ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋው 219 ሚልዮን 368 ሺህ 600 ብር የሆነ የኮንትሮባንድ ዕቃ በዲፕሎማቲክ የቀረጥ ነፃ መብት ሽፋን ወደ ሀገር ሲገባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በጀርመን ተራድኦ ድርጅት (GIZ) ስም በሀሰተኛ ሰነድ 4ሺህ 100 ኪ.ግ የሚመዝኑ 287 ዓይነት ዕቃዎች ሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ 118 ሚሊዮን 440 ሺህ ብር የሚገመተው ‹ካኖን› ካሜራዎች ናቸው፤ 52 ሚሊዮን 362 ሺህ 200 ብር የሚገመተው ደግሞ የስማርት ስልክ ስክሪን ነው፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ የተለያዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች፣ መድኃኒት፣ ፕሮጀክተር፣ የብር ጌጣጌጥ እና ልዩ ልዩ ኬብሎች ናቸው፡፡

Related stories   “ፍትህ ለትግራይ! ሞት ለመከላከያ ሰራዊትና … በትግራይ ሕዝብ ስም ትህነግ የመዘዙ ምንጭ ላይሆን?

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያረጋገጠው 410 ኪ.ግ ነው፤ ቀሪው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስም በተሠራ ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም የተፈጸመ የኮንትሮባንድ ወንጀል ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሦስት የጀርመን ተራድኦ ድርጅት ሠራተኞች እና ሁለት የዘራይደር የጉምሩክ አስተላላፊ ድርጅት ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ውለው በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

Related stories   በትግራይ 3.5 ሚሊዮን ተረጂዎች የዕለት ቀለብና ተመሳሳይ እርዳታ እየተደረገላቸው ነው

ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *