በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በህገወጥ መንገድ መሬት በመውረር ግንባታ ያከናወኑ የተገኙ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳረጋገጠው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፖሊስ አባላት መካከል ዋና ሳጅን ዘሪሁን ወልዴ፣ ረዳት ሳጅን አሸናፊ ካንኮ፣ ረዳት ሳጅን አግማስ አንዱዓለም እና ረዳት ሳጅን ሀብተማርያም ጓንጉል ዛሬ ይገኙበታል።

በቀጣይነትም በህገወጥ የመሬት ወረራ ላይ ተሳትፈው የተገኙ የመንግስት አካላት፣ ባለሃብቶች እና ግለሰቦች ላይ የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በበኩሉ በመዲናዋ የመሬት ወረራ በተካሄደባቸው አምስቱ ክፍል ከተሞች ውስጥ በህገወጥ መንገድ መሬት በመውረር ግንባታ ያካሄዱ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ እንደሚቀጠል ነው ያስታወቀው።
 
ህብረተሰቡም ህገወጥ የመሬት ወረራ የሚያደርጉ እና የሚያስተባብሩ አካላትን ለከተማ አስተዳደሩ በመጠቆም ህወጥነትን በጋራ እንዲከላከል ጠይቋል።
FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *