ለመረጃ ክፍት ናቸው። በየትኛውም ጊዜ መረጃ ለመስጠት ተባባሪ ናቸው። ከናዚ ጋር የሚመሳኧሉትን አቶ መለስ ዜናዊ ፊት ለፊት የገጠሙና ” ደርግ ሆንክ” በማለት ያወገዙ ናቸው። በዚህም የተነሳ የአገሪቱ ፕሪዚዳንት የሆነ ሰው ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ተከልከለዋል። ፍትህ ተዛብቶባቸዋል። ተንገላተዋል። የሚያውቋቸው የዋህ፣ ቀናና ተጋባቢ እንደሆኑ የሚናገሩላቸው ዶከተር ነጋሶ ጊዳዳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ ላጠፉት ጥፋት ሕዝብን ይቅርታ የጠየቁ ናቸው።

የአማራ ህዝብን ለይቶ ለማስመታትና ለማጠልሸት በተስፋዬ የተጻፈውን መጽሃፍ ” ፈጠራና በታሪክ ያልተመዘገበ” ሲሉ ሃቅን የመሰከሩ ሰው ነበሩ። ጥናታቸውን የሰሩት በኦሮሞ ታሪክ ላይ መሆኑንን አስታውቀው አንድም የተጻፈ ማጣቀሻም ሆነ ማስረጃ የማይቀርብበት መሆኑንን በመግለጽ ባማራና በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነትን ለመፍጠር የተመረተ የሃሰት ታሪክ መሆኑንን ያጋለጡ ናቸው።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

እኚህ በስልጣን ዘመናቸው ለፈጸሙት ስህተት በይፋ ይቅርታ የጠየቁት ዶከተር ነጋሶ ጊዳዳ ነብስ ይማር። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መንግስት የተሰማውን ሃዘን አስታውቆ የቅብር ስነስርዓት መርሃ ግብርን እንደሚያስታውቅ አመልክቷል።

የክልል መንግስታት፣ ሚኒስትሮችና የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣ ታዋቂ ሰዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማትና አገራት ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፐሬዚዳንት የሃዘን መገለጫ እያስተላለፉ ነው።

ጀርመን አገር በማረፋቸው የጀርመን ሬዲዮ የዘገበውን ከታች አስፍረናል።

ኢትዮጵያን ለሰባት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጠዋት በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በ76 ዓመታቸው አረፉ። ዶ/ር ነጋሶ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ በአንድ የጀርመን ሆስፒታል ውስጥ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነበር። በጀርመን ያሉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ያረፉት በፍራንክፈርት ከተማ ዛክሰን ሐውስ ሆስፒታል በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ አራት ሰዓት ገደማ ነው።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሐሙስ ዕለት ወደ ፍራንክፈርት ኡኒቨርስቴት ክሊኒክ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ የጤና ሁኔታቸው በመባባሱ ለድንገተኛ ህክምና ወደ ዛክሰን ሀውስ ሆስፒታል ዛሬ ጠዋት መወሰዳቸውን ተናግረዋል።  በቄለም ወለጋ ደምቢዶሎ በተባለ ቦታ ጳጉሜ 3 ቀን፤ 1935 ዓ.ም የተወለዱት ዶ/ር ነጋሶ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ከነበራቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ።

አምስት አስርት አመታት ገደማ በዘለቀ የፖለቲካ ሕይወታቸው ኢትዮጵያን በፕሬዝዳትነት ከመምራት ባሻገር የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እና የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከፍተኛ አመራር ሆነው አገልግለዋል። ዶ/ር ነጋሶ አሁን በተግባር ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽንንም በሊቀ-መንበርነት መርተዋል። በሽግግር መንግሥት ወቅትም የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ እና በኋላም የማስታወቂያ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ከጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ከተቃቃሩ በኋላ ሰኔ 15 ቀን፤ 1993 ዓ.ም. ከኦሕዴድ እና ኢሕአዴግ አባልነታቸው የተሰናበቱት ዶ/ር ነጋሶ በግንቦት 1997 ዓ.ም. በተደረገው የኢትዮጵያ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው ተወዳድረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫን አሸንፈዋል። ዶ/ር ነጋሶ ባለትዳር እና የልጆች አባት ነበሩ።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *