጻፈውን “የቡርቃ ዝምታ” አስመልክቶ “ገንዘብ ተከፍሎት ኦሮሞና አማራን ለማጣላት የጻፈው መጽሐፍ ነው” ካሉ በሁዋላ በኦሮምኛ ቋንቋ በፌስ ገጻቸው ላይ ይቅርታ ጠየቁ በሚል ወሬ መሰራጨቱ ተሰራጭቷል። አቶ አዲሱ ግን ይቅርታ አለመጠየቃቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። ወደ አዲስ አበባም እንደማይመጣና ባለበት በህግ የመጠየቁ ጉዳይ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተመለከተ

ዳኔል ብርሃኔ ” አዲሱ አረጋ ስለቡርቃ ዝምታና ተስፋዬ ገብረአብ በአማርኛ ለተናገረው በኦሮምኛ ይቅርታ ጠየቀ? እንዴት አይነት ዘመን ውስጥ ገባን? ይቅርታው አስቀድሞ በእቅድ የተያዘ የፕሮፓጋንዳው አካል አለመሆኑንስ እንዴት እንመን? ” ሲል በአቶ አዲሱ ላይ ትችትና ስላቅ ለማሰማት ቅድሚያ ይዞ ነበር።

Image may contain: 1 person

ይህ ብቻ አይደለም ተስፋዬ በሚባለው የቡርቃ ዝምታ መጽሃፍ የፈጠራ ታሪክ ተራች፣ በተጭበረበረ የፌስ ቡክ ገጽ በስሙ አዲሱ አረጋ ለተናገሩት የተለመደ ማደናገሪያ ምላሽ መስጠቱም ተመልክቷል። ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ  ” ትናንት አቶ ተስፋዬ በገጹ ላይ ስላሰፈረው ጽሑፍ ያጋራኋችሁ ሃሳብ የነበረ ሲሆን ብዙ ወዳጆቼ ገጹ የእሱ አይደለም ብላችሁ መልዕክቶቻችሁን አድርሳችሁኛል። ከልቤ እያመሰገንኩ ይህ እውነት ከሆነ ራሱ አቶ ተስፋዬ በስሙና በፎቶው የሚሰራጭን መረጃ ለፌስ ቡክ አመልክቶ በሰከንዶች ውስጥ ማስቆም እየቻለ ለምን ዝምታ መረጠ?… ” ሲል ጠይቋል።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

በሌላ በኩል ተስፋዬ የሚጠቀምባቸውን ስልቶችና የብዕር ይዘቱን የሚያውቁ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት እያኮበኮበ ባለበት ወቅት ከአቶ አዲሱ አረጋ የተወረወረውና  በምሁራን ውይይት ላይ ገለባ የተደረገው ተስፋዬ ራሱ ጽሁፉን እንዳዘጋጀው የተለያዩ የማህበራዊ ገጽ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ነው።

አማራና ኦሮሞን ለማጫረስ የቤት ስራ ወስዶ በከፍተኛ በጀት የተመረተው የቡርቃ ዝምታ ተረት ላደረሰው እልቂት ተስፋዬ እንዲጠየቅ አገር ወዳዶች በሚተጉበት ወቅት ከመንግስት ወገን ይህ ሃሳብ መነሳቱ ለተስፋዬ ስጋት እንደህሚሆንበት እሙን ነው።

በየጊዜው ለአማራ ህዝብ መልካም ሃሳብ አለኝ የሚለውና በውል የሚጨበጥ ዓላማ የሌለው ጃዋር መሃመድ ተስፋዬ ለምን ተነካ በሚል አቶ አዲሱን መጎንተሉ ደግሞ የጃዋርን ጨለማ የገፈፈ ሆኗል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

” አሁን ሃላፊነት የሚሰማኝ ሰው ሆኛለሁ፣ እንደ ቀድሞው አይነት ጃዋር አይደለሁም ” በሚል የሜንጫ ታሪኩን ለማደስ የሚወተውተው ጃዋር እልቂትንና ፍጅትን የሚጋብዘውን የተስፋዬ መጽሃፍ ለምን ተተቸ ብሎ መንፈራገጡ ተመልሶ እንደሚጎዳው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየተናገሩ ነው። ሲያብራሩም ጃዋር እየሰራ ያለው ሁሉ እየተሰበሰበና እየተከማቸ እንደሆነና በከፍተኛ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀር ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ  አልገባዉም። በቅርቡም የኦሮሚያ ፖለቲካ እንደሚሰክን አልታየውም። የሸዋ ኦሮሮሞ በቃህ ሲለው መግቢያ እንደሌለውም አልተረዳም። ብለዋል።

ከጃዋር ቁጣ በሁዋላ ይቅርታ ጠየቁ የተባሉት አቶ አዲሱ የሚከተለውን ነው የጻፉት –

“የእኛ አቅም የእናንተ ትችትና ምክር ነው። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ክፍተቶች ስንፈጥርና ስህተቶች ስንሠራ እነዚህን ትችቶችና ምክሮች ማቅረባችሁ ስለምትወዱን ነው ብለን እንገነዘባለን። በሥራ አጋጣሚ ከምንፈጽመው ድርጊትና ሊያስቀይማችሁ ከሚችል ንግግር ራሳችንን በማረም እና ጉድለቶቻችንን በመሙላት ምንጊዜም ማገልገላችንን እንቀጥላለን።” 

በዚህ የአቶ አዲሱ ንግግር ውስጥ ይቅርታ አይታይም። የኦሮሞንና የአማራ ህዝብ ህብረት ያሳሰባቸው ወገኖች ይህ በሃሰት ላይ ተመስርቶ፣ በርዕዮተ ዓለም ደረጃ ተገንብቶ፣ በበጀት ታግዞ ሲራገብ የነበረው አማራን የማጠልሸትና ከኦሮሞ ወገኖቹ ጋር ያለውን ሰላማዊ ግንኙነት የመበጠስ ሴራ መክሸፍ ያሳሰባቸው ገና ብዙ እንደሚሉና በተግባርም እንደሚፈጽሙ የሚጠበቅ መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች አመልክተዋል።

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ ላይ አልወርድ ያለው ተስፋዬ ገብረአብ በቅርቡ ለፍርድ እንደሚቀርብ ጉዳዩን የያዙት ከወራት በፊት መናገራቸው ይታወሳል። ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ስለመጋበዙ በመንግስት በኩል የሚታወቅ ጉዳኡ አለመኖሩን፣ እነ ጃዋር የሚጋብዙትም ከሆነ መንግስት ማናቸውንም አይነት ሃላፊነት እንደማይወስድ ዛጎል ያናገራቸው አንድ የኦዴፓ ሃላፊ ገልጸዋል። በተመሳሳይ ተስፋዬ አዲስ አበባን ሊረግጥ እንደማይችል በርካታ ምክንያት በመዘረዘር የሚናገሩም አሉ። እሱም አያደርገውም።

 

 

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *