“Our true nationality is mankind.”H.G.

“እንዲህ ወረኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል” ሙሉቀን መለሰ

አጫጭር ዜናዎች

“እንዲህ ወረኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል” ሙሉቀን መለሰ

” እንዲህ ወረኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል ” ሲል ባለ ብዙ ዝና ሙሉቀን መለሰ ሃዘኑን ገለጸ። የሸገር ሬዲዮ ” ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ” ሲል ሙሉቀን መለሰ ህይወቱ ማለፉን በይፋ ድረገጹ አትሞ ነበር። ዜናውን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በተለያዩ መገናኛዎች እንደ ሰደድ እሳት የተራባውን የሙሉቀን መለሰ ህልፈት ከሰዓታት በሁዋላ ሽገር ሬዲዮ ማስተካከያ አቅርቧል። ሙሉቀንም በዚሁ ማስተካከያ ስርጭት ላይ ነው ማዘኑን የገለጸው።

ወሬው የፈጠራ መሆኑንን ያመለከተው ሙሉ ቀን ” በፈጠራ ወሬ እዚህ አገር ዶላር ይከፈላቸዋል” ብሏል። ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታ በመልካም ሁኔታ እንደሚገኝም አስታውቋል። ሸገር የሚያምናቸው ምንጮቹ ከአሜሪካ የተሳሳተ መረጃ አቀብለውት የህልፈት ዜና መስራቱን በመጠቆም ሙሉቀንን በቀጥታ በስልክ ሲያነጋግር እንደተደመጠው፣ በንግግሩ የጸና ህመመተኛነት ምልክት እንኳን አይስተዋልም።

ሙሉቀን መናገር እየፈለገ በምስጋና በተቋጨውና ዓላማው የእሱን በህይወት መኖር ለመግለጽ በተሰራጨው አጭር ቃለ ምልልስ ” … እንዲህ ወሬኛ ሆነን መቅረታችን ያሳዝናል” ሲል የገለጸው በሃዘን ስለመሆኑ ግን ንግግሩ ያሳብቃል።

ዜናውን ፈጥረው ያራቡ ወገኖች ከዚህ መሰሉ ክፉ ተግባር ምን እንደሚጠቀሙ ግልጽ ባይሆንም ” እዚህ ሃገር ዶላር ይከፈላቸዋል” ሲል ሙሉቀን ያስተላለፈው መልዕት የሚሰመርበት ነው። በኢትዮጵያ አሁን የተያዘው የተገኘውን ሁሉ ዓየር ላይ ማዋልና ሳንቲም መልቀም መሆኑ ብዙዎችን እያሳሰበ ነው።

በመቶ የሚቆጠሩ የጉምዝ ተወላጆች ህይወት አለፈ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ  የእንባ ጠባቂን ለኦ ኤም ኤን እንዳሉት በስም ያልገለጿቸው ታጣቂዎች  በመቶ የሚቆጠሩ ጉምዞችን ገለዋል። ግድያው ህጻናትና ሴቶች ላይ ያነጣጠረ መሆኑም ታውቋል። አሁን ስፍራው ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ቁትትር ስር ሲሆን አካባቢው ተረጋግቷል። ቀደም ሲል በተካሄደው ግድያ የተጠረጠሩ ፫፫ ሰዎች መያዛቸውን የክልሉ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። አንድ የፖሊስ አባልም ይገኝበታል። አሁን ተፈጸመ ስለተባለው ግድያ በይፋ መንግስት ለጊዜው ያለው ነገር የለም።

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) የሚሰጠዉን የፌሊክስ ሁፌ ቡዌኝን የሰላም ሽልማት ዛሬ ተሸለሙ።የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅሕፈት ቤት እንዳስታወቀዉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለዓለም አቀፉ ሽልማት የተመረጡት ሠላም ለማዉረድ በመጣራቸዉ ነዉ።በቀድሞዉ የኮት ዲቯር ፕሬዝደንት ስም የተሰየመዉ ሽልማት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1991 ጀምሮ የደቡብ አፍሪቃዉን ኔልሰን ማንዴላን፣የፍልስጤሙን ያሲር አረፋትን፤የእስራኤሉን ሼሞን ፔሬስን ጨምሮ ከ20 ለሚበልጡ የዓለም እዉቅ ፖለቲከኞችና በጎ አድራጊዎች ተስጥቷል።ሽልማቱ ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በዉይይትና ድርድር በመፍታት ሰላም ለማዉረድ ለጣሩ መሪዎች፤ ፖለቲከኞችና የማሕበረሰብ ተጠሪዎች የሚሰጥ ነዉ።ሽልማቱ 150 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር፣ የወርቅ ሜዳይና የሰላም ዲፕሎማን የሚያሰጥ ነዉ። DW

የዘንድሮዉን የፕሬስ ነፃነት ቀንን ለማሰብ አዲስ አበባ ዉስጥ የተጀመረዉ ስብሰባና ዉይይት የሐሰት መረጃና ዜና ሥርጭትን መግታት በሚቻልበት ሥልት ላይ እንደሚያተኩር ተሰብሳቢዎች አስታወቁ።ነገ የሚከበረዉን የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀን ምክንያት በማድረግ በመላዉ ዓለም ከአንድ መቶ በላይ ስብሰባዎች፣ዉይይቶችና የመረጃ ልዉዉጦች ይደረጋሉ።ዛሬ አዲስ አበባዉ ዉስጥ የተጀመረዉ ዉይይት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚደረጉ ትላልቅ ዝግጅቶች አንዱ ነዉ። በዉይይቱ የሚካፈሉ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎች እንደሚሉት ሐሰተኛ ዜና እና የተዛባ መረጃ እየተበራከተ መምጣት ለነፃ ፕረስና ለዴሞክራሲ ትልቅ ስጋት እየሆነ ነዉ።በስብሰባዉ የሚካፈሉት የሶማሊያዉ የምርጫ ኮሚሽን ባልደረባ ሑሴይን አብዲ እንደሚሉት የሐሰት መረጃዎች የሐገራቸዉን የምርጫ ሥርዓት እስከማናጋት ደርሷል።ተሰብሳቢዎች የሐሰት መረጃና የዉሸት ዜና ሥርጭትን ለመግታት መንግሥታት፣መገናኛ ዘዴዎችና ሌሎች ድርጅቶች በጋራ የሚሰሩበትን ሥልት ይጠቁማሉ ተብሎ ይጠበቃል።ኢትዮጵያ የዓለም የፕረስ ቀን ስብሰባን ስታዘጋጅ የዘንድሮዉ የመጀመሪዋ ነዉ። DW

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

በተያያዘ ዜና የምያንማር መንግሥት ያሰራቸዉ ሁለት የሐገሪቱ ጋዜጠኞች ዛሬ የዓለም የፕረስ ነፃነት ሽልማትን ተሸልመዋል።ለሮይተር ዜና ወኪል ይሰሩ የነበሩት ጋዜጠኛ ክያዉ ሶኢ ኦ እና ዋ ሎኔ የታሰሩት ታሕሳስ 2010 ነዉ።ሁለቱ ጋዜጠኞች የታሠሩት የምያንማር መንግስት ጦር የሮሒንጂያ ሙስሊሞችን በጅምላ ሥለ መረሸኑ ለመዘገብ ምርመራ በማድረጋቸዉ ነዉ። የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፣የሳይንስና የባሕል ድርጅት UNESCO/Guillermo Cano ለሁለቱ ጋዜጠኞች ያዘጋጀላቸዉን ሽልማት ለየተሸላሚዎቹ ተወካዮች ዛሬ የሰጡት የኢትዮጵያና የአፍሪቃ ሕብረት ባለስልጣናት ናቸዉ። DW

የየመን መንግስት የፀጥታ ኃይላት እየያዙ አልባሌ ሥፍራ ያጎሯቸዉ የአፍሪቃ ስደተኞች በኮሌራ በሽታ በሞታቸዉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) አስታወቀ።የየመን ስደተኛ መንግስትና ተባባሪዎቹ ኃይላት በጦርነት ወደ ወደመችዉ ሐገር ሲገቡ የያዟቸዉን ከ1400 የሚበልጡ ስደተኞች አደን ዉስጥ አንድ የቆሸሸ ኳስ ሜዳ ዉስጥ አከማችተዋቸዋል።IOM እንደሚለዉ ከስደተኞቹ ቢያንስ 8ቱ በኮሌራ በሽታ ሞተዋል።በአካባቢዉ ሌሎች 200 ሰዎች በበሽታዉ መለከፋቸዉ ተዘግቧል።ከሟቾቹም፣ በሕይወት ከሚገኙ ስደተኞችም አብዛኞቹ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ።ስደተኞቹ የሠፈሩበት ኳስ ሜዳ ለሰዎች መስፈሪያ ሲበዛ ከባድ እንደሆነ ዓለም አቀፉ ድርጅት ከዚሕ ቀደም አስታዉቆ ነበር። DW

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ተወካዮች ከዚሕ ቀደም የተፈራረሙትን የሠላም ስምምነት ገቢር ለማድርግ «እንቅፋት» ሆነዋል ባሏቸዉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ እየተነጋገሩ ነዉ።ፕሬዝደንት ሳልቫኪር፣ የዋነኛዉ አማፂ ቡድን መሪ ሪያክ ማቸርና የሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ባለፈዉ መስከረም በተፈራረሙት ዉል መሠረት ከ10 ቀን በኋላ ተጣማሪ መንግሥት መመስረት አለባቸዉ።ይሁንና የሳልቫኪር መንግስት በተያዘዉ ቀጠሮ መሠረት ተጣማሪዉ መንግስት መመሥረት አለበት ሲል የማቻር ወገን ግን ለማቸር የደሕንነትና የጥበቃ ዋስትና እስኪሰጥ ድረስ መንግስት ምስረታዉ ለስድስት ወር ይራዘም ባይ ነዉ።የማቸር ተወካይ የአዲስ አበባዉ ዉይይት ዛሬ ከመጀመሩ በፊትም ይሕንኑ ሐሳብ ደግመዉታል። «በተሻሻለዉ የሠላም ስምምነት መሠረት ገቢር ያልሆኑ ቁልፍ ጉዳዮች አሉ።እነዚሕ ቁልፍ ጉዳዮች ገቢራዊ እስኪሆኑ ድረስ ያቀረብነዉ የጊዜ ገደብ አለ።ያላለቁ ጉዳዮችን ለመጨረስ ቢያንስ ስድስት ወራት ያስፈልገናል።አቋማችን ይሕ ነዉ።»በስደት ካርቱም የሚገኙት ሪያክ ማቻር በስምምነቱ መሠረት ወደ ጁባ የሚመለሱት በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግና ክብር ነዉ።ይሁንና ከዚሕ ቀደም ጁባ ዉስጥ እያሉ ተቃጣብኝ ከሚሉት የግድያ ሙከራ ያመለጡት ማቻር ዳግም ወደ ጁባ ለመመለስ ሙሉ ጥበቃ እንዲደረግላቸዉና ዋስትና እንዲሰጣቸዉ ይፈልጋሉ። DW

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0