” .. የምናወራው ጉዳይ የጤንነቱ ጉዳይ ነው። ጤናው በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። የልብ በሽተኛ ነው። የመተንፈሻ መሣሪያ ካልተገጠመለት ተኝቶ ማደር አይችልም። ሌላኛው ጉዳይ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ነው። ስለልጆቻችን እንመካከራለን ማለት ነው…”

! … አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበለጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ…”

BBC Amharic

በትግል ስማቸው ‘ጥንቅሹ’ ተብለው የሚታወቁት እና የጥረት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳ ከአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ የታገዱት ከወራት በፊት ነበር። ይህ ተሰምቶ ብዙም ሳይቆይ አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት ስምዖን መታሠራቸው ተዘገበ። አሁን አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት ከባህርዳር ከተማ ወጣ ብሎ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ።

ጥር 15፣ 2011 ዓ. ም. የተፈጠረውን የሚያስታውሱት የአቶ ታደሰ ካሳ ባለቤት ወ/ሮ ነፃነት አበራ፤ «የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውም ሆነ አቶ ደመቀ እነ ታደሰ እንዲታሰሩ ፍላጎት አልነበራቸውም» ይላሉ። ሙሉ ቃለ ምልልሱ እነሆ።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ያስውሱታል?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ንጋት 1፡45 ገደማ ነበር። ፖሊሶች መጥሪያ ይዘው መጡ። በወቅቱ የት ነው የምሄደው? ብሎ ጠይቋቸው ነበረ። ያው ታደሰ በሥራ ብዛት ምክን አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበለጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ።ያት የተለያዩ በሽታዎች አሉበት። የልብ ሕመም አለበት። ለማንኛውም ለዝግጅት እንዲሆን የት ነው የምሄደው? አማራ ክልል ነው ወይስ ፌዴራል ነው? የሚል ጥያቄ አቅርቦ ነበር። እዚሁ ፌዴራል ነው ጉዳያችሁ የሚታየው ነው ያሉን። ልብስ መያዝም አልፈቀዱለትም። ምናልባት ለዛሬ የሚሆን መድኃኒት መያዝ ትችላለህ ነው ያሉት። ስናረጋግጥ ግን ቻርተር አውሮፕላን አዘጋጅተው ነበር። በቀጥታ ወደቦሌ ነው የወሰዱት።

ቢቢሲ፦ ባህርዳር ከገቡ በኋላ የነበረውን ሁኔታ አቶ ታደሰ ነግሮዎታል?

ወ/ሮ ነፃነት፦ በግዜው እኔ አልሄድኩም። የአቶ በረከት ባለቤት እና ልጄ ነበር የሄዱት። ወደ ባህርዳር ዘጠነኛ ፖሊስ ጣብያ ነበር የሄዱት። እዚያ ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጥስ ሁኔታ ነው የተፈፀመባቸው። መያዛቸውን ያወቁ ሰዎች በስድብ እና ዛቻ ነው የተቀበሏቸው። ሌቦች፣ ፀረ-አማራዎች እና የመሳሰሉ ስድቦች ሲሰደቡ ነበረ። ፖሊስ ወጣቶቹ ገለል እንዲሉ ጥረት አድርጓል፤ ግን ብዙ ሊርቁ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊቀርቡ አልቻሉም። በእኔ እምነት ዘጠነኛ ፖሊስ የነበረውን ወከባ ለመቀነስ የፖሊስ ኃይል በመጨመር መካላከል ይቻል ነበር። ከእነሱ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር አለ የሚል እምነት የለኝም። እንዲሰደቡም ጭምር የአሣሪው አካል ፍላጎት አለ የሚል እምነት ነው ያለኝ።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ በሕግ ጥላ ሥር ከመዋላቸው በፊት ይህ ቀን ሊመጣ ይችላል ብለው አስበው ያውቃሉ? አውርታችሁ ታውቃላችሁ ስለዚህ ጉዳይ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ አባል ነበርኩ። የፓርቲው የሁለት ዓመት ተኩል አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ነበር ብዬ አልወስድም፤ በወቅቱ ስለነበርኩ ማለት ነው። በረከት እና ታደሰ ላይ ያተኮረ ስድብና ዛቻ ነው የነበረው። ጉባዔተኛው፤ «እነዚህ ፀረ-አማራ ናቸው፤ ታደሰ ትግሬ ነው፤ በረከት ደግሞ ኤርትራዊ ነው፤ ሰርገው የገቡ ናቸው፤ ጥረት ለብክነት የዳረጉ ናቸው፤ የሕወሓት ተለጣፊ ናቸው» እና የመሳሰሉ ነገሮች ሲነሱ ነበር። ማጠቃለያ ላይ የተነገረው ነገር ተገቢ አይደለም። የተናገረ፣ ሥነ ስርአት ያስያዘ ከፍተኛ አመራር ግን አልነበረም። ስለዚህ በጉባዔ ደረጃ የመጨረሻ መደምደሚያ የሆነው በሕግ እንጠይቃቸዋለን ነበር። ሁለቱም [አቶ ታደሰ እና አቶ በረከት] ይህንን ያውቁታል። ቢሆንም ታደሰ እታሠራለሁ የሚል እምነት አልነበረውም። ምክንያቱም በጥረት ጉዳይ የአሠራር ግድፈት ሊኖር ይችል ይሆናል፤ ይህ ደግሞ አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ሊታይ የሚችል እንጂ የሙስና ወንጀል ሆኖ እስከ አሥራት ሊያደርስ የሚችል አይደለም የሚል ፅኑ እምነት ነው የነበረው። እኔ ግን የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄ ነው፤ በሕዝቡ ዘንድ ስማችሁ ጠፍቷል እና ይህን ማስታገስ የሚችሉት እናንተን በማሠር ነው የሚል እምነት ነበረኝ። እሱ ግን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ አልነበረውም። ጥር 15፤ በግምት 1፡45 አካባቢ ሲይዙትም ሳይገርመው አልቀረም።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ተከፍቷል እያሉኝ ነው። ይህን የጥላቻ ዘመቻ ማነው የከፈተባቸው ብለው ያስባሉ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ በስም እከሌ ብዬ መጥራት አልፈልግም። መሆንም የለበትም። እንደ ኮሚቴ የተሠራ ሥራ ነው ብዬ አስባለሁ። ሁሉም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በታደሰም ሆነ በአቶ በረከት መታሠር ፈቃደኛ ነበሩ ብዬ አላስብም። እንደሰማሁት እንግዲህ፤ መረጃው ያው ምስጢር አይደለም፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ ላይ መታገድ አለባቸው እና የለባቸውም በሚል ክርክር ተደረገ። ውሳኔው ደሞ አቶ በረከትን ያካተተ አልነበረም። ታደሰ እና አቶ ምትኩ በየነ [የአምባሰል ንግድ ሥራዎች ኃላፊ] ላይ ነው የነበረው። በድምፅ ብልጫ ከማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲታገዱ ተወሰነ። እዚህ ውሳኔ ላይ አቶ ገዱ የነበራቸው አቋም፤ ከአሠራር ክፍተት አኳያ ሁላችንም እንፈተሽ ከተባልን፤ ጥረት ላይ ከተፈጠረው በአሥር እጥፍ የሚበለጥ ግድፈት ሊገኝብን ይችል ይሆናል። ልዩነቱ ጥረት ላይ ሰው አሰማርተን መረጃ የማጥራት ሥራ መሥራታችን ነው። በዚህ ደረጃ ብንሄድ የሚቀር ሰው የለም የሚል አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ። አቶ ደመቀም ተመሳሳይ አቋም እንደነበራቸው አውቃለሁ።

ቢቢሲ፦ በሕግ ጥላ ሥር እንዲውሉ በመወሰኑ ላይስ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ እንዲታሠሩ በመወሰኑ ላይ የእያንዳንዱ ሰው ሚና ምንድነው? የሚለውን በዝርዘር ባላውቅም፤ 25 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ተሰብስበው ነበር። በነገራችን ላይ 25 የብአዴን [አዴፓ] ሕጋዊ የማዕከላዊ ቁጥርም አይደለም፤ የአባላቱ ቁጥር 65 ነው። ከዚያ 13 ሰዎች ይታሠሩ፤ 12 ሰዎች ደግሞ አይታሠሩ የሚል ድምፅ ሰጡ። ስለዚህ በውሳኔ ነው የታሠሩት። ከከፍተኛ አመራሩ ማን ምን ብሎ ድምፅ እንደሰጠ ግን በውል አላውቅም።

ቢቢሲ፦ የኮሚቴው አባላት 65 ከሆኑ ለምን 25 ሰዎች ብቻ ተሰበስበው ይህን ውሳኔ ሊያስልፉ እንደቻሉ የምታውቁት ነገር አለ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ እኔ ይህን አላውቅም። ሕጋዊ ነው የሚልም እምነት የለኝም። የኮሚቴው አባላት ቁጥር 65 ነው። ምናልባት በአንዳንድ ምክንያቶች የተወሰኑ ሰዎች ቢቀሩ 60 ወይ 50 ሊሆን ይችላል እንጂ በዚህ ደረጃ ዝቅ ያለ የማዕከላዊ ኮሚቴ ቁጥር አላውቅም።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰን እየሄዱ የሚጠይቋቸው መች መች ነው? ሲያገኟቸውስ ምን ጉዳዮች አንስታችሁ ታወራላችሁ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ እኔ በየሁለት ሳምንቱ እሄዳለሁ። ልጄ ግን ሁሌም ችሎት ባለ ቁጥር ትሄዳለች። ስንገናኝ ብዙ ጊዜ የምናወራው ስለ ፍርድ ሂደቱ ነው። እንደሚታወቀው ጠበቃ የላቸውም። ማግኘት አልቻሉም። ሁለት ጠበቆች አግኝተን ነበር። ነገር ግን ማስፈራሪያ ከደረሳቸው በኋላ ጉዳዩን መከታተል እንደማይችሉ ነገሩን። በሕግ ነው የተያዙት፤ ስለዚህ ጉዳዩ በሕግ ማለቅ አለበት። አስፈፃሚው አካል፤ ሕግ አውጭውም ጭምር የአማራ ማስ ሚድያን ተጠቅመው ጠበቃ እንዳይቆም እየተደረገ ያለው ነገር ትክክል እንዳልሆነ በይፋ መግለጫ መስጠት አለባቸው ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ እዚህ አዲስ አበባ ላይ ያማከርናቸውን ጠበቆች ሐሳብ ነግረዋለሁ። ችሎት ላይ የተባለውን ነገር መነሻ በማድረግ እዚህ ካሉ ጠበቆች ጋር እንመክራለን። ሌላው የምናወራው ጉዳይ የጤንነቱ ጉዳይ ነው። ጤናው በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። የልብ በሽተኛ ነው። የመተንፈሻ መሣሪያ ካልተገጠመለት ተኝቶ ማደር አይችልም። ሌላኛው ጉዳይ ያው የቤተሰብ ጉዳይ ነው። ስለልጆቻችን እንመካከራለን ማለት ነው።

ቢቢሲ፦ የሚያስፈልጋቸውን ሕክምናና የምግብ አገልግሎት እያገኙ ነው?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ያው እሥር ቤት ውስጥ እንደማንኛውም ሰው የምግብ አቅርቦት ነው ያለው። ባለው ርቀት ምክንያት የሚያስፈልገውን ነገር ልናደርግ አልቻልንም። እዚያው ማረሚያ ቤት ውስጥ አንድ ካፌ አለ እዛ ነው የሚጠቀመው። የጤና ጉዳይ እዚያ ባለው ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል መፍትሄ ማግኘት የሚችል አይደለም። ነገር ግን አስፈላጊው መድኃኒት እንዲቀርብላቸው እናደርጋለን።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ ያለፈውን ነገር ዞር ብለው ሲያዩት ምን እንደሚሰማቸው ጠይቀዋቸው ያውቃሉ?

ወ/ሮ ነፃነት፦ በአንድ በኩል መታሠሩ ግፍ እንደሆነ ያየዋል። ታደሰ የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኖ ሲገባ 4 ድርጅቶችን ነው የተረከበው። በስምንት ዓመታት ውስጥ በሱ አመራር ሥር ድርጅቶቹ ከ4 ወደ 21 አድገዋል። ይሄ በግልፅ የሚታወቅ ነገር ነው። አማራ ውስጥ ስለ ኢንዱስትሪ ጉዳይ ሲነሳ ጥረት በታደሰ እየተመራ የሠራቸው ሥራዎች ናቸው የሚነሱት። ይሄን ለሠራ ጀግና፤ ይሄን ለሠራ የልማት አርበኛ ሽልማት ሲገባው በአሠራር ጉድለት፤ በተለይ ደግሞ የፖለቲካ ልዩነትን መነሻ በማድረግ እሥር ቤት መግባቱ፤ ይህን ደግሞ ያደረጉት አብረውት የታገሉ፤ የሚያምናቸው ሰዎች መሆናቸው በጣም ያሳዝነዋል። በአንድ በኩል ይሄ ነው። በሌላ በኩል ግን ጀግንነት ይሰማዋል። እኔ ታደሰ ካሳ በሕይወት ታሪኬ በሙስና የምታወቅ አይደለሁም። እንደውም አይበላ አያስበላ ነው የምባለው። ስለዚህ እውነተኛ ፍትህ ካለ የጠፋውን ስሜን አጠራለሁ። ነገ ከነገ ወዲያ የአማራ ሕዝብ እውነታውን ይረዳል ብሎ ያስባል።

ቢቢሲ፦ የሚቆጫቸው ነገርስ ይኖር ይሆን? ባደርገው ወይም ባላደርገው ኖሮ የሚሉት?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ብዙም የሚቆጨው ነገር የለም። የሚያስቆጭ ሥራ አልሠራም። የሚቆጨው ይሆናል ብዬ የማስበው ከሐምሌ ጀምሮ የተደረገ የስም ማጥፋት ዘመቻ አለ። ምናልባት ራሱን ግልፅ ለማድረግ የሚያስችል መድረክ አለማግኘቱ ነው። ብዙ ጊዜ የስም ማጥፋት ዘመዛ ሲደረግ በዝምታ አልፏል። በዝምታ ከማለፍ ማን ምን እንደሆነ መናገር ነበረብኝ ይላል። ይሄ ይቆጨዋል ብዬ አስባለሁ።

ቢቢሲ፦ ከሃገር የመውጣት ሃሳብስ አልነበራቸው ይሆን?

ወ/ሮ ነፃነት፦ ታደሰ ከሃገር የመውጣት ፍላጎት የለውም። ሃሳቡ ጡረታ ከወጣ በኋላ አዲስ አበባ ሳይሆን ቢሆን ሰቆጣ ወይ ደግሞ ወልዲያ እሄዳለሁ የሚል ነበር። እውነት ለመናገር ከሃገር መውጣት ቢፈልግ መውጣት የሚያስችሉ ብዙ አማራጮች ነበሩት። የሁለት ዓመት የአሜሪካ ቪዛ አለው። የእንግሊዝም አለው። ነገር ግን በተገኘው አጋጣሚ ሕዝቡን የማገልገል ሃሳብ ነበር የነበረው።

ቢቢሲ፦ አቶ ታደሰ የተመሠረተባቸው ክስ ውድቅ ሆኖ በቅርቡ እለቀቃለሁ ብለው ያስባሉ?

ወ/ሮ ነፃነት፦አ. . . አዎም አይደለም ነው የዚህ ምላሽ። እውነተኛ ፍትህ ኖሮ፤ ዳኞች እና አቃቤ ሕጎች የአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ከሌለባቸው፤ ወደ ክስ መከራከሪያ ሳንገባ በክስ መቃወሚያችን ብቻ ይሄ አያስከስስም ተብሎ፤ ውድቅ ተደርጎ ልንወጣ እንችላለን [አቶ ታደሰና አቶ በረከትም] የሚል ሃሳብ አለ። ምክንያቱም በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሁሉም ከአሠራር ግድፈት ጋር የተያያዘ ስለሆነና የአሠራር ግድፈት ደግሞ የሙስና አንቀፅን መጥቀስ ስለማይችል ዳኞች ያቀረብነውን መቃወሚያ አይተው ውድቅ ሊሉት ይችላሉ። ይህ ግን ፍትህ ካለ ነው። የአስፈፃሚው አካል ተፅዕኖ ከሌለበት ይህ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለው። ነገር ግን እየተደረገ እንዳለው ጠበቃ ሊቆምላቸው ካልቻለ፤ የስም ማጥፋት ዘመቻ በሚድያ ከተደረገባቸው፤ ይህ ደግሞ በዳኞች እና በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ከሆነ በነፃ መውጣት የሚቻልበት ሁኔታ የማይታሰብ ነው የሚል እምነት አለው።

ቢቢሲ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የአቶ በረከትን ቤተሰቦችን እንዳናገሩ ሰምተናል። በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ፤ ነገር ግን ፍትህ እንዳይጓደል እንደሚያሳስቡ ሰምተናል። የአቶ ታደሰን ቤተሰብስ አግኝተው ነበር?

ወ/ሮ ነፃነት፦ አዎ! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በጋራ ነው ያገኙን። የአቶ በረከት ባለቤትንም፤ እኔንም ጠርተው ነው ያናገሩን። ስላሉበት ሁኔታ፤ ስለደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ እሥሩ ፖለቲካዊ እንደሆነ፤ በተለይ ደግሞ ጠበቃ የማጣታቸው እና የጤንነታቸው ጉዳይ እንደሚያሳስበንና በፍትህ እንዲዳኙ እንደምንሻ ነግረናቸዋል። ከምንም በላይ ፍትህ ብቻ እንዲዳኛቸው እኔም አናግሬያቸዋለሁ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *